Sunday, December 9, 2012

ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም አሉ
ኢሳት ዜና<

                                                                                 


--------------""ወያኔዎች ስልጣኑን ለማቆየት እንኳንስ ባድመን አዲግራትንም ስጡን ቢሉዋቸው ሰጥተው ለመደረዳር ዝግጁ ናቸው”
__________"ወያኔ ከተቃዋሚዎች ጋር መደራደር የዲሞክራሲ እና የስልጣን ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር በመሆኑ አይፈልገውም”  < የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ 

ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት
 ቃለምልልስ ነው። ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል።

በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ መሰረዙዋን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መግለጹን ረዩተር ከትናንት በስቲያ ዘግቧል።

እነዚህ ዘገባዎች በስፋት በመገናኛ ብዙሀን በቀረቡበት ሁኔታ ነው፣ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” ከኤርትራ ጋር ወዳጅነት ከፈለጋችሁ ለምን ከኤርትራ ጋር ለምታደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ የመጫዎቻ ቦታው እንዲቀየር ፈለጋችሁ?” በሚል ለቀረበላቸው ድንገተኛ ጥያቄ በመደናገጥ መረጃ የለኝም ሲሉ መለስ የሰጡት።

የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር በውጭ ፖሊሲ ዙሪያ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጥ አካል መሆኑ በህገመንግስቱ ተቀምጧል። አቶ ሀይለማርያም ትልቅ አገራዊ የመነጋጋሪያ አጀንዳ የሆነውን ጉዳይ አለውቅም ማለታቸው አንድም ውሳኔው ከእርሳቸው ውጭ በሆነ አካል የተወሰነ ነው፣ ሌላም ለቃለምልልሱ ሲቀርቡ ረዳቶቻቸው አስቀድመው እንዲዘጋጁ ባለማድረጋቸው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሻንጉሊት ናቸው የሚለውን መልእክት ሆን ብሎ ለማስተላለፍ ከእርሳቸው ጀርባ ባሉ ሰዎች የተቀነባበረ ሊሆን ይችላል” በማለት የኢሳት ዘጋቢ አስተያየቱን አስፍሯል።

አቶ ሀይለማርያም አስመራ በመሄድ ከአቶ ኢሳያስ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም ከአቶ ኢሳያስ ጋር አስመራ በመሄድ ለመነጋገር ከ50 ጊዜ በላይ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። የአቶ መለስ መንግስት ከኤርትራ ጋር ለመነጋገር 5 ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል። አቶ መለስ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሙዋሉ በስተቀር ከአቶ ኢሳያስ ጋር እንደማይነጋጋሩ በፓርላማ ፊት በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ስለ5ቱ ቅድመ ሁኔታዎች ምንም አለማለታቸውን ዘገቢያችን ገልጿል።

” አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ወደ አስመራ በመሄድ ከአቶ
 ኢሳያስ ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ የባድሜን ጉዳይ አላነሱም። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው ?’” ተብለው አስተያየታቸውን የተጠየቁት የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ፣ “ወያኔዎች ስልጣኑን ለማቆየት እንኳንስ ባድመን አዲግራትንም ስጡን ቢሉዋቸው ሰጥተው ለመደረዳር ዝግጁ ናቸው” በማለት መልሰዋል።

ከኤርትራ ጋር ለመደራደር ከመለመን ይልቅ ቀላሉ መንገድ ከተቃዋሚዎች ጋር መደራደር አይደለም ወይ ተብለው ለተጠየቁት ደግሞ ፣ ዶ/ር ብርሀኑ ሲመልሱ ” ከተቃዋሚዎች ጋር መደራደር የዲሞክራሲ እና የስልጣን ጥያቄ የሚያስነሳ ነገር በመሆኑ አይፈልገውም” በማለት መልሰዋል

“አንዳንድ ምሁራን ‘ መንግስት ባድመን ካስረከበ ከትግራይ ህዝብና ከህወሀት ታጋይ ተቃውሞ ሊነሳበት ይችላል’ በማለት አስተያየት ይሰጣሉ ተብለው ለተጠየቁት ደግሞ ፣ ዶ/ር ብርሀኑ ” ወያኔ የትግራይን ህዝብ በሀይል እጨፈልቀዋለሁ ብሎ እንደሚያስብ እና ስልጣኑን የሚያቆይለት መስሎ ከታየው ምንም ነገር ለማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም” በማለት መልሰዋል።

No comments:

Post a Comment