Thursday, August 25, 2016

የነጻነት ጮራ በኢትዮጵያችን በቅርቡ ይፈነጥቃል!!!!
የፈይሳ ሌሊሳ ቤተሰቦች ከሮይተርስ የዜና አውታር ጋር በመኖሪያ ቤቱ ቃለምልልስ አድርገዋል። ወላጅ እናቱ ''መንግስት ቢመለስ 

ምንም አይሆንም ብሏል። ምን ይመስልዎታል?''ተብለው ሲጠየቁ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል።

''እኔ አላምንም እዛው ይሁንልኝ። ልጄን እወደዋለሁ ቢመጣልኝ እፈልግ ነበር ነገር ግን ምን አደርጋለሁ። ብዙ ቀናቶች ሳለቅስ አሳልፌያለሁ። አሁን ግን ጥሩ ስሜት ይሰማኛል። እዛው ባለበት እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ። እሱ ብቻ ባለበት ሰላም ይሁንልኝ እንጂ!''

ባለቤቱ በበኩሏ ''በወቅቱ በጣም ፍርሃትና ድንጋጤ ወሮኝ ነበር። ነገርግን አልተገረምኩም ምክንያቱም አውቀዋለሁና። በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ የተገደሉ ሰዎችን አካል ሲያይ፣ ሲታሰሩና ሲደበደቡ ሲያይ ውስጡ ይቃጠል ነበር። ባደረገው ያልተገረምኩት የውስጡን ቁጭት ስለማውቀው ነው።''የነጻነት ቁንጮ የጀግኖቹ ጀግናምንም ሳይቸግራው ገንዘብ ወይ መኪና
ወርቅ ፣ናሃስ ፣ብር ሳይል ሳይበግረው ዝና :ሁለት ታዳጊ ሕጻናት ልጆቹን፣ አሮጊት እናቱን፣ ባለቤቱን ትቶ የወገኑን ብሶት በዓለም ዓደባባይ አሰምቷል። የነጻነት ጮራ በኢትዮጵያችን በቅርቡ ይፈነጥቃል። እስከዛው ፈይሳ ሌሊሳ ባለህበት ሰላምህ ይብዛ!!!
..
.Tuesday, August 16, 2016

ኃላፊነት የማይሰማው መንግሥት ነው!!!አንጋፋው የተቃውሞ ፖለቲከኛ ዶክተር መረራ ጉዲና ሀገራቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መንታ መንገድ ላይ መቆሟን ተናገሩ፡፡

"ብዙ ህዝብ ባለፉት 25 አመታት አገዛዙ በፈጸመበት ጭቆና መማረሩን የተናገሩት ዶክተር መረራ አሁን ላይ በየቦታው ሰዎች ለተቃውሞ በየአደባባዩ መውጣታቸውንና በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመው ይህ ሁኔታ ባለበት ከቀጠለ ደግሞ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል"

፡፡-+የተቃወመውን ወይም በቀጥታ ድጋፍ ያልሰጠውን ሁሉ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ዴሞክራሲ፣ ደርግ ናፋቂ፣ የደርግ ርዝራዥ፣ የሻዓቢያ ተላላኪ፣ አሸባሪዎች፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች ወዘተ የዕለት ከዕለት ማጣጣያ ከሆኑ ቆይቷል። ህገ መንግስቱ አክብረው፣ በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ድርጅቶችን የአሸባሪነት ስም በመለጠፍ ትግሉ አቅጣጫውን እንዲስት በመገፋፋት፤ ህብረተሰቡ ነፃ ሆኖ እንዳይኖር እንዳይናገር፣ እንዳይፅፍ፣ እንዳይቃወም፣ እንዳይደራጅ በስጋትና ጭንቀት በአገሩ ነፃ ዜጋ ሆኖ እንዳይኖር እየተደረገ ነው፡፡ ሀገሪቱ እኛ ከሌለን ያልቅላታል የሚሉ በስልጣን ላይ ያለው አካል ብቻ ነው ያለነሱ መሪ ያለነሱ አልሚ ያልነበረ ለወደፊቱም የማይኖር ማይመስላቸው ስልጣኑን አኝ አርገው አለቅ ያሉት ;;

ህዋሃትም በሰሞኑ ዘገባው ባለፉት ወራት ሲታዩ የነበሩትን ህዝባዊ ተቃውሞ እንደ ተራ ጩኸት እያጣጣለው ልክ እንደ ደርግ "በጩኸት የፈረሰች ከተማ እያሪኮ ብቻ ነች" የሚል አይነት እድምታ ያላቸው መግለጫዎች እያሰሙ ነው። ዛሬ እንዲህ አይነት መግለጫ ፍሬ ቢስ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ… በጩኸት ከፈረሱ በኋላ፡፡ በግብፅ አብዮት ወቅት አንድ የትጥቅ ትግል የሚያካሄድ ተቃዋሚ ድርጅትን ይመሩ የነበሩ ከማል ሀቢብ የተባሉ ሆስኒ ሙባረክ በወደቁ ማግስት Tahrir Square (በነፃነት አደባባይ) በአፕሪል18 ቀን 2011ዓ.ም ለታተመው Time መጽሔት "እኛ ለ40 አመት በጠመንጃ መገልበጥ ያልቻልነውን ህዝቡ ያለአንዳች የጦር መሳሪያ በ18 ቀን ውስጥ እውን አደረገው" ብለው በመገረም ተናግረዋል።

ሰላማዊ ህዝባዊ የአደባባይ ተቃውሞና ጩኸት መንግስትን ባያሰጋው ኖሮ ለምን ሰው አደባባይ እንዳይወጣ ይከለክላል?

እሪሪሪ ብሎ መጮህ ነፃነት ያስገኛል። ስለዚህ እንጩህ !!