Sunday, April 14, 2013

የኢትዮጵያዊያኑ ፈተና በየመን በእውነት እጅግ ያሳዝናል፣ ያስለቅሳል!


የኢትዮጵያዊያኑ ፈተና በየመን በእውነት እጅግ ያሳዝናል፣ ያስለቅሳል!
ባለፉ ጥቂት ዓመታት ውስጥ የሶማሊያንና አደን ባሕረሰላጤን አቋርጠው የመን ውስጥ ከገቡና ባለፈው የአውሮፓ ዓመት ከተመዘገቡ 107 ሺህ ስደተኞች መካከል ሰማንያ ሺህ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ፡፡በቢሮው የሚንቀሣቀሰው አይሪን የሚባለው የሰብዓዊ ዜናዎችና ትንታኔዎች አገልግሎት አንዳንድ ኢትዮጵያዊያንን አነጋግሮ ሪፖርቱን በዌብ ሣይቱ ላይ አውጥቷል፡


በእውነት እጅግ ያሳዝናል፣ ያስለቅሳል
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ=========>>>VOAMonday, April 1, 2013

በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ

በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራ አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ


የፓርቲው ስያሜ፦” የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” እንደሆነ በምስረታው ጊዜ ይፋ ሆኗል።

ይፋ ከተደረገው የፓርቲው ዓላማና ፕሮግራም ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል 

 በመታገል የኦሮሞ ህዝብ ነፃነቱን እንዲቀዳጅና ራሱን በራሱ ማስተዳደር እንዲችል ይሠራል።
በ አቶ ሌንጮ ለታ ሰብሳቢነትና እና በ አቶ ዲማ ነገዋ ምክትል ሰብሳቢነት የሚመራው አዲሱ ፓርቲ ደንቡን በማጽደቅ በይፋ 

ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።