Thursday, December 13, 2012

አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች ከሦስት ዓመታት እስከ 13 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትናንትና ተወሰነባቸው

<<በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋ መምህርና የመድረክ ፓርቲ አመራር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች ከሦስት ዓመታት እስከ 13 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትናንትና ተወሰነባቸው
አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባን በስምንት ዓመታት፣ የኦህኮ ፓርቲ አመራር የነበሩትን አቶ ኦልባና ሌሊሳን በ13 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ 

ሌሎቹ ተከሳሾች ማለትም ወልቤካ ለሜ፣ መሐመድ ቡሳ፣ ሐዋ ዋቆ፣ ደረጀ ከተማ፣ አዲሱ ሙከሪና ገልገሎ ቱፋ ከሦስት እስከ 12 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳና አቶ ገልገሎ ቱፋ ለአራት ዓመታት ከማንኛውም ማኅበራዊ መብቶቻቸው ታግደዋል፡፡ ሌሎቹም ለሁለት ዓመታት ታግደዋል፡፡ 
ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ አቶ በቀለ ጥፋተኛ አለመሆናቸውንና አድርገዋል በተባሉት ጉዳይ ላይ ምንም ነገር እንዳልፈጸሙ፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት ሲታገሉ ሕዝቡን በድለው ከሆነ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ከመጠየቅና ባለቤታቸው በእሳቸው ምክንያት ከሥራ በመባረራቸው ልጆቻቸው ያለ ገቢ ከመኖራቸው በስተቀር፣ ምንም ያጠፉት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አቶ ኦልባናም ለምን እንደታሰሩ አለማወቃቸውን ከመግለጽ በስተቀር ምንም ባለማለታቸው በሁለቱም ላይ ቅጣቱ ከብዶ ተወስኗል፡፡ 

No comments:

Post a Comment