Sunday, June 30, 2013

የተዘነጉት ኦሮሞ እስረኞች እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ!

የተዘነጉት ኦሮሞ እስረኞች እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ!

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ኦብሴን(ሰማቸው ለደህንነታቸው ሲባል የተቀየረ ነው ) ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ኦብሴ ገና የ20 ዓመት ወጣት እና ....... የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት፡፡ ኦብሴን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል እ­ህቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እንደተለመደው ኦብሴን አገኘናት እና ብዙ ነገሮችንአጫወተችን፡፡ ትረካዋን የጀመረችው እ­ህቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ ተከሰው የተፈረደባቸውን ሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበውየተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉ ነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለትየእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነትአለመሆኑን ነገረችን፡፡ 
ሲፈን ትባላለች በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል ወንድሟን ልትጎበኝ ነው፡፡‹‹ለአንድ ሰው የመጡ የማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶችመሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደ ቤት የገቡት፡፡ስልካችሁን አጥፉ ወደ ማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣ ነው በቁጥጥር ስር ውለካል› አlት ። ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ቀኑ አርብ ነበር፤ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኑን አላየነውምነበር፤ ይሙት ይኑር የምናውቀውነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ የታሠረ ሰው ሲፈታ በሱ አማካይነት መልዕክት ደረሰን ፡፡ ‹አንቺ ደህና ከሆንሽ .,....ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል› የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንን የሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት ጉዳይ ፍርድ ቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለት ጉዳያቸው በኢፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡ 
ቦንሳ በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል አባቱን ልጎበኝ ነው፡፡ ግጥም መግጠም ይወዳል ፡፡እናም በየጊዜው የጀመረውን ግጥሞች የተበላሹ ሲመስለው ቅርጫት ውስጥ ይጥላቸዋል፡፡ ይመስለኛል፤ የቤት ሠራተኛችን እጅ አለበት፡፡ ሲታሰር የቀረበበት መረጃ እነዚህ የተጣሉ ወረቀቶችተሰብስበው ‹ለኦነግ ግጥም ስታዘጋጅ ነው›የሚል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፈቃድ የነበረው፣ ያውምየማይሠራ ሽጉጥም እንዲሁ በማስረጃነት የቀረበበት መሆኑ ነው፡፡›› በማለት ፍርዱ ፍትሐዊ አለመሆኑን እና አባቱም ነጻ መሆኑን እንደሚያምን ነግ­ሮናል፡፡ 
ጂቱ በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡‹‹የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ሲታሰሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜናነው፤ እንኳን አገር ወዳዷ እናቴ ማንም ባገሩ ላይ የሚያደርገውን ነገር ነው አደረጉ ያለው፤›› የዜናውን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ወቅሳለች፡፡ እናቷ ሕዝብና አገር የማሸበር ፍላጎት ሊኖራት ለአገር ፍቅር ሕይወቷን የሰጠች መሆኗን ስታጫውተን‹‹እናቴ ሁልጊዜ የምትነግረኝ ነገር አለ፤ ሕይወቴ ማለፍ ካለበት አገሬን በሚጠቅም ነገር መሆን አለበት ትለኝ ነበር፤›› ብላናለች፡፡ ነገር ግን መንግሥት በአንድ በኩል ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በመሞከር ነው ያሰርኳችሁ እያለ በሌላ በኩል ደግሞየፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፤›› ካለች በኋላ ‹‹ተቃዋሚ መባላቸው ካልቀረ የኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካ እስረኞች እንደሆኑ ቢያምን እንኳ ጥሩ ነው፤›› ብላናለች፡፡ ‹‹እናቴ ለአገሯ ከማንም በላይ ሠርታለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን የኦሮሞ ህዝብ ለእናቴ ውለታዋን እየከፈልዋት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ያለ ሃጢያታቸው ሃጢያት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት›› በማለት ፍርዱ አገር ወዳድእናቷን የሚያዋርድ እንደሆነ በሐዘን ተርካልናለች፡፡ 
የእናቷ በአሸባሪነት መፈረጅ ለጂቱ ማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሰባት መሆኑንም አጫውታናለች፡፡ ‹‹ለትምህርቴ መስጠት የሚገባኝ ጊዜ ያህል መስጠት አልቻልኩም፤ እናቴ የታሰረችው እኔ ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲ መግባት ሲኖርብኝ አሁን ግን ‹ነርሲንግ› እየተማርኩ ያለሁት በዚሁ ተፅዕኖ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የእነርሱን የእስር ዜና ኢቲቪ ከአቀረበበት መንገድ አኳያ ትምህርት ቤት ውስጥ ራሱ እኔን መቅረብ የሚፈሩ ሰዎች አሉ፤› በማለት የእናቷ እስር በእርሷ ማኅበራዊ ሕይወቷ ላይ ያጠላበትን ጥላ አጫውታናለች፡፡ 
በእናቴ ስም ተይዞ የነበረው የቀበሌ ቤታችን በልማት ስም ሲፈርስ እንኳን ለጎረቤቶቻችን በምትኩሲሰጣቸው ለእኛ ግን አልተሰጠንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መታወቂያ እንኳን ለኛ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም›› ቤታቸውን ካፈረሱባቸው በኋላ አክስቷ ጋር እየኖረች እንደሆነ ስትነግረን በየመሐሉ እየገታችው ታወራልን የነበረው እምባዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲወርድ ማድረግ የቻልነው ነገር ቢኖር በዝምታ ማጀብ ነበር፡፡ 
‹‹ያለ አባት ያሳደገችኝን የእናቴን ፍቅሯን አልጠገብኩትም›› የምትለን ጂቱ ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለኔ የሚገባኝ ቦታ ቃሊቲ አልነበረም፡፡››በማለት ብዙ ነገር መሥራት በነበረባት ጊዜ ቃሊቲ በመመላለስ እንዲባክን መንግሥት እንደፈረደባት እንደሚሰማት ነግራናለች፡፡ ‹ቶለሼ በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡‹አራት ዓመቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ነው ያሳለፍኩት፤ ከ16 ዓመታት በኋላ ከእስር የተፈታው አባቴ የራሱን ሁሉ ነገር ትቶ ሕይወቱን ለኔ መስዋዕት ባያደርግ ኖሮ አልወጣውም ነበር›› እናትዋ ከመታሰሯ ሁለት ወር ያክል ቀድሞ በተፈታው አባቷ ድጋፍ ከብዙ ቀውስ እንደተረፈች እየነገረችን ከናቷ ጋር የነበራትን ፍቅር ‹‹እናቴ ሁለ ነገሬ ነች!››ብላለች፡፡ 
‹‹እናቴን ሊጎዳ የሚያስብ ሰው እኔን አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ተሳቅቄ ነው የምኖረው›› በማለት በዙሪያዋ ያለውን ወዳጅ እና ጠላት እንኳንማመን እየቸገራት እሷ ራሷም ቢሆን ከማኅበረሰብ የመነጠል እና የመስጋት ስነልቦናዊ ችግር ውስጥ እንደሆነች አስረድታናለች፡፡ 
‹‹የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ‹የቤታችን ሰላም እናፍቅር ከበቀለ ገርባ ጋር ታስሯል› ያለችው በጣም ትክክል ነው›› በማለት በታሰሩት ሰዎች ቁጥርእኩልየሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ፈተና ውስጥ እያለፉ መሆኑን አበክራ ነግራናለች፡፡ 
የቶለሼ ታሪክ የብቻዋ ታሪክ አይደለም፡፡ የሌሎች የብዙ ቤተሰቦቻቸው የታሰሩባቸው ኦሮሞ ቤተሰቦች ታሪክ ነው፡፡ ቦንሳ ‹‹እንደኔ ሁሉ ችግር ላይ ያሉ፣ አባቶቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ ልጆች አሉ›› ፡፡ በእስረኞች መሐል ‹‹ተነስቷል በሚልፀብ›› ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ሌላ ተጨማሪ ጫና አሳድሮባቸዋል ፡፡ እዚህ የቀሩት ታሳሪዎችም አጋሮቻቸውን በማጣት ለብቸኝነት ስሜት ተዳርገዋል፡፡ 
ከነርሱ መዝገብ ውጪ ያሉ ሌሎችም እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው በተመሳሳይ ፈተና ውስጥ መሆናቸውን እስረኞችን ለመጎብኘት በሄድንባቸው ጊዜያት ተረድተናል፡፡ ይልቁንም፤ ከቦታ ቦታ እያዘዋወረ ስቃያቸውን ያበዛል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ወደ ዝዋይእንዲዘዋወር የተደረገው ከታሰሩት ኦሮሞዎች አቶ በቀለ ገርባ­ ተጠቃሽ ነው፡፡ 
አቶ በቀለ ባለቤት ከስራ ገበታዋ አባረዋትም ልጁ በእናትዬው መፍጨርጨር ሕይወታቸውን እንዲመሩ ከመገደዳቸውም በላይ አሁን የቤቱን አባውራ ለመጠየቅ ዝዋይ ድረስ እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት የፖለቲካ አይደሉም የሚላቸውን የፖለቲካ እስረኞችን ከነቤተሰቦቻቸው ከሚቀጣበት መንገድ ይታረም ዘንድ ሊጠየቅ ይገባዋል በማለት የምንመክረው፡

Juukii Bareentoo

Saturday, June 15, 2013

የወያኔ እስረኞች ነን !

የወያኔ እስረኞች ነን !

አቶ በቀለ ገርባን አቶ ሌሊሳ ኦልባናን እንዲሁም ብዙ ስማቸዉን ያልዘረዘርናቸዉ የኦሮሞ ታጋዬችን ወያኔ ለቅሞ ቢያስራቸውም…. ነገ ብዙ ሌሊሳዎች…. ብዙ ካሚል ሸምሱዎች…… ብዙ በቀለዎች …አንደ አሸን እና እንደ እንጉዳይ ወደ ትግሉ መድረክ ብቅ ልንል ይገባል። ምናልባት ወደ እንደዚህ አለው ትግል ለመግባት ፍርሃታችን ይዞን ይሆናል….ላለመታሰር ብለንም ፈርተን ይሆናል…..አልገባን ይሆን ይሆናል ወይንም እውነታውን እየካድን ሊሆን ይችል ይሆናል እንጂ አሁንም የወያኔ እስረኞች ነን። ምናልባት ከእነ ካሚል ሸምሱ እና ከእነ አቶ በቀለ ከእነ አቶ ሌሊሳየሚለየን እኛ መዝገብ የማያውቀን እስረኞች እና ቤታችን የምናድር ግዞተኛ መሆናችን ብቻ ነው።እኛ ሁላችንም ከፍርሃት በታች ተዘግተን ፣ ለፍርሃት ባሮች ሆነን ድፍን 21 ዓመታት አናታችን ላይ ዳንኪራቸውን እየረገጡብን፣ በብዙ አዋረዱን ላላፉት 21 ዓመታት በፍርሃት የወያኔ የማስፈራሪያ ሰለባዎች ሆንን። አሁን ግን ሁላችንምከተሸሸግንበት፣ የሞት ሽታ ከሸተተን መንደር መዉጣት እና ወያኔ…በተራው ሊፈራ እና ሊደነግጥ ይገባዋል።
ወዳጆቼ በፊንፊኔ ላይ የምንኖር ኦሮሞዎች እኛ ብቻቁጥራችን ከሺህዎች በላይ የምንዘል በወጣት የዕድሜክልል የምንገኘ ሁሉ መዝገብ የሚያውቀው እስረኛ ለመሆን ብንፈቅድ እንኳን ወያኔ እኛን ሁላችንንም ለማሰር አቅም አይኖረውም። በ1997 ዓ.ም በነበረው እንኳን ወያኔዎች ማሰር የቻሉት 50 ሺህ ሰው እንኳን አይሞላም ፤ በፍርሃት በየቤታችን ተቀፍድደን ከምንታሰር በዘመናችን ትውልድ የሚዘክረው ታላቁ የኦሮሞዎችን ትግል እንቀላቀል። ይህ ታላቅ ዘመቻ በእርግጥ ታላቁን የኦሮሞ ትግል ለመጀመር ፈር ቀዳጅ ይሆናል። አሁን ከፍርሃታችን ወጥተን ትልቅ እርምጃ ተራምደናል፤ ከዚህ በሃላ ተመልሰን ወደ ፍርሃት ቀንበር መግባት አይገባንም።ወያኔ ምንም ሊያደርገን አይችልም፤ ምናልባት ሊያደርጉን ከቻሉ የሚችሉት እኛን ማሰር ብቻ ነው፤ይህ ደግሞ በራሱ ትልቅ ድል ነው። 30 ሚሊዮን መዝገብ የነካውን እስረኛ መመገብ፣ ማስተዳደር፣ መጠበቅ በራሱ ወያኔን ያናጋዋል፣ ያፈርሰዋል። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ የልባችንን በልባችን ይዘን ክፍተቶቻችንን እርስ በርሳችን በአንድነት ተነጋግረን ዛሬ በዋናነት ስለምንሻዉ ነፃነት ተገንዝበን በአንድነት መውጣታችንም ሆነ መታሰራችን ወያኔን ከተቀመጠበት የስልጣን ኮርቻ ሊያወርደው የሚችል ትልቅ ውሳኔ ነውና ወደ ፊት እንበል ይለይለት።
ድል ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ!

Sunday, June 9, 2013

የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!!

የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!!


እ.አ.አ በ1997 በጨረታ ወደ ግል ንብረትነት ተዛወረ የተባለው የኦሮሞ ሀብት የተሸጠው 172 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ሽያጩ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ሽያጩን ተከትሎ በርካቶች አርረዋል፤ ተቃጥለዋል። “ዋይ ዋይ ወርቃችን” ብለው አንብተዋል። ህዝብ የፈለገውን ቢል ደንታ የሚሰጠው አካል ስለሌለ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኦሮሞ ህዝብ እጅ በአዋጅ ተነጠቀ።
ሽያጩን እውን ያደረገው የኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሀሰን አሊ ሲሆኑ፣ የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ አሰፋ አብርሃ የኤጀንሲው ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ። ሁለቱም ባለስልጣናት ዛሬ ሃላፊነት ላይ የሉም። ስለ እውነትና ስለአገር ሲሉ የሚያውቁትን ለመተንፈስ እስከዛሬ ቢጠበቁም ያሉት ነገር የለም። ሃሰን አሊ ሲኮበልሉ፣ አቶ አሰፋ አብርሃ ከወንድማቸው ጋር በሙስና ተወንጅለው የወህኒ ቤት ጊዜያቸውን አጠናቀው እየኖሩ ነው።
ምዕራብ ሃረርጌ አሰበ ተፈሪ መምህር የነበሩትና ኢህአዴግን መንገድ ላይ የተቀላቀሉት ሀሰን አሊ ካገር መኮብለላቸውን ተከትሎ የተለያዩ መረጃዎች ይወጡ ነበር፡፡ በርካቶች ጉዳዩን ከኦነግ ጋር ቢያያይዙትም “ካገር ውጡ ተብለው፣ ሀብትና ንብረት ተዘጋጅቶላቸው ኮብልለዋል” የሚል መረጃ ለባለስልጣናትና ለባለሃብቱ ቅርብ ነን ከሚሉ ወገኖች እንሰማ ነበር። በወቅቱ ኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ በነበረኝ ሃላፊነት ሳቢያ ከሰማኋቸው መረጃዎች ውስጥ ሃሰን አሊ “ውጡ” ተብለው እንደ ኮበለሉ የሰማሁት መረጃ ካለኝ ሃላፊነት ጋር ተዳምሮ እንዳጣራው ወሰንኩና ጊዜ ሰጥቼ አነፈንፍ ገባሁ።
የሌሎችን ባላውቅም እንደ ኦሮሞነቴ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ውድ ንብረት ለሼኽ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ መሸጡ ሁሌም ያንገበግበኛል። ሽያጩን አስመልክቶ የተለያዩ ጽሁፎች ቢወጡም እኔ ካሰባሰብኩት መረጃና እውነት ጋር የሚመጣጠን መስሎ ስላልታየኝ የድረገጽ ጋዜጣ ለመተንፈስ ወሰንኩ።
ሼኽ መሐመድ አላሙዲና ሃሰን አሊ እንዴት ተዋወቁ?
ሼኽ መሀመድ አላሙዲና ሀሰን አሊን እንዳስተዋወቃቸው የነገረኝን ሰው ባንድ አጋጣሚ የማወቅ እድል አጋጥሞኝ ነበር። ተግባሩ ብዙም ደስ ስለማያሰኝ ፊት እነሳው ነበር፡፡ ባለስልጣናትን በገንዘብ እየደለለ ሲሰርቅ ብዙ ጊዜ ስለማውቅ አልወደውም ነበር። የራሱን ትልቅነት ለመግለጽ ድንገት ቢሮዬ በመጣበት ወቅት የነገረኝ ፍንጭ ትዝ ሲለኝ ላገኘው ወሰንኩ። ይህ ሰው ባለኝ ሃላፊነት እንደፈለገኝ ላገኘው ስለምችል፣ እሱም ለሚሰራው ድለላና አየር ባየር ንግድ እኔ ከፈለኩት ቅር ስለማይለው ፊት ነስቼው ያቋረጥኩትን ግንኙነት እንደገና መቀጠል ብቸኛ አማራጬ ሆነ፡፡ይህን ሰው ከተጠቀሙበት በኋላ ወርውረውት በነበረበት ወቅት ላይ ስላገኘሁት የፈለኩትን ለማግኘት አጋጣሚው ተመቻቸልኝ፡፡
ቀደም ሲል ሃሰን አሊን ያውቃቸው እንደ ነበር፣ አብረው ሃድራ እንደሚያሞቁ፣ የፈለገውን ነገር ማድረግ ከፈለገ ሃድራው በሚሞቅበት ወቅት እዛው በሙቀት እንደሚያከናውኑ አውግቶኛል። ለዚህ ጽሁፍ ስለማይጠቅም እንጂ በርካታ ታላላቅ ጉዳዮች ቢሮ ውስጥ ሳይሆን በተፈረሸ መደብ ላይ እንደሚከናወን በስፋት ስም እየጠቀሰ ነግሮኛል። እንግዲህ ይህ ሰው የ“ባለሃብቱ” ወዳጅ ነበር። ለዚያውም የመጀመሪያ!
በዚሁ ሽርክናቸው ሰውየው ሃሰን አሊን መተዋወቅ እንደሚፈልጉ ባሳወቁት መሰረት ሃሰን አሊን በመያዝ ሳር ቤት አካባቢ አገናኛቸው። ባለሃብቱ በወቅቱ ብዙም የሚያውቃቸው ባልነበረበት ወቅት ሃሰን አሊን አስቀድመው ተወዳጁ። በመኖሪያቤት ሃድራ ላይ የተመሰረተው ወዳጅነት ጠበቀ። በኦሮሚያ በኩል አድርገው ዋናውን ሳሎን ወረሱ።
ሀሰን አሊ ከኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነታቸው ለቀው ስደትን ለምን መረጡ?
አሰበ ተፈሪ የሁለተኛ ደረጃ መምህር እያሉ ወያኔ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ በረዣዥም በአለም የምግብ ድርጅት ሽንጣም የጭነት ተሽከርካሪዎች በሸራ ተሸፍነው ቀለሃ ሳያባክኑ ወደ ሃረርና ድሬዳዋ ሲተሙ ቆቦ የምትባል የመስመር ከተማ ላይ ሆኜ የመከታተሉ እድል ነበረኝ፡፡ ወያኔ የሀረርንና የድሬዳዋን ከተማ ለመያዝ ስትሮጥ አሰበ ተፈሪ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃትምህርት ቤት ከአቶ ሀሰን አሊ ጋር ተገናኙ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ሀሰን አሊ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኑ፡፡ አስተማሪው ፕሬዚዳንት በስልጣን በቆዩባቸው ጊዜያት ከሚታሙባቸው ከፍተኛ ሙስናዎች መካከል፣ ባሌ ውስጥ ተከስቶ በነበረው የዋና ከተማነት ጥያቄ ተከትሎ የተቀበሉት ብር ነው። የባሌ ሮቤ ነጋዴዎች ሮቤ በዋና ከተማነት እንድትቀጥል ያሰባሰቡትን አንድ ሻንጣ ብር በስጦታ አቅርበውላቸው ነበር። ያረፉበት ቤት ድረስ የቀረበላቸው ስጦታሮቤን በዋና ከተማነት ጸንታ እንድትቆይ ወሰነ። ገንዘብ ተናገረ። ከአገር የመኮብለላቸው ጉዳይ ከዚሁ ጋር ተያያዥ ነው ቢባልም በፖለቲካው መስመር ደግሞ ኦነግ ናቸው የሚል ሰፊ ሃሜትነበረባቸው። እኔ ባካሄድኩት ማጣራትና በሰበሰብኩት መረጃ መሰረት ቀደም ሲል የጠቀስኩዋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው፣ አቶ ሀሰን አሊ በለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ በሙስና መጨመላለቃቸው ለመኮብለላቸው ዋናው ምክንያት ስለመሆኑ ሚዛን የደፋ ምርመራ አካሂጃለሁ፡፡
የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን ለመሸጥ ወጥቶ በነበረው ጨረታ የተለያዩ ኩባንያዎች ቢሳተፉም ሼክ መሀመድ አላሙዲ ያሸነፉበትድራማና የሀሰን አሊ ወደ አሜሪካ መኮብለል በተመለከተ ያሰባሰብኩትን መረጃ ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡ ለራሴና ለወዳጆቼ ደህንነት ስል ስም ከመጥቀስ ግን እቆጠባለሁ፡፡
ሃሰን አሊ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የሚመሩት የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የለገደንቢን ወርቅ ሽያጭ ጨረታ ከማስፈጸሙ በፊት ለገደንቢን አስመልክቶከፍተኛ የማባበል ስራ ተሰርቷል። በየጊዜው ሲደረጉ የነበሩ ማባበሎችን ይከታተል የነበረው የመረጃ መነሻ እንዳስረዳኝ ለገደንቢ እንደ መስቀል ሰንጋ ጠልፎ የተበለተው አስቀድሞ ነው። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃቶችከኢትዮጵያ ኪስ የሚወስዱትን ንብረት ህጋዊ ለማስመሰል ያቋቋሙት ይህ ኤጀንሲ በቁንጮ አመራሩ መመሪያ ሰጪነት ባካሄደው ጨረታ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችም ተሳትፈው ነበር።
አንድ ቀን እዛው ቤት ውስጥ እንደተለመደው ሃድራው እየሞቀ በጨረታው የተሳተፈ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ የተሻለ ገንዘብ ማስገባቱ ባለሃብቱ ጆሮ ይደርሳል፡፡ ኩባንያው ያስገባው ገንዘብ መጠን ይገለጽላቸዋል፡፡ መጀመሪያ ያስገቡት ሰነድ ተቀይሮ ሌላ ሰነድ እንዲያስገቡ በተነገራቸው መሰረት አዲስ ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ድራማ ለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ ሀብትነት ወደ ሼክ መሀመድ አላሙዲ ንብረትነት በ1997 ለስምንት ዓመት ተዛወረ፡፡
በጉጂ ዞን ሻኪሶ ወረዳ ሳካሮ በተባለው ቦታ የተሰራው ይህ አዲስ 4ኪሜ የዋሻ መንገድ ቀጭን ረጅም ጥቅልል ብረት ከምድር በታች እስከ 70ሜትር ይዘልቃል፡፡
በዓመት 3.5 ቶን ወርቅ በአማካይ ሲያመርት ቆይቶ ምርቱን በማሳደግ በአሁኑ ሰዓት ከ4.0 ቶን በላይ ማሳደጉን ይፋ ያደረገው ሚድሮክ ጎልድ በዚህ ዓይነት አሳፋሪ ድራማ ወደ ግል ይዞታነት ከተዛወረ በኋላ ሀሰን አሊ አገር ጥለው እንዲወጡ ተወሰነባቸው፡፡ የሽያጩ ድራማ ደብዛ መጥፋት ስላለበት ሀሰን አሊ በኦነግ ስም ካገር እንዲኮበልሉ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ ከተጠናቀቀ በኋላ አሜሪካ ለስራ በሚል ሰበብ እንዲሄዱ ተደርጎ በዛው ቀሩ፡፡ አሜሪካን አገር ሱፐር ማርኬትና ነዳጅ ማደያ ተገዝቶላቸው ስለነበር ከነቤተሰቦቻቸው ወደ ንግድ ዓለም መግባታቸው ተሰማ። አሜሪካ ተገኝቼ ማጣራት ባልችልም አደራውንእዚያው ለምትኖሩ ታጣሩትና ትጎለጉሉት ዘንድ አሳስባለሁ። ምንም በሉ ምን የኢትዮጵያው “ለገደንቢ” የግለሰብ “ሚድሮክ” የሆነው በተፈረሸ ፍራሽ ላይ ነው – በምርቃና!!
ከ2005 በኋላ ለገደንቢ ወርቅ የማን ይሆናል?
ሚድሮክ ጎልድ ይፋ እንዳደረገው ሃያ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ዘመናዊ መሳሪያ ተገዝቶ ወርቅ የማምረቱ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ በማስፋፊያ በተከለሉ ቦታዎች ላይ ከ4.7 እስከ 6.52ቶን የሚደርስ ወርቅ በዓመት ለማምረት የተጀመረው ስራ ውጤት ማሳየት ጀምሯል፡፡ ስለማስፋፊያ ስራው አዲስ ስምምነት መንግስትም ሆነ ማዕድን ሚኒስቴር ያሉት ነገር የለም፡፡ ሚድሮክ ከኮንትራት ዘመኑ (2005) በማለፍ እስከ 2020 በያዘው ዕቅድ ከ70 ቶን በላይ ወርቅ ለገበያ በማቅረብ ለመሸጥማቀዱን በመንግስት ሚዲያ ይፋ አድርጓል፡፡ 1.6 ቢሊዮን ዶላርየተጣራ ትርፍ እንደሚያገኝም አፉን ሞልቶ ተናግሯል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አገርምን ታገኛለች በሚለው ጉዳይ ላይ ጥያቄ ማንሳትሃጢያት ነው፡፡ያስገድላል፣ ያሳስራል፣ ያስደበድባል …
ለመሆኑ ከ1997 ለስምንት ዓመት ኮንትራት የተሰጠው ለገደንቢ ወርቅ እስካሁን በአላሙዲ እጅ እንዲቆይ የተደረገበትውልና የውሉ ዝርዝር ለምን ምስጢር ሆነ? በምን ዓይነት አዲስ ውልና ክፍያ ተጨማሪ ቦታ ተከለለ? በምን ያህል ዶላር የሽያጭ ውልና መግባቢያ ባለሃብቱ ወርቁን እንዲዝቁ ተወሰነ? ማዕድን ሚኒስቴር አለሁ ቢል ወይም ራሱ ሚድሮክ በግልጽ በድረ ገጹ ቢያሰፍረው ቢያንስ ቂማችን ይቀንስ ነበር።
ለወትሮውም በብድር እንደተሸጠ የሚነገርለት ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ብድሩ ሙሉ በሙሉ መከፈሉ በ
ይፋ ባይገለጽም ሀብቷን በድራማ ጨረታ በብድር የሸጠችው ኦሮሚያ ህዝቧ ከሃብታቸው ድርሻቸው 2% ብቻ ነው፡፡ከሮያሊቲክፍያ ማግኘት የሚገባትን ሚጢጢ ገንዘብ እንኳን ባግባቡና በወቅቱ አታገኝም፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር አቶ ሱፍያንየመንግስት የልማት ድርጅቶች ሃላፊዎችን ሰብስበው ሲያነጋግሩ ‘’ለመሆኑ ሚድሮክ ጎልድ ላይ ያለን ድርሻ ስንት ነው? ማስገባት ያለባቸውን ገንዘብስ ይከፍላሉ?” በማለት መጠየቃቸው በወርቅ ማዕድኑ ዙሪያ ያለውን እንቆቅልሽ ወለል አድርጎ እንደሚያሳይ ስብሰባው ላይ የተሳተፉ በወቅቱ የተናገሩት ነው።
በቀኝ በኩል የሚታየው አርቲፊሻልና በኬሚካል የተፈጠረ ሐይቅ ሲሆን በግራ ደግሞ ያለው የተፈጥሮ ሐይቅ ነው፡፡ አርቴፊሻሉ ሐይቅ ቀለም የተከሰተው በቁፋሮ የሚወጣውን ወርቅ ለማጣራት ጥቅም ላይ በሚውለው ኬሚካል አማካኝነት ነው፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ከለገደንቢ ከርስ የሚጣራው የኦሮሚያ ደም /ወርቅ/ ወደ ገበያ ሲሄድ ቁጥጥር አለመደረጉ ሌላው አስገራሚ ድራማ ነው፡፡ አገርና ህዝብ እመራለሁ የሚለው ኢህአዴግ ሚድሮክ በቀጠራቸው ባንዳዎች አማካይነት ወርቁን በሉፍትሐንሳ አውሮፕላን ብቻ የሚያመላልሱት ለምንድ ነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ የለውም፡፡ በሌላ አነጋገር አገር የሚገባትን የሽያጥ ታክስም ወደ ውጪ በሚላከው መጠን መሰረት እየተሰላ አይከፈልም። በእንዲህ ዓይነት መልኩ በአገራችን ኢኮኖሚና ህልውና ላይ ይጋለብበታል፡፡ ሚድሮክ ወርቅ አንዱ ማሳያ እንጂ ማጠቃለያ ግን አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወርቁን ወደ ሚላክበት ስፍራ በማመላለስ የትራንስፖርት ንግድ ለመነገድ ጠይቆ “አይሆንም” ነው የተባለው ለምን? ኢህአዴግና ባለስልጣናቱ ለዚህም መልስ የላቸውም፡፡ አገር ወዳዶች ግን መልሱን ያውቁታል፡፡ ልባቸው እየደማ፣ ኅሊናቸው እየቆሰለ ፣ አገራቸው ስትታረድ የሚመለከቱወገኖች ለምንና? እንዴት? ብለው ሲጠይቁ አሁንም ይገደላሉ፣ይታሰራሉ፣ ይገረፋሉ፣ህዝብን በማነሳሳትና በሽብርተኛነት ወንጀል ይከሳሳሉ፡፡ እስከ ህልፈታቸው ወህኒ እንዲጣሉ የተሸጡ ወንድሞቻቸው ይፈርዱባቸዋል፡፡ በሃገረ ማሪያምና በቡሌ ሆራ ወረዳ የሆነው ይኸው ነው!
ሚድሮክ ወርቅ እያግበሰበሰ ያለው ሃብት ስለጣፈጠው በግልጽ ባልተቀመጠ ውል ግዛቱን እያስፋፋ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ሲያፈናቅል የቡሌ ሆራና የሀገረ ማሪያም ነዋሪዎች ከልማቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ባካባቢው ላይ እየደረሰያለው ብክለት ጉዳት እያደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው በመቃወማቸው በሽብርተኛነት ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ጥር 5 ቀን 2002 በሻሸመኔ ምድብ ችሎት በሽብርተኛነት ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የአካባቢው ተወላጆች ላይ የደረሰውን መከራ የሰብአዊ መብት ጉባኤ 34ኛ መደበኛ ጉባኤ ህዳር 8 ቀን 2003 ዓም ስም በመዘርዘር ይፋ አድረጓል፡፡ ከሳምንት በላይ ትምህርት ተቋርጦ በርካታ ተማሪዎችና ነዋሪዎችም ታስረው እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡
የፌዴራሉን እንተወውና ኦሮሚያና ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በምን ምክንያት ተጣሉ? በወቅቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና ኦህዴድ፣ወደፊት የባለሃብቱና የኦሮሚያ እጣ ፈንታ ምን ይመስላል? በሚሉት ርዕሶች ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባ ይዤ እመለሳለሁ። በመግቢያዬ እንዳልኩት ዋይ ዋይ ወርቃችን!!


Juukii Bareentoo 

Tuesday, June 4, 2013

Human rights situations that require UNHRC’s attention – Ethiopia

The current Ethiopian Government has continued systematic restrictions on basic rights and freedoms to which all humans are entitled, including freedom of thought and expression, and civil and political rights. The independent media, political opposition parties, and civil societies, are continuously harassed and intimidated by the government; many of them are outlawed, and political leaders are sentenced to long prison terms under the so- called Anti-Terrorism proclamation.


June 4, 2013
Oral Statement: by Mr. Garoma Wakessa
Executive Director the Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)
Item 4: Human rights situations that require the Council’s attention – Ethiopia
Thank You Mr. Chairman,
Human rights violations in Ethiopia are gross, are of all kinds and widespread. Due to the limited time allotted to this Oral Statement, I will focus on the most crucial components.
The current Ethiopian Government has continued systematic restrictions on basic rights and freedoms to which all humans are entitled, including freedom of thought and expression, and civil and political rights. The independent media, political opposition parties, and civil societies, are continuously harassed and intimidated by the government; many of them are outlawed, and political leaders are sentenced to long prison terms under the so- called Anti-Terrorism proclamation.
The provisions of Ethiopia’s 2009 Anti-Terrorism Proclamation define terrorist activities so vaguely that they are easily used to criminalize all civil society activists and political opposition leaders, supporters, and peaceful demonstration organizers.
Today, media practitioners in Ethiopia face charges such as treason and terrorism simply because they put information on paper -and publish it. Opposition political party leaders and supporters face the same charge because they exercise their political freedoms.

In the past two years, Muslims who demanded non-interference of government in their religious affairs have been harassed, sometimes killed or imprisoned. University students who staged demonstrations to demand better treatment at their University campuses were beaten or imprisoned under the Proclamation.
Mr. Chairman,
In Ethiopia, the giving away of land to Transnational Corporations and other wealthy states has become a critical and burning issue for millions of family members. Thousands of small land holders in Gambela, (South Ethiopia), in Oromia Regional State ( Central and Western Ethiopia) and Benshangul ( South West part of Ethiopia) have been forcefully evicted from their ancestral lands and become jobless and homeless; those who resisted forced eviction or demanded compensation for their plundered land have been killed. Others were charged as terrorists and now languish in prison.
Mr. Chairman,
Today, children, women, senior citizens in Ethiopia regularly face starvation and are dying every day. They require the attention of the UN Human Rights Council. The Ethiopian Government has the legal obligation to respect and protect human rights set out in the international human rights conventions it ratified. Investors also should abide by the UN Global Compact – the ten principles which clearly explain their responsibilities in the areas of human rights, labor, and environmental rights in the country in which they are investing.
Mr. Chairman,
The Human Rights League of the Horn of Africa is very concerned with the deteriorating situation of human rights in Ethiopia and calls upon the UN Human Rights Council,
  • Urge the Ethiopian authorities to carry out their obligations under domestic, regional and international obligations to protect and promote freedom of expression, by immediately ending the practice of arresting and prosecuting those who hold different political opinions;
  • Call on the government of Ethiopia to allow the Special Rapporteur on the land issue to visit the country to determine the extent to which the government of Ethiopia and the investors are complying with their domestic, regional and international human rights obligations. It is their responsibility to respect human rights.
Thank you!!
Garoma Wakessa
Executive Director the Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA)