Thursday, December 20, 2012

አራት ኢትዮጵያዊን ጋዜጠኞች የሄልማን/ሃሜት ተሸላሚ ሆኑ





አራት ኢትዮጵያዊን ጋዜጠኞች የሄልማን/ሃሜት ተሸላሚ ሆኑ

መስፍን ነጋሽ ,ውብሸት ታየ ,እስክንድር ነጋ ,ርዕዮት ዓለሙ
አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የሚዲያ ሥራ በዓለም እጅግ አዳጋች በሆነበት ሀገራቸው ሃሣብን በነፃ የመግለፅ መብቶች እንዲከበሩ ላደረጓቸው ጥረቶች (እአአ) የ2012ን ስመ-ጥሩን የሄልማን/ሃሜትን ዓለምአቀፍ ሽልማት አግኝተዋል


በሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ድርጅት በሂዩማን ራይትስ ዋች አስተዳደር ጥላ ሥር የሚገኘው ሄልማን/ሃሜት በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የፖለቲካና ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዒላማ ለሆኑ ደራሲዎችና ጋዜጠኞች ሽልማቱን የሚሰጠው በያመቱ ነው።

ስመ ጥሩ ሽልማት መጠሪያውን ያገኘው እአአ በ1950ዎቹ ፀረ-ኮሚኒስት ምርመራዎች ወቅት ወከባ ከደረሰባቸው ሁለት ጋዜጠኞች ከሊልያን ሄልማን እና ዳሸል ሃሜት ነው።

እስክንድር ነጋ ፈንታ፥ ነፃ ጋዜጠኛና ብሎገር ወይም የኢንተርኔት አምደኛ፥
​​

ርዕዮት ዓለሙ ጌቤቦ፥ በታገደው ሣምንታዊ “ፍትሕ” ጋዜጣ አምደኛ፥
​​
ውብሸት ታየ

ውብሸት ታየ አበበ፥ የተከለከለው ሣምንታዊ “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፥
​​
መስፍን ነጋሽ

የ “አዲስ ነገር Online” አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ፥ የዘንድሮውን ሽልማት ካገኙ  ከ 19 ሀገሮች የተውጣጡ 41 ጋዜጠኞችና ፀሀፊዎች መካከል ናቸው።
​​
እስክንድር፥ ርዕዮትና ውብሸት ባሁኑ ወቅ ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ የአዲስ ነገሩ መስፍን ነጋሽ ግን፥ እአአ በ2009 ዓ.ም ሀገሩን ጥሎ ወጥቶ በስደት ላይ ይገኛል።

ባጠቃላይ አራቱም ግን በሀገሪቱ በፀረ ሽብር ሕግ መሠረት በዚህ ዓመት ጥፋተኞች ተብለው ተፈርዶባቸዋል።

No comments:

Post a Comment