Saturday, December 19, 2015

የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል

"ጥቂቶች በብርሀን ፍጥነት ተዝቆ ወደማያልቅ ሀብት የተመነጠቁበት መንኮራኩር፣ መሬት "

ከ5 ዓመታት በፊት እኚህ ክቡር ሰው ሲናገሩ መስሚያ ጆሮ ቢኖራችሁ ዛሬ መያዣ መጨበጫ ባልጠፋችሁ። በነገራችን ላይ ይህ የአቶ በቀለ ገርባ ንግግር እና የአቶ አንዷለም አራጌ ንግግር ምንጊዜም ልቤን የሚያነሳሳኝ፣ በሀገሬ ተስፋ ከሚሰጡኝ መሳጭ ንግግሮች ዋነኞቹ ናቸው

ሀገር መምራት ቀላል እንዳልሆነ እናውቃለን ነገር ግን ከዓመት ዓመት የሕዝቡን ብሶት እያዳመጠ እየተሻለው፣ ልምድ እየቀሰመ ሀገሪቱን ሕዝቡን ወደፊት ማራመድ ሲገባው ከዕለት ወደ ዕለት ወደኋላ እየተመለሰ፣ የኋሊት እየሄደ ሀገሪቱን መምራት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል::

የኤፌድሪ ሕግ መንግስት እንደሚናገረው ፣ የገዢው ሥርዓት የፖሊሲ ሰነድ እንደሚገልጸው መሬት የመንግስት እና የሕዝብ ነው ይላል:: ነገርግን መሬት የሕዝብ ነው፣ የመንግስት ነው፣ የሁለቱም ነው? መሬት የማንም አይደለም:: መሬት የገዢ ባለስልጣኖች የግል ንብረት ነው::

እንደፈለገ የሚሸጡት፣ የሚለውጡት፣ ጓደኛ የሚያፈሩበት፣ በዘመድ አዝማድ የሚያከፋፍሉት፣ ለወገን እያሉ ለነሱ ፓርቲ አባላት መመልመያ የሚጠቀሙበት ማማለያ ነው መሬት::

*መሬት የተማረውን ሳይቀር፡ ምሁሩን ሳይቀር ማሳወርያ ሆኗል። ዛሬ ምሁሩን አንዳንድ ቦታ በአበዛኛው በምንመለከትበት ጊዜ ስለፍትሕ፣ ስለመብት፣ ስለ እኩልነት የማያወራበት ጊዜ ደርሷል።ምክንያቱ ይኼ ማሳወርያ ነው ዛሬ በየከተማው እና በአዲስ አበባ ዙርያና ሌሎች ከተሞች አካባቢ በብዛት መሬት እየተሰጣችው አፋቸው ተሸብቧል።ስለዚህ መሬት አፍ መሸበቢያ ነው።

* መሬት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ መሳቢያ ማግኔት ሆኗል። ዳያስፖራ እየተባለ በአንድ ወቅት ግር... ብለው መጥተው፣ እዚህ ወገኖቻችን ሜዳ ላይ ወድቀው አንዲት ስንዝር መሬት የሌላቸው ወገኖች እያሉ በውጭ ቢያንስ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መጥተው መሬት ተቀራምተው ሽጠውት ሄደዋል። ስለዚህ ማግኔት ነው የምንለው ለዚህ ነው።
*መሬት ዛሬ ጥቂቶች በብርሀን ፍጥነት ተዝቆ ወደማያልቅ ሀብት የተመነጠቁበት መንኮራኩር ነው።
ብንመለከት፣ እነድውም አንዳንዶቹን ሀብታሞች ብንጠይቃቸው... በሕዝቡ ዘንድ "ታሪኬ በአጭሩ" እየተባሉ የሚጠሩ አሉ። "እንዴት ነው፣ ይህ ሀብት ከየት መጣ እንዴት አገኛችሁ?" ተብለው ቢጠየቁ "እንደዚህ አድርጌ፣ እንደዚህ ለፍቼ አመጣሁ..." ማለት እንኳ የማይችሉ፣ገንዘቡን እንዴት እንዳፈሩት የማያውቁ...ስለዚህ ዛሬ መሬት እንደዚህ ነው:: መሬት የምንም አይደለም
መሬት ወሳኝ ሀብት መሆኑን እናውቃለን::
እኛ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ሀብት ጋራ ባለን ግንኙነት ምክንያት የዜገነት ደረጃችን በ4 ቦታ የተከፈለ ይመስለኛል:-->

1.መሬቱን የሚሸጡ አሉ አንደኛ ደረጃ ዜጎች
2.መሬቱን ከነሱ የሚቀበሉ አሉ፣ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች

3.እነሱ ሲቀባበሉ ቁጭ ብሎ ትዕይንቱን የሚመለከተ ዜጋ ደግሞ አለ ፤ ሦስተኛ ደረጃ- የበይ ተመልካች
4.መሬቱን ተነጥቆ፣ እትብቱ ከተቀበረበት፣ ተወልዶ ካደገበት መሬቱ ሥፍራ እየተባረረ መሬቱ ለሌላ የሚሰጥ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆነ አርሶ አደር ደግሞ አለ::

እኛ ምንታገለው ለዚህ ነው!!!

*****ደግማችሁ ደጋግማችሁ አድምጡት፣ የተቃውሞው መሠረታዊ ጥያቄዎች ያልገባችሁ ፍንትው ይልላችኋል። ይህ የጭቁን ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው!
የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል