Thursday, February 13, 2014

አራት የኦሮሞ ተወላጅዎች በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ተያዙ...

አራት የኦሮሞ ተወላጅዎች በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ተያዙ....

የምስራቅ አፍሪካ ሰብአዊ መብቶች ሊግ በላከው መግለጫ አራት የኦሮሞ ተወላጅዎች በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል የተያዙት በተለያዩ ቀናት ነው።
ቱምሳ ሮባ ካቲሶ የተያዘው ኢስሊ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ ሲሆን፣ በሁለት መኪኖች የመጡ የጸጥታ ሃይሎች በፈረንጆች አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 1፣ አፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ወስደውታል።
ጫላ አብደላ፣ ናሚ አብደላ፣ እንዲሁም ስሙ በውል ያልታወቀው ሶስተኛው ሰው ደግሞ ፌብሩዋሪ ሶስት በተመሳሳይ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኬንያ መንግስት በጻፈው ደብዳቤ፣ የኦሮሞ ተወላጅዎችን ወደ ኢትዮጵያ ሳይላኩ አይቀርም ብሎአል። የኬንያ መንግስትም በአለማቀፍ ህግ መሰረት የሰዎችን አድራሻ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ደህንነቶች በቅርቡ 2 የኦጋዴን መሪዎችን ኬንያ ውስጥ አፍነው መውሰዳቸው ይታወቃል። ጣራ ከመንካት ያለፈዉን የኦሮሞ ተወላጆችን ስቃይ ፤ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ የዉጪ ሚድያዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በየዕለቱ የሚከሰተዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አለመዘገብ እንዲሁም በዉጪ ሀገር የሚሠቃዩ የኦሮሞ ስደተኞችን የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች እንደ ኦሮሞነታቸዉ ባለመቀበሉ ችግሩን አብሶታል ፡፡ በዉጪ የሚገኙ የኦሮሞ ሚድያዎች ዜናዎቻቸዉ ጠቅላላዉን የኦሮሞ ገፈት ቀማሾችን ያለተኮረ መሁኑ ያሣዝናል ፡፡

No comments:

Post a Comment