Friday, February 28, 2014

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ አብጠለጠለ!


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ አብጠለጠለ
መስሪያ ቤቱ በ2013 ሪፖርቱ በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ሃሳብን በነጻነት የመግልጽና የመደራጀት መብት ቀዳሚ መሆኑን ሪፖርቱ ይገልጻል።
ዜጎች በዘፈቀደ ይታሰራሉ፣ ይታፈናሉ፣ በእስር ቤት ይሰቃያሉ፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ይገደላሉ፣ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ማስፈራሪያ ይደርስባቸዋል እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸዋል።
ፍርድ ቤቶች በመዳከማቸው የፖለቲካ ፍለጎት ማስፈጸሚያ መሳሪያ መሆናቸውን፣ ዜጎች መንግስትን የመለወጥ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን፣ ፖሊስ፣ አስተዳደርና ፍርድ ቤቶች በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው ተጠያቂነት ያለበት ስርአት ማስፈን አለመቻሉን ሪፖርቱ ያስረዳል።
በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ቁልቁል የፍጢኝ ታስረው የውስጥ እግራቸው እንደሚገረፍ፣ በውሃ ውስጥ እየገቡ እንዲሰቃዩ እንደሚደረግ፣ በእስር ቤት ውስጥ ድብደባ መፈጸምና ለህይወት አስጊ በሆነ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ መቅጣት በኢትዮጵያ የተለመደ ነው ብሎአል።
ከልካይ የሌለበት የሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያም ዜጎችን እንደፈለገ እንደሚገድልና እንደሚያስር፣ በክልሎች ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ልዩ ሚሊሺያዎችም እንዲሁ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጉዳይ አስፈጻሚዎች መሆናቸውን አትቷል።
ከሁለት አመት በፊት ባለው አሃዝ በ6የፌደራልና በ120 የክልል እስር ቤቶች ከ70 እስከ 80 ሺ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ወንጀሎች መታሰራቸውን የገለጸው ሪፖርት፣ በይፋ የማይታወቁ በጦር ካምፖች ውስጥ ያሉ እስር ቤቶችንም ዘርዝሯል። ደዴሳ፣ ብር ሸለቆ፣ ጦላይ፣ ሆርማት፣ ብላቴ፣ ታጠቅ፣ ጅጅጋ፣ ሆለታና ሰንቀሌ ስውር እስር ቤቶች ተብለው ተጠቅሰዋል።
የኢድ አል ፈጥር በአልን ለማክበር በስታዲየም ላይ ተገኝተው በነበሩ ሙስሊሞች ላይ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከታሰሩት ወደ 1 ሺ ከሚጠጉት ሰዎች መካከል የተወሰኑት በእስር ቤት ውስጥ መሞታቸውንም ሪፖርቱ ጠቅሷል።
የሙስሊም ጉዳዮች መጽሄት አዘጋጅ ሰለሞን ከበደ በእስር ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈጸመበት የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ በ አንዱአለም አራጌ፣ ኦባና ሊሌሳ፣ በቀለ ገርባና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ላይ እየደረሱ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲሁም በሴቶችና ህጻናት ላይ ስለሚደርሱ የመብት ጥሰቶች፣ በአናሳ ጎሳ አባላት ላይ ስለሚደረሰው መፈናቀልና ግጭት በዝርዝር አስቀምጣል።
የአሜሪካ ምክር ቤት የኢትየጵያ መንግስት የሰብአዊ መብቶች አያያዙን እስከሚያከብር ድረስ የ2014 እርዳታ እንዳይሰጥ ህግ ማውጣቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ደረስ በዚህ ህግ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

Monday, February 24, 2014

GOLD, CORRUPTION AND HUMAN RIGHTS




በዓመት 3500 ኪሎ ወርቅና እና 4500 ኪሎ ብር (silver) ከኢትዮጵያ እንደሚረከብ በስዊዝ Argor Heraus Refinery የተባለው የወርቅ ማጣሪያ ኩባንያ አስታወቀ። የወርቁ ባለቤት ሼክ መሃመድ አላሙዲ፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፍያ ሳላ አለሙዲ እና የኢትዮጵያ መንግስት መሆናቸውን በድህረ ገፁ አሳውቋል። Argor-Heraeus Refinery የተባለው የስዊዝ ኩባንያ በኮንጎ ጦርነት ወከባ የተዘረፈ ህገ ወጥ ወርቅ በማከማቸቱ ክስ ላይ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት ለጌ ደምቢ የሚባለውን የወርቅ ማውጫ ገደል በ172 ሚሊዮን ዶላር ለሃያ አመታት ለሼክ መሃመድ መሸጡን ድህረ ገፁ ቢናገርም በኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ የተነገረው ነገር የለም። ከለጌ ደምቢ 6500 ኪሎ በዓመት ወደ ስዊዝ Argor Heraus Refinery የተባለው የወርቅ ማጣሪያ እንደሚያስረክብ ድህረ ገፁ ይናገራል።
በአጠቃላይ ሼክ መሃመድ እና የኢትዮጵያ መንግስት በአመት 10000 kg ወርቅ ወደ ስዊዘርላንድ ይልካሉ ማለት ነው።

Wednesday, February 19, 2014

የካቲት 12

በኢጣሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወኪል አገረ ገዢ የነበረው ማርሻል ሩዶልፎ ግራዚያኒ፣የኔፕልስ ልዕልት ልጅ መውለዷን ምክንያት በማድረግ በቤተመንግሥቱ ለድሆች ምጽዋት ለመስጠት ስለፈለገ የከተማው ድሆች እንዲሰበሰቡ አዝዞ፣ ሶስት ሺህ የሚሆኑ ምንዱባኖች በቅጥሩ ውሥጥ ተኮልኩለው ነበር፡፡ ለእያንዳንዱ ደሀም ሁለት የማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር፡፡

በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ራሱ ጀነራል ግራዚያኒ፣ የሜትሮፖሊታን ጳጳስ አቡነ ኪርል እንዲሁም ታላላቅ የኢጣሊያ ሹማምንት ተገኝተው ነበር፡፡

እኩለ ቀን ሲሆን ግራዚያኒ በቤተ መንግሥቱ መግቢያ ደረጃ ላይ ሆኖ ለተሰበሰበው ሕዝብ ዲስኩር ማሰማት እንደጀመረ በግቢው በር በኩል ሁለት ቦምቦች ተከታትለው ፈነዱ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የፈነዳው ቦምብ ግን ከፍተኛ የፋሺስት ኢጣሊያ ባለሥልጣናት ከተቀመጡበት መካከል አረፈ፡፡ በቀጣዮቹ ደቂቃዎች አራት ተጨማሪ ቦምቦች ተወርውረው ፈነዱ፡፡ማርሻል ግራዚያኒ ጀርባውን ቆስሎ ወደቀ፣ የኢጣሊያ አየር ኃይል አዛዥ የነበረው ጀነራል አውሬሊዮ ሊዮታ ቀኝ እግሩንና ቀኝ ዐይኑን አጣ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጉይዶ ኮርቲሲ እና ሌሎች ኢጣሊያውያን እንግዶች በፈንጂው ተጎዱ፡፡ ፍንዳታው ጋብ ሲል ከንቲባ ኮርቴሲ ከወደቀበት ተነስቶ የተሰበሰቡት ኢትዮጵያውያን ላይ በማነጣጠር የመጀመሪያውን ጥይት ተኮሰ፤ የፋሺስት ፖሊሶችም ምሣሌውን በመከተል ሶስት ቀን የሚቆየውንና መላውን ከተማውን ያዳረሰውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከዚያው ከቤተ መንግሥት ውሥጥ ጀመሩ፡፡
በደረሰበት የፈንጂ አደጋ ማርሻል ግራዚያኒ በ350 ፍንጣሪዎች ቆስሏል፡፡

የካቲት 12 ቀን ስለ ደረሰበት አደጋ ግራዚያኒ ለኢጣሊያ ቅኝ ግዛቶች ሚኒስትር ባስተላለፈው ቴሌግራም ‹‹ ዛሬ ጠዋት በ5 ሠዓት ግቢ ተገኝቼ ነበር፡፡
ታላላቅ መኳንንት፣ የኦርቶዶክስና የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች ሁሉ ተሰብስበው ነበር . . . 6 ሠዓት ሲሆን አሥር የብሬዳ የእጅ ቦምቦች ካልታወቁ ሠዎች ተጣሉብን፡፡
በዚህም ምክንያት ሠላሳ ሰዎች ቆሰሉ፡፡ በኔ መቁሰል ምክንያት አገሪቱን የተከበሩ ፔትሬቴ እና ጀነራል ጋሪባልዲ እንዲጠብቁ አድርጌአለሁ፡፡ ለአዲስ አበባ ከተማ ጸጥታም አላፊ አድርጌያቸዋለሁ›› ብሏል፡፡ ግራዚያኒ በሌላ ጊዜ ወደ ሮማ ባስተላለፈው ቴሌግራሙ የተደረገበትን የመግደል ሙከራ አስመልክቶ ሲጽፍ ‹‹የተጣለብኝ ቦምብ ቢያንስ 18 ይሆናል፡፡

አሳባቸው ባንድ ፈንጂ እኔን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም የመንግሥቱ ባለሥልጣኖች ጠራርጎ ለማጥፋት ነበር . . .
በተጣለብኝም ቦምብ 250 ፍንጥርጣሪ ብረቶች ከገላዬ ወጥተዋል፡፡ እነዚህንም ፍንጣሪዎች ለታላቅ መታሰቢያነት አስቀምጫቸዋለሁ›› ብሏል፡፡

Thursday, February 13, 2014


ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጽ/ቤታቸው ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ በቀረበላቸው ጥያቄ በመቆጣት ዘለፋ ሰነዘሩ፡፡

አቶ ታምራት ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት
ጥያቄ በአሁን ሰዓት አገሪትዋን የሚመራት ማንነው ነው የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩም





ብስጭታቸውን በምላሻቸው ወቅት
አንጸባርቀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ
ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ
ጋዜጠኛውን ሂድና እዚያ ሐሜት
የምትጽፍበት ገጽ ላይ ጻፈው በማለት
መዝለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን
አስደንግጦአል፡፡

አንዳንድ ጋዜጠኞች ስለሁኔታው
በሰጡት አስተያየት ጋዜጠኛ ታምራትን
በማድነቅ አንድ ጋዜጠኛ በሕዝብ
ውስጥ የሚነገርን ጥያቄ አውጥቶ
መጠየቁ ተገቢና ሙያዊ ሃላፊነቱ
መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚኒስትሩ
ጥያቄው የቱንም ያህል ቢያበሳጫቸው
በዚህ መልኩ ምላሽ መስጠታቸው
ራሳቸውን ከማስገመት ያለፈ ትርፍ
እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ወደስልጣን
የመጡት አቶ ኃይለማርያም ቀደም
ሲል በአቶ መለስ ብቻ ሲመራ
የነበረውን የጠ/ሚኒስትር ስልጣን
የጋራ አመራር በሚል ፈሊጥ ሶስት
ቦታዎች በመክፈልና በምክትል ጠ/
ሚኒስትር ማዕረግ ለኢህአዴግ አባል
ድርጅቶች ስልጣናቸው ማከፋፈላቸው
በሕዝብ ዘንድ ያለስልጣን የተቀመጡ
አሻንጉሊት መሪ እስከመባል
አድርሶአቸዋል፡፡

አራት የኦሮሞ ተወላጅዎች በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ተያዙ...

አራት የኦሮሞ ተወላጅዎች በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ተያዙ....

የምስራቅ አፍሪካ ሰብአዊ መብቶች ሊግ በላከው መግለጫ አራት የኦሮሞ ተወላጅዎች በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል የተያዙት በተለያዩ ቀናት ነው።
ቱምሳ ሮባ ካቲሶ የተያዘው ኢስሊ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ ሲሆን፣ በሁለት መኪኖች የመጡ የጸጥታ ሃይሎች በፈረንጆች አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 1፣ አፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ወስደውታል።
ጫላ አብደላ፣ ናሚ አብደላ፣ እንዲሁም ስሙ በውል ያልታወቀው ሶስተኛው ሰው ደግሞ ፌብሩዋሪ ሶስት በተመሳሳይ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኬንያ መንግስት በጻፈው ደብዳቤ፣ የኦሮሞ ተወላጅዎችን ወደ ኢትዮጵያ ሳይላኩ አይቀርም ብሎአል። የኬንያ መንግስትም በአለማቀፍ ህግ መሰረት የሰዎችን አድራሻ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ደህንነቶች በቅርቡ 2 የኦጋዴን መሪዎችን ኬንያ ውስጥ አፍነው መውሰዳቸው ይታወቃል። ጣራ ከመንካት ያለፈዉን የኦሮሞ ተወላጆችን ስቃይ ፤ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ የዉጪ ሚድያዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በየዕለቱ የሚከሰተዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አለመዘገብ እንዲሁም በዉጪ ሀገር የሚሠቃዩ የኦሮሞ ስደተኞችን የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች እንደ ኦሮሞነታቸዉ ባለመቀበሉ ችግሩን አብሶታል ፡፡ በዉጪ የሚገኙ የኦሮሞ ሚድያዎች ዜናዎቻቸዉ ጠቅላላዉን የኦሮሞ ገፈት ቀማሾችን ያለተኮረ መሁኑ ያሣዝናል ፡፡

Monday, February 3, 2014

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ (ዩኒቨርሲቲ ወይሰ የጦር ካመፕ???


በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየተከሰቱ እንደሆነ በአካባቢው የሚገኙ ያነጋገርናቸው ተማሪዎችና ነዋሪዎች አረጋግጠውልናል። ፌደራል ፓሊስና አድማ በታኝ ሁኔታውን ለማብረድ ሀይል ተጠቅሟል
በዛው ቀን ከሰዓት በኋላ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች ታምመው ወደ ህክምና ተቋማት እንደሄዱና፣ 10 የሚሆኑት የጸና ህመም እንዳጋጠማቸው ጠቅሷል፡፡

ከክስተቱ ጋር በተያያዘ በርካታ የፖሊስ አባላት በዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ውስጥ በብዛት እንደነበሩና የተጎዳ ተማሪ ግን እንደሌለ ተናግሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት በሚያካሂደው የተማሪዎች የስፖርት ውድድር ሳቢያ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ትኩረቱን ነፍጎናል፤ በመጸዳጃና በምግብ ቤት አካባቢ ችግር አለ ብሏል፡፡

ተማሪው፣ ከቀናት በፊት የዩኒቨርሲቲው የኢንጅነሪንግ ተማሪዎች ባነሱትና እስካሁንም ባልተመለሰው ጥያቄያቸው ሳቢያ ከፖሊስ ሀይሎች ጋር በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ ግን በርካታ ተማሪዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግሯል፡፡