በዚህ መንገድ በሚመራ ህብረተሰብ ውስጥ በዕውቀት (በችሎታ) ማነስ ወይም በተራ ስህተት ወይም በስንፍና ካልሆነ በስተቀር ሆን ተብሎ፣ ታስቦና ታቅዶ በተንኮል በሚፈጸም ቂም በቀል፣ ግፍና በደል አገርና ሕዝብ አይጎዱም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ መንገድ ቢመራ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት የመላቀቅ፣ በዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሥርዓት የመመራትና በነፃነት፣ በሠላምና በአንድነት የክብር ኑሮ የመኖር ተስፋው እየራቀ ሳይሆን እየቀረበና እየለመለመ ይመጣል። የሚያሳዝነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመራው በዚህ መንገድ ሳይሆን በኢህአዴግ መንገድ ነው። የኢህአዴግ መንገድ ደግሞ በአብዛኛው ከላይ ከተገለጸው መንገድ የተለየ ነው። በእኔ እምነት የኢህአዴግ መንገድ ቀናነት፣ ግልጽነትና ሀቀኝነት የሚጎድለው መንገድ ነው።
ከታሪካቸው እንደተረዳሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከልብ አማኝ ክርስቲያን ናቸው፣ ወደ ፊት ካልተለወጡ በስተቀር። በመሆናቸውም የጌታ ኢየሱስ አስተምህሮን የህይወታቸው መመሪያ አድርገው ይወስዳሉ ብዬ አምናለሁ። በከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህርና ዲን በነበሩበት ጊዜ የዕለት ተዕለት ሥራቸው ከዕውቀት፣ ከጥናትና ከምርምር እንዲሁም ከትምህርት አስተዳደር ጋር የተያያዘ ስለነበር የሥራ ህይወታቸውን ከሃይማኖታዊ መርሆቻቸውና እሴቶቻቸው ጋር አጣጥመው ለማስኬድ ብዙም አያስቸግራቸውም ነበር ብዬ እገምታለሁ። ከጊዜ በኋላ፣ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ ሲገቡና በመሥመሩ በደረጃ እያደጉ ሲመጡ ግን ችግር ሳይገጥማቸው አልቀረም ብዬ አስባለሁ።
ፖለቲካ በመሰረቱ ሳይንስም ኪነጥበብም ነው። በመሆኑም በትምህርት ዓለም እንደተፈላጊ የዕውቀት መስክ ተወስዶ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ እየሠለጠኑበት ነው። ሆኖም በጊዜ ሂደት ቅንነቱና ሀቀኝነቱ የጎደላቸው ፖለቲከኞች ፖለቲካን በሥራ ላይ ሲያውሉት አጠቃቀሙን ስላበላሹት ሕዝብ ስለፖለቲካ ያለው አመለካከት ቀና አይደለም። ከዚያም ባሻገር ፖለቲካ ማለት የመቅጠፍ፣ የማስመሰል፣ የመዋሸትና ቅንነት የጎደለው አካሄድ ነው እስከማለት ተደርሷል።
ፖለቲካን እንደ ሳይንስነቱና እንደ ኪነጥበብነቱ በሥራ ላይ ለማዋል ከፍተኛ ቅንነትና ሀቀኝነት (ፈረንጆች በጠቅላላው honesty and integrity የሚሉትን) ይጠይቃል። ቅንነቱና ሀቀኝነቱ ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደ ፖለቲካ ሙያ ባለመምጣታቸው ግን በአገራችን ፖለቲካ እንደሚባለው ሊሆን አልቻለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተናገሯቸው ውስጥ ሁለት ኣጫጭር ምሳሌዎችን በመውሰድ በኢህአዴግ መንገድና የጌታ ኢየሱስ መንገድ ባልኩት መካከል ያለውን ልዩነት እንደምሳሌ በትንሹ እንመልከት። የምንመለከታቸው ምሳሌዎች ትንንሽ ይሁኑ እንጂ የትልልቅ ችግሮች ምልክቶች ናቸው። አንደኛው ትንሽ ነገር ግን የትልቅ ነገር ምሳሌ ነው የምለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ የመጀመሪያ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሲያቀርቡ ከተናገሩት የተወሰደ ነው። አንድነት ፓርቲንና ልሣኑን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን ይመለከታል። እርሳቸው ወደ አሉት በቀጥታ ከመሄዳችን በፊት ግን ትንሽ ማብራሪያ ላስቀድም።
አንድነት ፓርቲ እንደማንኛውም ዜጋ ሆነ ድርጅት በሕገ መንግሥቱና በፓርቲዎች ምሥረታ ዓዋጅ የተሰጠው ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ለመጠቀም ፍኖተ ነፃነት የተባለ ጋዜጣ ጀመረ። ጋዜጣው የሚታተመው በብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ነበር። ጋዜጣው በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነቱ እያደገና የህትመት ቅጂውም እየጨመረ ሲመጣ ችግሮች መታየት ጀመሩ። ለምሳሌ መጀመሪያ ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ደርጅት በአታሚና በአሳታሚ መፈረም አለበት ያለውንና በሕገመንግሥቱ የተከለከለውን ቅድመ ሳንሱር በጓሮ በኩል የሚያስገባ አዲስ የሥራ ውል ሠነድ ድንገት ይዞ ብቅ አለ። አንድነት የሠነዱን ይዘት በሕግ ባለሙያ አስጠና። ጥናቱም የተወሰኑ የሰነዱ ቁልፍ አንቀጾች ሕጋዊ መሠረት የሌላቸው መሆናቸውን አመለከተ። ስለዚህ አንድነት ሠነዱን እንደማይፈርም አስታወቀ። በዚህ ጊዜ አታሚው ድርጅት በቀጥታ የውል ሠነዱ ካልተፈረመ ጋዜጣውን አላትምም ማለትን ትቶ ሌሎች ምክንያቶችን ማፈላለግ ጀመረ። ከጋዜጣው አዘጋጆች እንደተረዳሁት፣ አንዱ የተሰጠው ምክንያት “በርካታ ሰዎች በጋዜጣችሁ በምታወጧቸው ነገሮች ላይ ቅሬታ ያላቸው መሆኑን ስለገለጹልን” የሚል ነው። አታሚው ድርጅት ይህንኑን ምክንያት በጽሑፍ እንዲሰጥ በጽሑፍ ተጠይቆ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ነው የተረዳሁት። የብርሃንና ሠላም ምክንያት ምን ያህል አሳማኝ ነው? በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት (አለ እንበልና) ጋዜጣውን ያነበቡ ሰዎች ቅር ተሰኙ ተብሎ አላትምም ይባላል? ቅር የተሰኙ ሰዎችስ እነማን እነማን ናቸው? እዚህ ላይ ቅንነት፣ ግልጽነት፣ ሀቀኝነት፣ ነፃነትና ሌሎች ባህሪያት የሀገራችን ዜጎች፣ ድርጅቶችና ኃላፊዎቻቸው እንዲሁም ህብረተሰባችን በአጠቃላይ ዛሬም ቢሆን የሚመሩባቸው የተከበሩ እሴቶች ናቸው ከሚል እምነት በመነሳት አንዳንድ ጥያቄዎችን እናንሳ። ለምንድን ነው ብርሃንና ሠላም አሳታሚ ድርጅት በድንገት፣ የዜጎችና የድርጅቶች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ሕገመንግሥታዊ መብትን የሚጥሱ አንቀጾችን የያዘ የሥራ ውል እንዲህ ደፍሮ ያመጣው? ሠነዱ የያዘው ሀሳብ ምን ያህል የራሱ ነው? የበላይ ስውር እጅ አለበት? ድርጅቱ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን ለማተም ለምን ይህን ያህል ተቸገረ? ጋዜጣውን አላትምም ያለበትንስ ምክንያት በጽሑፍ ለመስጠት ያልፈለገው ለምንድን ነው? በእኔ እምነት ከዚህ ሁሉ በስተኋላ የአንድነት ጋዜጣ እንዳይታተም የሚያደርግ የኢህአዴግ እጅ አለበት። ይህ የተለመደ የኢህኣዴግ ፖለቲካዊ አካሄዱ ነው።
Wednesday, January 30, 2013
Tuesday, January 29, 2013
የወያኔው ቁንጮ ስበሀት ነጋ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንቅስቃሴ የደገፈ ሁሉ አሸባሪ ነው አሉ!!!
የወያኔው ቁንጮ ስበሀት ነጋ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንቅስቃሴ የደገፈ ሁሉ አሸባሪ ነው አሉ። እንዲሁም ፓትርያርክ አቡን መርቆርዮስንም ነቅፈዋል… እንደ ስበሀት ነጋ ከሆነ አደጋ አለ። የኢሳትን ልዮ ዜና ዘገባ ያዳምጡ።
Monday, January 28, 2013
የፖለቲካ እሥረኞች ይፈቱ’ የሚል ሠልፍ ዋሽንግተን ውስጥ በኦሮሞ ተወላጆች ተካሄደ
ከአቶ በቀለ ገርባ እና ከአቶ ኦልባና ሌሊሣ በተጨማሪ በስም የተጠቀሱት ወልቤካ ለሚ፣ አደም ቡሣ፣ ሃዋ ዋቆ፣ ሞሐመድ መሉ፣ ደረጀ ከተማ፣ አዲሱ ምክሬ እና ገልገሎ ጉፋ በእሥር ላይ እንደሚገኙ የሠልፉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡
ሰላማዊ ሠልፉን ያዘጋጁት የኦሮሞ ጥናት ማኅበር፣ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ድርጅት፣ የኦሮሞ ወጣቶች ራስ አገዝ ማኅበር፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግና የኦሮሞ ድጋፍ ቡድን ናቸው፡፡
ሠልፈኞቹ ባለስምንት ነጥብ ጥያቄአቸውን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በፅሁፍ ያስገቡ ሲሆን በአደባባዩ ላይም እነዚህን ጥያቄዎቻቸውን የያዘውን ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በስም የተፃፈውን ደብዳቤ የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ሞሲሣ አጋ ሙሉውን በንባብ አሰምተዋል፡፡
ስምንቱ ጥያቄዎቻቸው፡- የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ በቀለ ገርባን፣ አቶ ኦልባና ሌሊሣን፣ እንዲሁም ሌሎቹንም ሰባት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ በፖለቲካ ምክንያት ተይዘው የረዥም ዓመታት እሥራት የተፈረደባቸውን ሰዎች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ዩናይትድ ስቴትስ ብርቱ አቅም ያለውን የፖለቲካ፣ የምጣኔ ኃብትና የዲፕሎማሲ ጫናዋን እንድታሣድር፤
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መንግሥት የኢትዮጵያን ሕገመንግሥት እንዲያከብር፣ ከፍርድ ውጭ የሆኑ ግድያዎችንና ንፁሃን ሰዎችን ያለክሥ ለተራዘመ ጊዜ ማሠሩን እንዲያቆም የአሜሪካ መንግሥት ምክር እንዲሰጥ፤
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ድጋፍ ከመስጠቷ በፊት የፖለቲካ እሥረኞች ሁሉ እንዲፈቱ አስገዳጅ ጫና እንድታደርግ፤
የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞን ሕዝብና የሌሎቹንም ሰብዓዊ መብቶች፣ ሃሣብን የመግለፅና የመደራጀት ነፃነቶችን እንዲያከብር አሜሪካ እንድትጠይቅ፤
የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረታዊ የሆኑ የዜጎችን መብቶች የሚጥሱ አዳዲስ ሕግጋትን ሁሉ፣ በተለይ ፀረ-ሽብር የሚባለውን ሕጉን፣ የፕሬስ ሕጉን፣ የረድዔት ድርጅቶች በሃገሪቱ ውስጥ እንደልባቸው እንዳይንቀሣቀሱ የሚገድበውን የሲቪል ማኅበራት ማቋቋሚያ ሕጉን፣ እንዲሁም ስካይፕንና ሌሎችም የሚድያ አገልግሎት ዘዴዎችን መጠቀምን ሕገወጥ የሚያደርገውን በቅርብ ያወጣውን ሕጉን እንዲሠርዝ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እንዲጠይቅ፤የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገወጥ የሆነው የኦሮሞ ልጆችን ከይዞታዎቻቸው ማፈናቀልና መሬቶቻቸውን መሸጥ በአፋጣኝ እንዲያቆም አሜሪካ እንድትጠይቅ፤
መንግሥቱ የሃይማኖት ነፃነትን እንዲያከብር እና በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ውስጥም ጣልቃ መግባት እንዲያቆም የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እንዲጠይቅ የሚሉ ናቸው፡፡
በሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ላይ እሥራቱ በተካሄደ ጊዜ አቶ ኦልባና ሌሊሣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ቢሮ ላፊ፣ አቶ በቀለ ገርባ ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበርና የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡
አቶ ኦልባና ሌሊሣና አቶ በቀለ ገርባ የተያዙት ‘እኛ ካነጋገርናቸው በኋላ ነው’ ሲሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ አጥኚና መርማሪ የነበሩት ክሌር ቤስተን እነ አቶ ኦልባና በታሠሩ በአምስተኛው ቀን ለቪኦኤ ተናግረው ነበር፡፡
Source Voa Amharic

ያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ ፍቃድ ተሰጥቷቸው ሥራ ላይ የነበሩት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰዎች ባልተገለፀላቸው ምክንያት በአፋጣኝ ሃገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ መታዘዛቸውንና መውጣታቸውን ክሌር ቤስተን ተናግረው ነበር፡፡
በወቅቱ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ብዙ ሰዎች መታሠራቸውን የኢትዮጵያ መንግሥትም አልሸሸገም፡፡ የታሠሩት ግን ‘በሕገወጥ ወይም በሽብር ተግባራ ላይ በመገኘታቸው ነው’ ነው የሚለው፡፡ ያኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ ከነ አቶ ኦልባና መያዝ ጥቂት ቀደም ብሎ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር ይህንኑ አጠንክረው ተናግረዋል፡፡
የእነአቶ ኦልባና እሥራት እንደተፈፀመ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሺመልስ ከማል በሰጡት መግለጫ አንደኛው የታሠሩት በሽብር ፈጠራ ምከንያት ከታገደው ኦነግ ጋር አላቸው በተባለ ግንኙነት መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡ ኅዳር 2005 ውስጥ ተከሣሾቹ እነ አቶ ኦልባና ሌሊሣ እና በቀለ ገርባ የረዥም ዓመታት እሥራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል:::

ዓርብ፣ ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተካሄደውን ዓይነት ተመሣሣይ ሠልፍ ለንደንም ላይ መካሄዱን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል፡
Source Voa Amharic
Wednesday, January 16, 2013
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ፀሀፊ በድህነት ኃይሎች ጉዳት ደረሰብኝ አለች

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የጉለሌ ክ/ከ ፀሀፊ የሆነችው ወጣት ወይንሸት ስለሺ የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡30 ሲሆን አፍንጮ በር አካባቢ ከሚገኘው የማህበሩ ፅ/ቤት ለመድረስ 50 ሜትር ሲቀራት በደህንነት ሀይሎች ተይዛ አንድ ሌሊት ሙሉ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት አንደደረሰባት ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቀች፡፡
በማህበሩ ፅ/ቤት ዘወትር ማክሰኞ የሚደረገውን የመማማሪያ ፕሮግራም ለመሳተፍ እየሄደች ሳለ በፅ/ቤታቸው አቅራቢ መንገድ ዳር ጠብቀው አንገቷ ስር መርፌ ከወጎት በኃላ እራሷን ስትስት መኪና ውስጥ በማስገባት አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው አንድ ስውር ቪላ ቤት ግቢ ውስጥ በማስገባት ከብርሀኑ ነጋ ጋር ግንኙነት አላችሁ ከውጭ ሀገር የሚደግፋችሁ ማን ነው የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው በሰጠችው ምላሽ ባለመደሰታቸው በጥፊ መመታቶን ገልፃ ለጠየቆት ጥያቄ እውነቱን አውጪ በማለት ግራ እግሯን በመጋረጃ ብረት በመምታት ጉዳት ያደረሱባት ሲሆን በኤሌክትሪክ ንዝረትም ጀርባዋ ላይ የከፋ ጉዳት እንደደረሰባት ገልፃ የህክምና ውጤቷን በመጠባበቅ ላይ መሆኗን ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቃለች፡፡
ለስራ የምትጠቀምባቸውን ሁለት ቴፕ ሪከርደሮች (ዲጂታልና አናሎግ) የቤተሰብ ሁለት ሺ አንድ መቶ ሃምሳ ሰባት ብር እና ሞባይል ስልክዋንም እንደወሰዱባት አስታውቃለች፡፡
ወይንሸት ስለሺ እባላለው የጉለሌ ክ/ከ የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ፀሀፊ ነኝ ፡፡በግሌ የደረሰብኝ ማክሰኞ ታህሳስ 30 ቀን 2005 ዓ/ም ማታ ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት ላይ ዘወትር በማህበሩ እምናደርገው የውይይት ጊዜ አለን፡፡በዚህ ውይይት ላይ ለመገኘት ሽሮ ሜዳ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቴ ወደ አፍንጮ በር የሚገኘው የማህበራችን በር ለመድረስ 50 ሜትር ሲቀረኝ ከለሩን ያላየሁት መኪና ሁለት ሰዎች ይዞ አጠገቤ ቆመ፡፡መንገዱ በጣም ጠባብ ስለነበር ወደ ዳር ወጥቼ ላሳልፈው ዘወር ስል አንገቴ ስር መርፌ ወጉኝ እና እራሴን አስተውኝ በመመኪና ውስጥ ጎትተው እስከሚያስገቡኝ ጊዜ ድረስ ብቻ ነውየማውቀው፡፡
ከዛ በኃላ ይዘውኝ ሲሄዱ እራሴን አላውቅም ነበር፡፤ቃሊቲ አካባቢ ጉራንጉር ውስጥ ስንደርስ መኪናው ቆመ እራሴን ያወኩት ከአመራሮቼ ጋር ስልክ ሲደዋወሉ ነበር፡፡እነሱን በጣም አስደንግጠው ሲረበሹ ከቆዩ በኃላ ነው እኔ የነቃሁት፡፡ ስነቃ አንደኛው ሰው እሺ ባለራዕይ ነቃሽ አለኝ፡፡ እሺ ምን ፈልጋችሁ ነው አልኩት፡፡በወቅቱ የወጉኝ መርፌ ማጅራቴንና ጭንቅላቴን ይዞኝ ስለነበር አይኑን በደንብ ገልጬ ማየት አልቻልኩም፡፡ራሴን ከብዶኝ ነበር የሆነ የተቀዳ ድምፅ አሰሙኝ፡፡ ሀብታሙ ስለ ባለዕራዩ ነው የሚያወራው ከዛ የማላውቀው ድምፅ አሰሙ ይህ ድምፅ የብርሀኑ ነጋ ድምፅ ነው፡፡ከሱ ጋር ንግግር ያደረጉት ድምፅ ነው ተቀርፆ የመጣ ነው፡፡ስለዚህ ከግንቦት 7 ጋር ህብረት አላችሁ፤ ስለዚህ ይህን መረጃ ይዘናል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ የማህበሩ አባላት የእነ ብርሀኑ፣ የሀብታሙ እና ሌሎች አመራሮችን ድንገት ቆመው የተነሱ የሚመስል ፎቶ አውጥተው እሱም የአባልነት ፎቶአቸው መሆኑን ከዛ ያስመጣነው ነው ስለዚህ ያላችሁን ህብረት ተናገሪ አለኝ፡፡
እኛ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ቡድን አይደለም አምነንበትም አልመንበትም ምንም አይነት ህብረት የለንም፡፡ ሀብታሙ ከብርሀኑ ጋር ተደዋውሎ የሚነጋገርበት ጊዜም የለውም የማውቀው ይህንን ነው፡፡ማህበራችነም የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም፡፡ሲቪክ ማህበር ነው የሚል ነገር ነው ያስቀመጥኩላቸው፡፡ እና ይሄ የእናንተ ፈጠራ ነው ስለው በጥፊ መታኝ ሁለት ናቸው፡፡ከመኪናው የኃላ ወንበር ላይ ዳር እና ዳር ሆነው መሃል አስቀምጠውኝ ነው የሚያወሩኝ፡፡ሹፌሩ ዞሮም አያየኝም ምንም አይናገርም ፀጥ ብሎ ነው የተቀመጠው ሁለቱ ናቸው የሚያጣድፉኝ፡፡መልካቸውን በደንብ አይቻቸዋለው የትም ቦታ ላይ ባያቸው አውቃቸዋለው፡፡እና በጥፊ እየመቱ አውጪ አሉኝ ምንም አይነት ነገር የለኝም አልኳቸው እኔ የማህበሩን በራሪ ወረቀት አዘጋጅ ስለነበር ጋዜጠኞች የሚጠቀሙበትን ሁለት መቅረፀ ድምፅ ይዣለው፡፡እነርሱም ይህቺን ዲጂታል መቅረፀ ድምፅ ይዛችሁ በየቢሮው እየሰለላችሁ የምትሰሩት ስራ በዚህ ማረጋገጫ አግኝተናል አሉ፡፡ ሁለተኛ ነገር ደግሞ ሁለት ሺ ንድ መቶ ሃምሳ ሰባት የቤተሰብ ብር ይዤ ነበር፡፡ይህን ብር ከሽሮ ሜዳ ሃያሁለት አካባቢ ሄጄ ብሩን ለማድረስ ነበር የያዝኩት፡፡ይህን ብር ወስደው ከውጭ ሀገር የሚላክላችሁ በር ነው እናንተ ያለውጭ ሃገር ድጋፍ ምንም ላይ እንደማትደርሱ እናውቃለን፡፡ስለዚህ ይህ ለእኛ ማስረጃችን ነው ብለው ብሬን ስልኬን እና ሁለት ቴፕ ሪከርዴን ከወሰዱ በኃላ አሁንም አታወጪም እውነቱን ሲለኝ ያለው ነገር ይሄ ስለሆነ ምንም ነገር ልነግርህ አልችልም አልኩት፡፡
በጥፊ ደገመኝና ሹፌሩን ንዳው አለው እና ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባ ቦታው በጣም ጨለማ ስለሆነ ዳርና ዳር ያለውን ነገር መለየት አልቻልኩም፡፡ሁለተኛ የደረሰበት አካባቢ ቪላ ቤት ነው ትልቅ ግቢ ነው የውጪው በር ሎሚ ከለር የተቀባ ነው ይህንንም ያየሁት የመኪናውን መብራት ሲያበራው ነው፡፡ ከእኔ በስተግራ በኩል ተቀምጦ የነበረው ወርዶ በሩን ከፈተለትና መኪናው ሲገባ ቤቶች አሉ አንድም ቤት ግን መብራት የበራ የለም ጨለማ ነው፡፡ አንገቴን በእጁ መዳፍ አጥብቆ ይዞ የመኪናው መብራት ጠፍቶ ጨለማ ሆኗል፡፡
እያንደረደረ አንዱ ክፍል ውስጥ አስገቡኝ፡፡በዛ ሰዓት የተሰማኝ ስሜት ሴት መሆኔ በሴትነቴ ተጠቅመው ብዙ ነገር ሊያደርጉኝ ነው የሚል ስጋትም ነበረኝ፡፡ፈራው ግን የፈለገ ነገር ቢመጣ ደግሞ የያዝኩት ዓላማ የወጣቶችን ስብዕና የያዘ መሆኑ በውሸትም ምንም ነገር ማለት አልፈለኩም፡፡
ስለዚህ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉኝ ያለው ነገር ግን ይሄው ነው አልኳቸው፡፡እና ውስጦ ክፍት በሆነችው የመጋረጃ ብረት አንዱ እሱን ይዟል አንደኛው ኤሌክትሪክ ገመድ ይዟል፡፡ቀጥታ በመጋረጃው ብረት ግራ እግሬ ላይ በደንብ አድርጎ ሲመታኝ ተንበረከኩ፡፡
አሁንስ እውነቱን አታወጪም አለኝ የፈለከውን አድርገኝ እኛ ከምንም ጋር ምንም አይነት ህብረት የለንም፡፡ የማውቀው የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሲቪክ ማህበር እንደሆነ ነው ከዛ የዘለለ ምንም ዓይነት ህብረት አላውቅም አልኩት:: የለበስኩትን ጃኬት አስወለቁኝ እና ቤቱ ሶስት በአራት ያክላል ፣ግድግዳው ሶኬት ብቻ ነው፤መቀመጫ የለውም፡፡ ወለሉ እምነበረድ ነው ግድግዳው ሲሚንቶ ነው በጣም ነው የሚቀዘቅዘው የቤቱ መብራት ማብሪያና ማጥፊያ ከውጪ በኩል ነው ያለው፡፡እና ሶኬት ሰክተው ጀርባዬ ላይ አነዘሩኝ፤ሾከድ አደረጉኝ ፤እየጎተቱ በያዘው ኤሌክትሪክ ሾከድ ያደርገኛል፡፡
በቃ ግደሉኝ አልኳቸው ማረድ ጀምረንሽ ቢሮዋቹ በር ላይ አርደን እንጥልሻለን ከዛ እነሱ ሌሎች አመራሮች ይማሩበታል፡፡እኔን ብትገድሉኝ የእኔ አላማ የሚከተል ብዙ ሺኅ ወጣት አለ፡፡እኔ ግን እዚህ ብዋሽ ብዙ ወጣት ነው ገደል የምከተው ስለዚህ የፈለከውን አድርገኝ አልኩት፡፡እስከ ሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ማለት ነው አመራሮች እኔ ስልክ ላይ ሲደውሉ እያነሱ ሲያሾቡባቸው ነበር፡፡ እስከ 7፡00 ሰዓት ሲያሰቃዩኝ ነበር፡፡እንድቆስል እንድደማ ምንም አላደረጉም ምንም የሚታይ ነገር አላደረጉብኝም፡፡
ግን ኤሌክትሪኩ ያደረሰብኝ ነገር አለ፡፡እግሬ ላይ የመቱኝ አብጧል፡፡አንገቴ ላይ የወጉኝ መርፌ እብጠት ይደማ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ካደረጉ በኃላ ሰባት ሰዓት ላይ ከውጭ ቆልፈውብኝ ሄዱ፡፡
ሲሄዱም የሆነ ሀይል ጨምረው እነደሚመጡ አስቤ ጥግ ይዤ ቁጭ ብዬ ጠበኳቸው፤ በዛ ሰዓት በኤሌክትሪክ ሾከድ ያደረጉኝ ፣መርፌ የወጉኝ ፣እግሬ ላይ የመቱኝ ነገር ከቅዝቃዜው ጋር ሲያመኝ አደረ፡፡
ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ተመልሰው መጡና ለምን አንቺ እውነቱን ነግረሽ አትሄጂም ዱላ ከሚበዛብሽ አሉኝ፡፡ከዚህ በላይ ምንም ልላችሁ አልችልም አልኩ፡፡ ደረቅ ነሽ አለኝ፡፡እኔ የምደርቀው ለእውነት ነው ስላቸው በመለስኩላቸው ቁጥር ያው የተለመደ ምት አለ፡፡በእርግጫም ይሁን ብቻ ደስ ሲላቸው ምት አለ፡፡ግን ጠዋት ላይ ማውራትም አልቻልኩም፡፡ 12፡30 ሲሆን ይዘውኝ ሲወጡ የመኪናውን ታርጋ ማየት እችላለው የሚል ግምት ነበረኝ፡፡
ካልገደሉኝ በስተቀር በቃሌ እይዘዋለው ብዬ ነበር ይዘውኝ ሲወጡ ግን፣ በመዳፉ ዓይኔንና ማጅራቴን ይዞ እያንደረደረ ወደ መኪና አስገባኝ፡፡የመኪናውን ውስጡን እንጂ ውጭውን አላየሁትም፡፡ሰዓቱንም ያየሁት መኪና ውስጥ ከተቀመጥኩበት ፊት ለፊት ሰዓት አለው መኪናውን አዙረው ከጉራንጉር ውስጥ ወጥተን ወደ ዋናው የቃሊቲ መንገድ ወጥተን ቃሊቲ መናህሪያ አካባቢ ስንደርስ ትልልቅ ኮንቴነር ጭነው የቆሙ መኪኖች አካባቢ ላይ መኪናውን አስጠግተው አቆሙና በኤኔትሬው መኪና ጀርባ ወስደው ራቅ አድርገው የሆነ ድንጋይ ላይ አስቀመጡኝና ቢፈልጉ መጥተው ይውሰዱሽ አሉኝ፡፡
የወሰዱብኝን ሁሉ ሳይመልሱልኝ አስቀመጡኝ፡፡የሚገርመው ይህን ያህል ብር እሷ እጅ መገኘቱ እሷ ማን ስለሆነች ነው ብለው ለአመራሮቼ በራሴ ስልክ መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል፡፡ያለምንም ነገር ባዶዬን እዛ ድንጋይ ላይ አስቀመጡኝ፡፡መኪናውን ፊት ለፊት ቢያቆሙት እንኳን እኔ ተነስቼ ታርጋ የማየት አቅም አልነበረኝም፡፡በወቅቱ አስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ከዛ ቦታ ላይ አልተንቀሳቀስኩም፡፡መቆም አልችልም ነበር፡፡መንገደኞች እየመጡ ምን ሆነሽ ነው ሲሉኝ ምንም አልሆንኩም ነበር የምላቸው ማውራትም አልችልም ነበር ማለት ነው የሁሉንም አመራር ስልክ በቃሌ ነው የያዝኩት ግን በዛን ወቅት የሁሉንም ስልክ ጠፋኝ ማስታወስ አልቻልኩም፡፡
በኃላ ላይ ግን የባልደረባዬን የብርሀኑን ስልክ ነው ያስታወስኩት፡፡ትንሽ ሜትር ሄጄ እየተቀመጥኩ እየተንፎቀኩ ሱቅ ላይ ደረስኩኝ ወጋገን ባንክ ፊት ለፊት ያለችው ሱቅ ላ ደውዬ ወይንሸት ነኝ ስለው አየፈለጉኝ ስለነበር የት ነሽ አለኝ ያለሁበትንም ስለማላውቀው ለባለሱቁ ስልኩን ሰጥቼው ምልክቱን በሚገባ ነግሮት ባለሱቁ በሰጠኝ ወንበር ቁጭ አልኩ ወደ 7፡00 ሰዓት አካባቢ ደረሱልኝና ይዘውኝ ወደ ፒያሳ አካባቢ መጡ፡፡አመራሮች ጠቅላላ ሲጠብቁ ስለነበር የተፈጠረውን ነገር ለመናገር አልቻልኩም፡፡የተወሰነች ነገር ነገርኮቸው፡፡ህክምና መሄድ አለብኝ ከዛ በፊት ግን ለፖሊስ ማሳወቅ አለብሽ የሚል አቅጣጫ ከአመራሩ የተቀመጠው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ፖሊስ ጣቢያ የገባው አስከ ምሽቱ 1፡30 ድረስ አቆይተውኛል፡፡
እያንዳንዱ መርማሪ ሙሉ ታሪኬን ይቀበሊና እኔን አይመለከተኝም እሱ ጋር ሂጂ ይለኛል፡፡ሌላውማ ሙሉ ታሪኬን ተቀብሎ እኔን አይመለከትም እሱ ጋር ሂጂ ይለኛል፡፡መጨረሻ ላይ ግን ማውራት አቅም አነሰኝ አልታከማኩማ ምግብ አልበላሁም ስለዚህ ከዚህ በላይ ማውራት አልችልም የሚል ነገር ነው ያሰቀመጥኩላቸው፡፡ወይም አንቀበልም ብላችሁ ሸኙኝ አልኳቸው፡፡ለጃል ሜዳ ፖሊስ ጣቢ መጨረሻ ላይ ግን የመርማሪዎቹ አዛዥ እሱ ቃሌን ከተቀበለ በኃላ ማረጋገጥ ያለበትን ካረጋገጠ በኃላ ቃል ተቀብሎኝ ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ ቃል መስጠቱን ጨርሼ ወጣው ፤ህክምና መሄድ እንዳለብኝና የህክምና ውጤት እንዳመጣ ተነገረኝ፡፡ከወጣው በኋላ የካቲት 12 ሆስፒታል እንድሄድ ቢነገረኝም ሆስፒታሉ በዛ ሰዓት ያለ ፖሊስ ማዘዣ ድንገተኛ ብዬ መግባት እንደማልችል አውቃለው፡፡ስለዚህ አመራሮች ያደረጉት ምግብ እንድበላ ነው ያደረጉት፡፡እኔ ግን 22 አካባቢ ወዳለው የእህቴ ቤት ነው የገባሁት ፡፡እቤት ገብቼ ማታ በጣም ስለታመምኩ ህክምና አገኘው ማሰታገሻ መርፌ ተወጋውና ጠዋት የካቲት 12 ሆስፒታል ሄድኩ፡፡አንገቴ ላይ የተወጋሁትን ምርመራ አደረኩኝ፡፡እግሬ ላይ ተመትቼ ያበጠውን አዩ፡፡በኤሌክትሪክ ሾክድ የተደረኩትን ጀርባዬን ዶክተር ካየ በኃላ ያለውን ነገር መዝግበው ውጤት ሰኞ ጠዋት እንደሚሰጠን እየጠበቅን ነው፡፡ከዛ በኋላ ፖሊስ ጣቢያ እንድመጣ ጠይቀውኝ ነበር፡፡ተመልሰሽ ነይ ብለውኝ ነበር፡፡ውጤት ሳልይዝ የምርመራ ውጤት መጠየቂያ የማልይዝ ከሆነ ምን አስኬደኝ በሚልና ስላመመኝ ወደ ቤት ሄድኩ፡፡ይህው ነው፡፡በመንግስት ሀገር በመሀል ከተማ አፈና ይካሄድብናል፤ አሁን ለማን ይሆን አቤት የሚባለው?

ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ
Saturday, January 12, 2013
ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ከጌታ መንገድና ከኢህአዴግ መንገድ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨረቃን ከሰማይ አውርዱልን እያለ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ ያለው ግልጽነትን፣ ቀጥተኝነትን፣ ቅንነትንና ሀቀኝነትን አውርዱልን ነው። ዴሞክራሲን አውርዱልን ነው። ቁሳዊ ልማት ብቻውን አይበቃም፣ ሰብአዊና መንፈሳዊ ልማትንም አውርዱልን ነው።
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ
የጌታ ኢየሱስ መንገድ ስል የክርስትና ሃይማኖት ዕምነት ቀኖናውን (ዶግማውን) ሳይሆን ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ሲያስተምር ያሳየውን የቀናነት፣ የሃቀኝነት፣ የግልጽነት፣ የፍትሓዊነት፣ የእኩልነት፣ የአንድነት፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲያዊነት፣ የመተሳሰብ፣ የመፈቃቀር፣የመከባበር፣ የመተማመን... መንገድ ማለቴ ነው። ይህ መንገድ የክርስትና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የእስልምና እንዲሁም የሌሎች የዓለም ታላላቅ ሃይማኖቶች መንገድ ነው።

Tuesday, January 8, 2013
የርዕዮት ዓለሙ ይግባኝ ውድቅ መደረጉን ዓለምአቀፍ ድርጅቶች አወገዙ
ርዕዮት ዓለሙ የዓለምአቀፉ የሴቶች ሚድያ ድርጅት የ2012 ዓ.ም በጋዜጠኝነት ላሣየችው ድፍረትተሸላሚ እና የዚሁ የ2012 ዓ.ም የሄልማን/ሃሜት ሽልማቶች ተሸላሚ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ
<<<>>> http://amharic.voanews.com/flashaudio.html በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማፅናቱ ያሣዘናቸው መሆኑን ዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት - IWMF እና ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት - ሲፒጄ አስታውቀዋል፡፡IWMF መግለጫውን በይፋ አውጥቶ ያሠራጨ ሲሆን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኤሊሣ ሊዝ ሙኞዝ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ጉዳይ ድርጅታቸውን በእጅጉ የሚያሠጋው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ርዕዮት ለጋዜጠኝነት ነፃነት ያላትን ድፍረት፣ ቁርጠኝነትና ጥንካሬ እናደንቃለን፡፡ ቀደም ፀሰል የተላለፈባት ፍርድ በመፅናቱ ማዘናችንን እንገልፃለን፡፡ ይህ ለእርሷ ሕይወት ብቻ ሣይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሣብን በነፃነት ለመግለፅ ነፃነትም ጭምር አሣዛኝ ቀን ነው፡፡ ለሌሎች በእሥር ላይ ለሚገኙ ጋዜጠኞችም የሚሰማንን መቆርቆር እንገልፃለን” ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡
ዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ባወጣው ይፋ መግለጫው ኢትዮጵያ ውስጥ እሥር ቤት ውስጥ ባሉ ጋዜጠኞች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ፣ በፕሬስ ነፃነት አያያዟ በዓለም እጅግ ጨቋኝ ከሚባሉ ሃገሮች ተርታ መመደቧን አስታውሶ ባለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመን በአፍሪካ ውስጥ ከኤርትራ በስተቀር ሌላ ማንም ሃገር በማይስተካከለው ሁኔታ ጋዜጠኞችን ማሠሩን አመልክቷል፡
የሚወቅሱትን ድምፆች ለማፈን በአደናጋሪው የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕግ መንግሥቱ በተደጋጋሚ መጠቀሙ እጅግ አሣሣቢ ነው” ያለው ይኸው መግለጫ ርዕዮት በሰኔ 2003 ዓ.ም (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ከተያዘች ወዲህ ለብዙ ወራት ያለ ክሥ መታሠሯን እና በኋላም ተግባሯ ሙሉ በሙሉ የጋዜጠኛ ሥራ ሆኖ ሣለ በሽብር ፈጠራ መከሰሷን ዘርዝሯል፡“ባለፈው ነሐሴ በከፊል በተሣካው ይግባኝ በርዕዮት ላይ ቀድሞ የተላለፈው የ14 ዓመት እሥራት ፍርድ ወደ አምስት ዓመት እንዲቀንስ ቢደረግም እስከአሁን የቆየችባቸው 19 ወራት እያንዳንዷ ቀን ወይም ወደፊት በእሥር የምትቆይባቸው 41 ወራት እያንዳንዷ ቀን የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሬስ ነፃነትን ዋጋ እንዳረዳ የምትጎተጉት ማስተወሻ ነች” ብሏል መግለጫውበሌላ በኩል ደግሞ ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ውሣኔውን እንደሚቃወምና እንደሚያወግዝ የአፍሪካ የአድቮኬሲ አስተባባሪ መሐመድ ኬይታ አስታውቋል፡
Friday, January 4, 2013
በሀረር ከተማ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፖሊሶች አንድ ህፃን ልጅ ገደሉ
በሀረር ከተማ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ በተፈጠረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ፖሊሶች አንድ ህፃን ልጅ ገደሉ!!!
Subscribe to:
Posts (Atom)