Friday, August 2, 2013

የኦሮሞ ተወላጆች ዋሽንግተን ላይ ተሰለፉ

የኦሮሞ ተወላጆች ዋሽንግተን ላይ ተሰለፉ

ከዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የኦሮሞ ተወላጆች ዛሬ በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥትና በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰልፎችን አካሄደዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ያሰሙት ሰልፈኞች ከመልዕክቶቻቸው መካከል

“በምሥራቅ ሐረርጌ እየደረሰ ያለው ግፍ ይቁም፤

በኦሮሞ ምሁራንና ተማሪዎች ላየ እየበረታ ያለው የመብት ረገጣ ይቁም፤ በኦሮሞ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለው ከመሬት የማፈናቀል ሥራ ይቁም” የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡
ሰልፉ የተዘጋጀው በኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር መሆኑ ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment