Monday, October 24, 2016

የሕወሃት ወታደራዊ አገዛዝ !



የሕወሃት ወታደራዊ አገዛዝ የተጨማለቀ የሕግ ስርዓት :

የሕወሃት አገዛዝ አንዱ ባህሪዉና መለያው ዜጎችን ማሰቃየት ነው። ማሰር እንጂ መፍታት፣ መጣል እንጂ ማንሳት፣ መግደል እንጂ ማዳን፣ ማዋረድ እንጂ ማክበር፣ መስበር እንጂ መጠግን ፣ መከፋፈል እንጅ አንድ ማድርግ አያወቁበትም። እንደ እንስሳት ጉዳዮችና ልዩነቶችን በሃይልና በጡንቻ መፍታት እንጅ እንደ ሰለጠነ ሰው በሰለጠነ መንገድ መፍታት አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ብቃቱ የለዉም።

ለስሙ ፍርድ ቤት፣ ዳኛ፣ ሕግ ፣ ሕገ መንግስት እያሉ ህወሃቶች ጠዋትና ማታ ያሰለቹናል። ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ታሪክ እንደነርሱ ሕግን መቀለጃና ማሾፊያ ያደረገ አገዛዝ የለም :የወያኔ የጅምላ እስራትና ግድያውን ቢያስፋፋም ሕዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

አሀኡነማ ሰው መግደለ ማሰረ መሰ ቃ የት ሕጋአው አደረጉተ ዱ ርአ ውነሰ ሀገአረዋት
ግን ግ ዜ ው ደረሰዋል: ወያኔ ዝቅ ብሎ የሚለምንበት !!

 

Tuesday, October 11, 2016

በህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ያሸነፈ የለም





የስርዓቱ መውደቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ከዚህ በኋላ የትኛውም ጥገና አያተርፈውም። በገንዘብ የሚፈወስ አይደለም። ደምወዝ በመጨመር የሚተርፍ አይደለም። ዘግይቷል። ረፍዷል። ህወሀት መጠየቅ ያለበት መውጪያ መንገድ ብቻ ነው።




የወያኔ የጊዜአዊ አዋጅ ድንፋታና የሆዳም የካዲሬዎቹ ጫጫታ ሕዝባዊ ትግሉን አይበገረውም። እንዲያውም አስቆጥቶና እልክ አሰግበቶ የበለጠ ሕዝቡን ወደ ትግል ያስገባዋል እንጂ ! ስለሆነም ይህንን ጉግ ማንጉግ፡ ሞራልና ሕሊና የሌለው፡ ከፀረ ሀይማኖትና ከፀረ እግዚአብሔር አልፎ ፡ ፀረ-የሰው ልጅ የሆነውን የመህይም ጥርቃሞ ቲፒ ኤል ኤፍ TPLF (ወያኔ/ኢሕአደግ) የሚባለውን የማፊያ ቡድን ከመላ ኢትዮጵያ ለማጥፋት... በዘር፡ በሀይማኖት፡ በፖሌቲካና በኢኮኖሚ ሳንለያይ አንድ ሁነን ታግለን የድሉን ቀን እናቅርበው እላለሁ። የወቀቱ መፈክር "እየተደራጁ መታገል፡ እየታገሉ ነፃነት" መሆን አለበት !

ከዚህ በኋላእኛ ስንሰርቅና ስንከብር እናንተ ዝም ብ ለችሁ ተመለከቱ በቃ ዘ ር ፍ በቃ !!! የትግራይ ነፃ አውጪው የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት 11% አገሪቱን አሳድገናል ብለው ነገር ግን ሃቁ ከ20 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከኃይለ ሥላሴም፣ ከደርግም እጂግ በከፋ ቁጥር ተርቦ እነሱን ለማትረፍ ዓለም በሚረባረብበት ጊዜ እነሱ ከኢትዮጵያ ህዝብ ሌት ከቀን በመዝረፍ አገር ውስጥ ከገነቡት ትላልቅ ህንፃ፣ ቪላና የተለያዩ ድርጅቶች ውጪ በተለያዩ ዓለማት የውጪ ባንኮች ያስቀመጡት ገንዘብ ብዛት በአሜሪካን ዶላር $ 22,572,000,000 (ሀያ ሁለት ቢሊዮን አምስት መቶ ሰባ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር

Thursday, August 25, 2016

የነጻነት ጮራ በኢትዮጵያችን በቅርቡ ይፈነጥቃል!!!!












የፈይሳ ሌሊሳ ቤተሰቦች ከሮይተርስ የዜና አውታር ጋር በመኖሪያ ቤቱ ቃለምልልስ አድርገዋል። ወላጅ እናቱ ''መንግስት ቢመለስ 

ምንም አይሆንም ብሏል። ምን ይመስልዎታል?''ተብለው ሲጠየቁ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል።





''እኔ አላምንም እዛው ይሁንልኝ። ልጄን እወደዋለሁ ቢመጣልኝ እፈልግ ነበር ነገር ግን ምን አደርጋለሁ። ብዙ ቀናቶች ሳለቅስ አሳልፌያለሁ። አሁን ግን ጥሩ ስሜት ይሰማኛል። እዛው ባለበት እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ። እሱ ብቻ ባለበት ሰላም ይሁንልኝ እንጂ!''

ባለቤቱ በበኩሏ ''በወቅቱ በጣም ፍርሃትና ድንጋጤ ወሮኝ ነበር። ነገርግን አልተገረምኩም ምክንያቱም አውቀዋለሁና። በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ የተገደሉ ሰዎችን አካል ሲያይ፣ ሲታሰሩና ሲደበደቡ ሲያይ ውስጡ ይቃጠል ነበር። ባደረገው ያልተገረምኩት የውስጡን ቁጭት ስለማውቀው ነው።''የነጻነት ቁንጮ የጀግኖቹ ጀግናምንም ሳይቸግራው ገንዘብ ወይ መኪና
ወርቅ ፣ናሃስ ፣ብር ሳይል ሳይበግረው ዝና :ሁለት ታዳጊ ሕጻናት ልጆቹን፣ አሮጊት እናቱን፣ ባለቤቱን ትቶ የወገኑን ብሶት በዓለም ዓደባባይ አሰምቷል። የነጻነት ጮራ በኢትዮጵያችን በቅርቡ ይፈነጥቃል። እስከዛው ፈይሳ ሌሊሳ ባለህበት ሰላምህ ይብዛ!!!
..
.



Tuesday, August 16, 2016

ኃላፊነት የማይሰማው መንግሥት ነው!!!



አንጋፋው የተቃውሞ ፖለቲከኛ ዶክተር መረራ ጉዲና ሀገራቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ለመግባት መንታ መንገድ ላይ መቆሟን ተናገሩ፡፡

"ብዙ ህዝብ ባለፉት 25 አመታት አገዛዙ በፈጸመበት ጭቆና መማረሩን የተናገሩት ዶክተር መረራ አሁን ላይ በየቦታው ሰዎች ለተቃውሞ በየአደባባዩ መውጣታቸውንና በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመው ይህ ሁኔታ ባለበት ከቀጠለ ደግሞ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል"

፡፡-+የተቃወመውን ወይም በቀጥታ ድጋፍ ያልሰጠውን ሁሉ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ዴሞክራሲ፣ ደርግ ናፋቂ፣ የደርግ ርዝራዥ፣ የሻዓቢያ ተላላኪ፣ አሸባሪዎች፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች ወዘተ የዕለት ከዕለት ማጣጣያ ከሆኑ ቆይቷል። ህገ መንግስቱ አክብረው፣ በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ድርጅቶችን የአሸባሪነት ስም በመለጠፍ ትግሉ አቅጣጫውን እንዲስት በመገፋፋት፤ ህብረተሰቡ ነፃ ሆኖ እንዳይኖር እንዳይናገር፣ እንዳይፅፍ፣ እንዳይቃወም፣ እንዳይደራጅ በስጋትና ጭንቀት በአገሩ ነፃ ዜጋ ሆኖ እንዳይኖር እየተደረገ ነው፡፡ ሀገሪቱ እኛ ከሌለን ያልቅላታል የሚሉ በስልጣን ላይ ያለው አካል ብቻ ነው ያለነሱ መሪ ያለነሱ አልሚ ያልነበረ ለወደፊቱም የማይኖር ማይመስላቸው ስልጣኑን አኝ አርገው አለቅ ያሉት ;;

ህዋሃትም በሰሞኑ ዘገባው ባለፉት ወራት ሲታዩ የነበሩትን ህዝባዊ ተቃውሞ እንደ ተራ ጩኸት እያጣጣለው ልክ እንደ ደርግ "በጩኸት የፈረሰች ከተማ እያሪኮ ብቻ ነች" የሚል አይነት እድምታ ያላቸው መግለጫዎች እያሰሙ ነው። ዛሬ እንዲህ አይነት መግለጫ ፍሬ ቢስ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ… በጩኸት ከፈረሱ በኋላ፡፡ በግብፅ አብዮት ወቅት አንድ የትጥቅ ትግል የሚያካሄድ ተቃዋሚ ድርጅትን ይመሩ የነበሩ ከማል ሀቢብ የተባሉ ሆስኒ ሙባረክ በወደቁ ማግስት Tahrir Square (በነፃነት አደባባይ) በአፕሪል18 ቀን 2011ዓ.ም ለታተመው Time መጽሔት "እኛ ለ40 አመት በጠመንጃ መገልበጥ ያልቻልነውን ህዝቡ ያለአንዳች የጦር መሳሪያ በ18 ቀን ውስጥ እውን አደረገው" ብለው በመገረም ተናግረዋል።

ሰላማዊ ህዝባዊ የአደባባይ ተቃውሞና ጩኸት መንግስትን ባያሰጋው ኖሮ ለምን ሰው አደባባይ እንዳይወጣ ይከለክላል?

እሪሪሪ ብሎ መጮህ ነፃነት ያስገኛል። ስለዚህ እንጩህ !!

Friday, February 19, 2016

አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !





ኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆናለች። እነ ጀነራል ሶሞራ በጭካኔና በግፍ ሕዝቡን በጥይት እያረገፊት ነው"" ባለፉት 3፣ 4 ቀናት ብቻ ቢያንስ ወደ መቶ የሚጠጉ ወገኖቻችን ተገድለዋል። "ቢያንስ" የሚለው ላይ አስመርበታለሁ። ለምን እጅግ በጣም ብዙ የቆሰሉ አሉ። የቆሰለ ሁሉም ይደናል ማለት አይደለም። ሃኩም ሄዶ መሞትም አለ።፡

በጣም ያሳዝናል.....በጣም ልብን ያደማል። አለም በሰለጠነችበት በዚህ 21ኛው አለም፣ እንደ ረሃብ፣ ድርቅ፣ ድህነት የመሳሰሉ የሁላችንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ችግሮች እያሉን፣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፣ በአጋዚዎች እጆች ላለፉት 25 አመታት እንደነበረው አሁን ዜጎች እየተገደሉ መሆናቸው በጣም ይሳዝናል።

በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚያሳየው ተቃዉሞው በጣም ተባብሷል። ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምቴ ፣ ከነቀምቴ ወደ ጂማ፣ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ ....የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል። በብዙ ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ ከፌዴራሎች ጋርም ግብግብ የፈጠሩበት ሁኔታ ነው ያለው። ሰላማዊ የሆነው እንቅስቃሴ፣ ወያኔዎች የኃይል እርምጃ በወሰዱ ቁጥር ወደ አመጽ መሸጋገሩ አይቀርም። እየተሸጋገረም ነው።


አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !

‎OromoProtest‬