Sunday, May 18, 2014

ላለፉት 23 ቀናት ክሥ ሳይመሠረትባቸው ታስረው ከሚገኙት ዘጠኝ የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ሚድያ ፀሐፊዎች የሆኑ ጋዜጠኞችና አምደኞች ስድስቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል!

zone9-e1398747809895


ላለፉት 23 ቀናት ክሥ ሳይመሠረትባቸው ታስረው ከሚገኙት ዘጠኝ የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ሚድያ ፀሐፊዎች የሆኑ ጋዜጠኞችና አምደኞች ስድስቱ ዛሬ፤ ቅዳሜ፣ ግንቦት 9/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበዋል

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት የጋዜጠኞቹንና የአምደኞቹን ጉዳይ ያየው በዝግ ሲሆን የቀረቡት ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሣዬ እንዲሁም ሌሎች ሦስት አምደኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡




የዞን-9 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች አራዳ ፍርድ ቤት ቀረቡ




ዛሬ ችሎት ያልቀረቡት አምደኞች መቼ እንደሚቀርቡ ለጊዜው በትክክል ባይታወቅም ሰሞኑን ይቀርባሉ የሚል ጭምጭምታ ተሰምቷል፡፡

የስምንት ታሣሪ ጋዜጠኞቹንና አምደኞቹን ፖሊስ በሽብር አድራጎት እንደሚጠረጥራቸው ለችሎቱ አስታውቆ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ  የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡





አራዳ ፍርድ ቤት




ፍርድ ቤቱም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ የ28 ቀናቱን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱንና ጉዳዩንም ለፊታችን ሰኔ 7/2006 ዓ.ም መቅጠሩን ተከላካይ ጠበቃው አቶ አምሃ መኮንን ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment