Thursday, January 16, 2014

በፊንፊኔ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት ተቀየሩ!!!!



በፊንፊኔ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት ተቀየሩ ።



በፊንፊኔ ፖሊስ ኮሚሽን በአስሩም ክፍለ ከተሞች የመከላከያ መኮንኖች ተዛውረው መመደባቸውን ታማኝ የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባላት የሆኑትና ከመቶ አለቃ እስከ ሻለቃ ደረጃ ያላቸው የመከላከያ መኮንኖች የፊንፊኔን ፖሊስ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ በአስሩም ክፍለ ከተሞች የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

ከዚሁም ጎን ለጎን በፊንፊኔ በሚገኙ ወረዳዎች “ኮሚኒቲ ፖሊስ” በሚል አዳዲስ የፌደራል ፖሊሶች እንደመተደቡ ምንጮቹ አያይዘው ገለፀዋል። በፊንፊኔ በፖሊስ ሃይል እምነት ያጣው ገዢው ፓርቲ ሕወሐት/ኢህአዴግ ታማኝ በሚላቸው መኮንኖችና የፌደራል ፖሊሶችን እየተካና አፈናውን እያጠናከረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም አሁን በተጀመረው የክልሉን ፖሊስ የማፍረስ ተግባር በቅርብ ጊዜ የፊንፊኔ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል።
ገዢው ፓርቲ ራሱ በደነገገው ሕገ-መንግስት ላይ ፖሊስ ፀጥታውን እንደሚቆጣጠር እንዲሁም መከላከያ መኮንኖች ገለልተኛ ሆኖ የአገሩን ሉአላዊነት እንደሚጠብቅና ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት ነፃ ሆኖ እንደሚቆም ሕገ-መንግስቱ የሚገልፅ ቢሆንም ነገር ግን ራሱ ላወጣው ሕገ መንግስት ተገዢ መሆን እንዳልቻለ የሕወሐት መኮንኖች ከመከላከያ ተዛውረው የፊንፊኔን ፖሊስ በበላይነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ መመደባቸው የሕገ-መንግስት ጥሰት እያካሄደ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ነው ብለዋል ምንጮቹ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በፊንፊኔ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች አጋልጠዋል። በፊንፊኔ የካና አራዳ ክፍለ ከተሞች “ኬርና ፕላን” በተባሉ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተሰሩት ጤና ጣቢያዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀይረው እስረኞች እየታሰሩባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06/07 ቤላ፣ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ቀበሌ 11 እንዲሁም ጃንሜዳ ቀበሌ 05 የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች በከፊል እንደሚጠቀሱ ያስታወቁት ምንጮቹ በተጠቀሱት ቦታዎች እስረኞች በብዛት ታስረው እንደሚገኙ አያይዘው ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment