Saturday, June 15, 2013

የወያኔ እስረኞች ነን !

የወያኔ እስረኞች ነን !

አቶ በቀለ ገርባን አቶ ሌሊሳ ኦልባናን እንዲሁም ብዙ ስማቸዉን ያልዘረዘርናቸዉ የኦሮሞ ታጋዬችን ወያኔ ለቅሞ ቢያስራቸውም…. ነገ ብዙ ሌሊሳዎች…. ብዙ ካሚል ሸምሱዎች…… ብዙ በቀለዎች …አንደ አሸን እና እንደ እንጉዳይ ወደ ትግሉ መድረክ ብቅ ልንል ይገባል። ምናልባት ወደ እንደዚህ አለው ትግል ለመግባት ፍርሃታችን ይዞን ይሆናል….ላለመታሰር ብለንም ፈርተን ይሆናል…..አልገባን ይሆን ይሆናል ወይንም እውነታውን እየካድን ሊሆን ይችል ይሆናል እንጂ አሁንም የወያኔ እስረኞች ነን። ምናልባት ከእነ ካሚል ሸምሱ እና ከእነ አቶ በቀለ ከእነ አቶ ሌሊሳየሚለየን እኛ መዝገብ የማያውቀን እስረኞች እና ቤታችን የምናድር ግዞተኛ መሆናችን ብቻ ነው።እኛ ሁላችንም ከፍርሃት በታች ተዘግተን ፣ ለፍርሃት ባሮች ሆነን ድፍን 21 ዓመታት አናታችን ላይ ዳንኪራቸውን እየረገጡብን፣ በብዙ አዋረዱን ላላፉት 21 ዓመታት በፍርሃት የወያኔ የማስፈራሪያ ሰለባዎች ሆንን። አሁን ግን ሁላችንምከተሸሸግንበት፣ የሞት ሽታ ከሸተተን መንደር መዉጣት እና ወያኔ…በተራው ሊፈራ እና ሊደነግጥ ይገባዋል።
ወዳጆቼ በፊንፊኔ ላይ የምንኖር ኦሮሞዎች እኛ ብቻቁጥራችን ከሺህዎች በላይ የምንዘል በወጣት የዕድሜክልል የምንገኘ ሁሉ መዝገብ የሚያውቀው እስረኛ ለመሆን ብንፈቅድ እንኳን ወያኔ እኛን ሁላችንንም ለማሰር አቅም አይኖረውም። በ1997 ዓ.ም በነበረው እንኳን ወያኔዎች ማሰር የቻሉት 50 ሺህ ሰው እንኳን አይሞላም ፤ በፍርሃት በየቤታችን ተቀፍድደን ከምንታሰር በዘመናችን ትውልድ የሚዘክረው ታላቁ የኦሮሞዎችን ትግል እንቀላቀል። ይህ ታላቅ ዘመቻ በእርግጥ ታላቁን የኦሮሞ ትግል ለመጀመር ፈር ቀዳጅ ይሆናል። አሁን ከፍርሃታችን ወጥተን ትልቅ እርምጃ ተራምደናል፤ ከዚህ በሃላ ተመልሰን ወደ ፍርሃት ቀንበር መግባት አይገባንም።ወያኔ ምንም ሊያደርገን አይችልም፤ ምናልባት ሊያደርጉን ከቻሉ የሚችሉት እኛን ማሰር ብቻ ነው፤ይህ ደግሞ በራሱ ትልቅ ድል ነው። 30 ሚሊዮን መዝገብ የነካውን እስረኛ መመገብ፣ ማስተዳደር፣ መጠበቅ በራሱ ወያኔን ያናጋዋል፣ ያፈርሰዋል። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ የልባችንን በልባችን ይዘን ክፍተቶቻችንን እርስ በርሳችን በአንድነት ተነጋግረን ዛሬ በዋናነት ስለምንሻዉ ነፃነት ተገንዝበን በአንድነት መውጣታችንም ሆነ መታሰራችን ወያኔን ከተቀመጠበት የስልጣን ኮርቻ ሊያወርደው የሚችል ትልቅ ውሳኔ ነውና ወደ ፊት እንበል ይለይለት።
ድል ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ!

No comments:

Post a Comment