Friday, February 19, 2016

አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !





ኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆናለች። እነ ጀነራል ሶሞራ በጭካኔና በግፍ ሕዝቡን በጥይት እያረገፊት ነው"" ባለፉት 3፣ 4 ቀናት ብቻ ቢያንስ ወደ መቶ የሚጠጉ ወገኖቻችን ተገድለዋል። "ቢያንስ" የሚለው ላይ አስመርበታለሁ። ለምን እጅግ በጣም ብዙ የቆሰሉ አሉ። የቆሰለ ሁሉም ይደናል ማለት አይደለም። ሃኩም ሄዶ መሞትም አለ።፡

በጣም ያሳዝናል.....በጣም ልብን ያደማል። አለም በሰለጠነችበት በዚህ 21ኛው አለም፣ እንደ ረሃብ፣ ድርቅ፣ ድህነት የመሳሰሉ የሁላችንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ችግሮች እያሉን፣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፣ በአጋዚዎች እጆች ላለፉት 25 አመታት እንደነበረው አሁን ዜጎች እየተገደሉ መሆናቸው በጣም ይሳዝናል።

በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚያሳየው ተቃዉሞው በጣም ተባብሷል። ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምቴ ፣ ከነቀምቴ ወደ ጂማ፣ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ ....የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል። በብዙ ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ ከፌዴራሎች ጋርም ግብግብ የፈጠሩበት ሁኔታ ነው ያለው። ሰላማዊ የሆነው እንቅስቃሴ፣ ወያኔዎች የኃይል እርምጃ በወሰዱ ቁጥር ወደ አመጽ መሸጋገሩ አይቀርም። እየተሸጋገረም ነው።


አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !

‎OromoProtest‬