Sunday, October 18, 2015

BREAKING NEWS

BREAKING NEWS

**********************

The public meeting convened by Oromo Federalist Congress (OFC) in Finfinne Sunday, October 18, to discuss the so-called Addis Ababa and Oromia Special Zone Integrated Development Master Plan has ended adopting a 9-point resolution expected to be announced by OFC in an official press release. Sources say the meeting concluded that the Master Plan is a land grab policy disguised as a development plan and called on Ethiopian authorities to halt it, and on the public to continue rejecting it.

Saturday, October 17, 2015

365 DAYS IN PRISON

ፍትሕና ልዕልና ጋዜጦች፣ እንዲሁም የፋክትና የአዲስ ታይምስ መፅሔቶች ባለቤትና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ከታሠረ ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም አንድ ዓመቱን ደፍኗል፡፡ የተመስገን ጤና አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቡቹ ገልጸዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ግን ተመስገን ሕክምና እያገኘ መሆኑን ጤናማም እንደሆነ ይናገራል፡፡

የተመስገን ደሣለኝ ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሣለኝ ተመስገንን ረቡዕ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ዝዋይ ሄዶ መጎብኘቱንና፣ ወንድሙ የግራ ጆሮው ሙሉ በሙሉ እንደማይሰማ፣ ጀርባው ላይ ያለው እብጠት እየባሰበት መሆኑን በጀርባው መተኛትም እንደማይችል አስረድቷል፡፡
ተመስገን ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ሕክምና እንደማያገኝና ቤተሰቡም ለማሳከም ቢጠይቅም ፍቃድ መነፈጉን፣ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ይዘው ሄደው “በማረሚያ ቤቱ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም” የሚል መልስ ማግኘታቸውን ታሪኩ ለቪኦኤ ገልጿል፡፡
ተመስገን ያዘጋጃቸው ከነበሩት መፅሔቶች በአንዱ ላይ አምደኛ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምም ከጥቂት ወራት በፊት ከፕሮፌሰር መስፍንና ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው እዚያው ዝዋይ ድረስ ሄደው እንዳዩትና በወቅቱ የግራ ጆሮው ይደማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
የተመስገን ደሣለኝ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንንም የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ዝዋይ ሄደው ያዩት መሆናቸውንና በቦታው ርቀት ምክንያት ከዚያ በኋላ በአካል እንዳላገኙት ገልፀው ከቤተሰቦቹ ግን አሁን ያለበትን ሁኔታ እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት፣ መንግሥቱ ባወጣቸው ደንቦችና በዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችም መሠረት ማንም እሥረኛ ጤንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መያዝ እንደሚገባው፤ አስፈላጊ በሆነ ጊዜም ሕክምና የማግኘት መብት እንዳለው፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርም ሆነ የወህኒ ቤቱ ሃኪም ታራሚው ሕክምና ማግኘቱን የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤቱ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ ተመስገን አዲስ አበባ ድረስ ተወስዶ ሕክምና ማግኘቱን፤ በማረሚያ ቤቱ ውስጥም እየታከመ መሆኑን፣ ጤናማና እየተንቀሣቀሰ ያለ መሆኑን ገልፀው ጤንነቱ ታውኳል፤ ሕክምና ማግኘት አልቻለም የተባለው ሃሰት መሆኑን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡
ጠበቃው አቶ አምሃ ግን አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ አለመታከሙን፣ ሄዶ ቢሆን ኖሮ እርሣቸው ያውቁ እንደነበር ተናግረዋ የማረሚያ ቤቱን የሥራ ኃላፊ መግለጫ አስተባብለዋል፡፡