Thursday, May 21, 2015

ህዝባዊ እምቢተኝነት ያብብ ይለምልም!




ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙዚቃው በተላለፈው ጥሪ የ24ዓመቱን የህወሀት አገዛዝ በቃህ የሚልበት ጊዜው ዛሬ ሳይሆን አሁኑኑ ነውገዥው የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አምስተኛው የኢትዬጲያ ብሄራዊ ምርጫ ይካሄዳል ፡፡ ሶስተኛውና ተስፋ የፈነጠቀው አገራዊ ምርጫ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የፓለቲካ ምህዳር መዘጋት ከተጠናቀቀ በኋላ የተካሄደውን አራተኛው ምርጫ ኢህአዴግ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫ “በማሸነፍ” ተቆጣጥሮታል፡፡ ከቀናት በኋላ የሚካሄደው አምስተኛ አገራዊ ምርጫ የፓለቲካ ምህዳሩን ለማሻሻል የሚረዳና መጠነኛ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እያዳከመ ተቺዎችን እና ሌሎች ነጻ ድምጾችን ለእስር ዳርጎ በከፍተኛ ጫና ታጅቦ ይካሄዳል፡።በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት አቶ በቀለ ገርባ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ተደበደቡ። ዘረፋም ተፈጽሞባቸዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተርመረራ ጉዲና መንግስት ምጥ ይዞታል። የህዝብ ማዕበል አስፈርቶታል። የለየለት ተናካሽ ወጥቶታል ይላሉ።
_ምርጫው ሲቃረብ አፈናው፡ እስሩ፡ ማሰቃየቱ፡ ማሳቀቁ፡ ግድያው በየአቅጣጫው በርትቷል። ሰማያዊ፡ መድረክና ሌሎች ፓርቲዎች አቤቱታቸውን እያቀረቡ ናቸው። በዚህ መሃል ዕቅድ ያልተያዘላቸው፡ በጀት ያልተመደበላቸው ፕሮጀክቶች መሰረተ ድንጋይ በየቦታው እየተጣለላቸው ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በዚህም የተነሳ ሰሞኑን ስራ በዝቶባቸዋል።
_አዲስ አብዮተኛ ሙዚቃ ሰሞኑን ለአድማጭ ጆሮ ደርሷል።
ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙዚቃው በተላለፈው ጥሪ የ24ዓመቱን የህወሀት አገዛዝ በቃህ የሚልበት ጊዜው ዛሬ ሳይሆን አሁኑኑ ነው!!!