የተዘነጉት ኦሮሞ እስረኞች እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ!
ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ኦብሴን(ሰማቸው ለደህንነታቸው ሲባል የተቀየረ ነው ) ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ኦብሴ ገና የ20 ዓመት ወጣት እና ....... የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ናት፡፡ ኦብሴን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል እህቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እንደተለመደው ኦብሴን አገኘናት እና ብዙ ነገሮችንአጫወተችን፡፡ ትረካዋን የጀመረችው እህቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ ተከሰው የተፈረደባቸውን ሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበውየተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉ ነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለትየእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነትአለመሆኑን ነገረችን፡፡
ሲፈን ትባላለች በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል ወንድሟን ልትጎበኝ ነው፡፡‹‹ለአንድ ሰው የመጡ የማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶችመሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደ ቤት የገቡት፡፡ስልካችሁን አጥፉ ወደ ማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣ ነው በቁጥጥር ስር ውለካል› አlት ። ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ቀኑ አርብ ነበር፤ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኑን አላየነውምነበር፤ ይሙት ይኑር የምናውቀውነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ የታሠረ ሰው ሲፈታ በሱ አማካይነት መልዕክት ደረሰን ፡፡ ‹አንቺ ደህና ከሆንሽ .,....ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል› የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንን የሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት ጉዳይ ፍርድ ቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለት ጉዳያቸው በኢፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡
ቦንሳ በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል አባቱን ልጎበኝ ነው፡፡ ግጥም መግጠም ይወዳል ፡፡እናም በየጊዜው የጀመረውን ግጥሞች የተበላሹ ሲመስለው ቅርጫት ውስጥ ይጥላቸዋል፡፡ ይመስለኛል፤ የቤት ሠራተኛችን እጅ አለበት፡፡ ሲታሰር የቀረበበት መረጃ እነዚህ የተጣሉ ወረቀቶችተሰብስበው ‹ለኦነግ ግጥም ስታዘጋጅ ነው›የሚል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፈቃድ የነበረው፣ ያውምየማይሠራ ሽጉጥም እንዲሁ በማስረጃነት የቀረበበት መሆኑ ነው፡፡›› በማለት ፍርዱ ፍትሐዊ አለመሆኑን እና አባቱም ነጻ መሆኑን እንደሚያምን ነግሮናል፡፡
ጂቱ በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡‹‹የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ሲታሰሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜናነው፤ እንኳን አገር ወዳዷ እናቴ ማንም ባገሩ ላይ የሚያደርገውን ነገር ነው አደረጉ ያለው፤›› የዜናውን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ወቅሳለች፡፡ እናቷ ሕዝብና አገር የማሸበር ፍላጎት ሊኖራት ለአገር ፍቅር ሕይወቷን የሰጠች መሆኗን ስታጫውተን‹‹እናቴ ሁልጊዜ የምትነግረኝ ነገር አለ፤ ሕይወቴ ማለፍ ካለበት አገሬን በሚጠቅም ነገር መሆን አለበት ትለኝ ነበር፤›› ብላናለች፡፡ ነገር ግን መንግሥት በአንድ በኩል ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በመሞከር ነው ያሰርኳችሁ እያለ በሌላ በኩል ደግሞየፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፤›› ካለች በኋላ ‹‹ተቃዋሚ መባላቸው ካልቀረ የኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካ እስረኞች እንደሆኑ ቢያምን እንኳ ጥሩ ነው፤›› ብላናለች፡፡ ‹‹እናቴ ለአገሯ ከማንም በላይ ሠርታለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን የኦሮሞ ህዝብ ለእናቴ ውለታዋን እየከፈልዋት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ያለ ሃጢያታቸው ሃጢያት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት›› በማለት ፍርዱ አገር ወዳድእናቷን የሚያዋርድ እንደሆነ በሐዘን ተርካልናለች፡፡
የእናቷ በአሸባሪነት መፈረጅ ለጂቱ ማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሰባት መሆኑንም አጫውታናለች፡፡ ‹‹ለትምህርቴ መስጠት የሚገባኝ ጊዜ ያህል መስጠት አልቻልኩም፤ እናቴ የታሰረችው እኔ ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲ መግባት ሲኖርብኝ አሁን ግን ‹ነርሲንግ› እየተማርኩ ያለሁት በዚሁ ተፅዕኖ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የእነርሱን የእስር ዜና ኢቲቪ ከአቀረበበት መንገድ አኳያ ትምህርት ቤት ውስጥ ራሱ እኔን መቅረብ የሚፈሩ ሰዎች አሉ፤› በማለት የእናቷ እስር በእርሷ ማኅበራዊ ሕይወቷ ላይ ያጠላበትን ጥላ አጫውታናለች፡፡
በእናቴ ስም ተይዞ የነበረው የቀበሌ ቤታችን በልማት ስም ሲፈርስ እንኳን ለጎረቤቶቻችን በምትኩሲሰጣቸው ለእኛ ግን አልተሰጠንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መታወቂያ እንኳን ለኛ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም›› ቤታቸውን ካፈረሱባቸው በኋላ አክስቷ ጋር እየኖረች እንደሆነ ስትነግረን በየመሐሉ እየገታችው ታወራልን የነበረው እምባዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲወርድ ማድረግ የቻልነው ነገር ቢኖር በዝምታ ማጀብ ነበር፡፡
‹‹ያለ አባት ያሳደገችኝን የእናቴን ፍቅሯን አልጠገብኩትም›› የምትለን ጂቱ ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለኔ የሚገባኝ ቦታ ቃሊቲ አልነበረም፡፡››በማለት ብዙ ነገር መሥራት በነበረባት ጊዜ ቃሊቲ በመመላለስ እንዲባክን መንግሥት እንደፈረደባት እንደሚሰማት ነግራናለች፡፡ ‹ቶለሼ በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ከታሰሩት ኦሮሞዎች መካከል እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡‹አራት ዓመቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ነው ያሳለፍኩት፤ ከ16 ዓመታት በኋላ ከእስር የተፈታው አባቴ የራሱን ሁሉ ነገር ትቶ ሕይወቱን ለኔ መስዋዕት ባያደርግ ኖሮ አልወጣውም ነበር›› እናትዋ ከመታሰሯ ሁለት ወር ያክል ቀድሞ በተፈታው አባቷ ድጋፍ ከብዙ ቀውስ እንደተረፈች እየነገረችን ከናቷ ጋር የነበራትን ፍቅር ‹‹እናቴ ሁለ ነገሬ ነች!››ብላለች፡፡
‹‹እናቴን ሊጎዳ የሚያስብ ሰው እኔን አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ተሳቅቄ ነው የምኖረው›› በማለት በዙሪያዋ ያለውን ወዳጅ እና ጠላት እንኳንማመን እየቸገራት እሷ ራሷም ቢሆን ከማኅበረሰብ የመነጠል እና የመስጋት ስነልቦናዊ ችግር ውስጥ እንደሆነች አስረድታናለች፡፡
‹‹የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ‹የቤታችን ሰላም እናፍቅር ከበቀለ ገርባ ጋር ታስሯል› ያለችው በጣም ትክክል ነው›› በማለት በታሰሩት ሰዎች ቁጥርእኩልየሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ፈተና ውስጥ እያለፉ መሆኑን አበክራ ነግራናለች፡፡
የቶለሼ ታሪክ የብቻዋ ታሪክ አይደለም፡፡ የሌሎች የብዙ ቤተሰቦቻቸው የታሰሩባቸው ኦሮሞ ቤተሰቦች ታሪክ ነው፡፡ ቦንሳ ‹‹እንደኔ ሁሉ ችግር ላይ ያሉ፣ አባቶቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ ልጆች አሉ›› ፡፡ በእስረኞች መሐል ‹‹ተነስቷል በሚልፀብ›› ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ሌላ ተጨማሪ ጫና አሳድሮባቸዋል ፡፡ እዚህ የቀሩት ታሳሪዎችም አጋሮቻቸውን በማጣት ለብቸኝነት ስሜት ተዳርገዋል፡፡
ከነርሱ መዝገብ ውጪ ያሉ ሌሎችም እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው በተመሳሳይ ፈተና ውስጥ መሆናቸውን እስረኞችን ለመጎብኘት በሄድንባቸው ጊዜያት ተረድተናል፡፡ ይልቁንም፤ ከቦታ ቦታ እያዘዋወረ ስቃያቸውን ያበዛል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ወደ ዝዋይእንዲዘዋወር የተደረገው ከታሰሩት ኦሮሞዎች አቶ በቀለ ገርባ ተጠቃሽ ነው፡፡
አቶ በቀለ ባለቤት ከስራ ገበታዋ አባረዋትም ልጁ በእናትዬው መፍጨርጨር ሕይወታቸውን እንዲመሩ ከመገደዳቸውም በላይ አሁን የቤቱን አባውራ ለመጠየቅ ዝዋይ ድረስ እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት የፖለቲካ አይደሉም የሚላቸውን የፖለቲካ እስረኞችን ከነቤተሰቦቻቸው ከሚቀጣበት መንገድ ይታረም ዘንድ ሊጠየቅ ይገባዋል በማለት የምንመክረው፡
Juukii Bareentoo

No comments:
Post a Comment