Friday, November 15, 2013

አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል!

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጐን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን በዛሬው እለት አስመስክሯል



ሳውዲ ኤንባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ሊያረጉ የነበሩት ያገሬ ልጆች በፈደራል ፖሊስ እደዚ ነበር የተበተኑት አስኪ ፈረዱ!


የሳውዲ መንግስትና ኢህአዴግ በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ማጥቃት የቀጠሉ ቢሆንም በዛሬው እለት በየት/ቤቱ የታዩት ነገሮች ከሌላው ጊዜ በጣም የተለየ ነበር፡፡ ብዙ ተማሪዎች ጥቁር ልብስ በመልበስና በእረፍት ሰዓት ደግሞ ጧፍ በማብራት ሳውዲ በወገን ላይ እያደረሰ ያለው ስቃይና የመንግስትን ቸልተኝነት አውግዘዋል፡፡ከነዚህም ት/ቤቶች ውስጥ መድሀኒያለም ፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኮልፌ እንዲሁም ሌሎች የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በስፋት በዛሬው የጥቁር መልበስና የጧፍ ማብራት ስነ-ስርአት አድርገው ሀዘኛቸውን ገልጸዋል፡፡ሰኞና ከዛም በኋላ ባሉት ቀናት ተማሪዎቹ ከወገናቸው ጎን መቆም እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል፡፡
--------------------------------------------------------------------
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጐን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን በዛሬው እለት አስመስክሯል!
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡
የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡

No comments:

Post a Comment