የኦነግ ወታደሮች አንድ የጸጥታ ሹም ገድለው 7 ፖሊሶችን አቆሰሉ
ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
በቦረና ዞን ፣ የሚኦ ወረዳ የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ጁኬ የአካባቢውን ፖሊሶች በማሰልፍ የኦነግን ታጣቂዎች ለማደን ሚያዚያ 29፣ 2005 ዓም ቢንቀሳቀሱም የኦነግ ወታደሮች ጨሶ እና ሜጢ በሚባል ቦታ ላይ አድፍጠው በመጠበቅ በወሰዱት እርምጃ ፣ የጸጥታ ሹሙን አቶ ጁኬን ገድለው፣ 7 ፖሊሶች ደግሞ አቁስለዋል። 6ቱ ፖሊሶች በያቤሎ ሆስፒታል ተኝተው በመታከም ላይ ሲሆኑ አንዱ ፖሊስ ደግሞ በጽኑ በመቁሰሉ ወደ አዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል ። የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ ሹም የቀብር ስነስርአትም ግንቦት 1 ፣ 2005 ዓም በኢዲሎላ ከተማ መፈጸሙን የአካባቢው ወኪላችን ገልጿል።
ኢሳት ዜና

No comments:
Post a Comment