የመለስ ራዕይ በ‹‹አዲስ ታይምስ›› መፅሄት ተተገበረ
ምንም ጥርጥር የለውም መለስ ዜናዊ ፍፁም አምባገነን ነበር፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ከአንድ ክፍለ ጦር በላይ የተለየ ሀሳብን እና ነፃ ሚዲያን ይፈራል፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ወራሾቹም ሀሳቡን በነፃነት የሚገልፅን ከመለስ በባሰ መልኩ ይፈራሉ፡፡ ይህ ፍራቻቸው ወደ ጭፍን አምባገነንነት ስለቀየራቸው መላ ሀገሪቷን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየገፏት ነው፡፡
የሆነ ሆኖ መለስ ከአደባባይ ከራቀ በኋላ በፍትህ ቤተሰቦች የሚመራ ትልቅ ሚዲያ ሲዘጋ ‹‹አዲስ ታይምስ›› ሁለተኛዋ ናት፡፡
ለ‹‹አዲስ ታይምስ›› መዘጋት መንግስት የሰጠው ሶስት ምክንያት፡-
1. የባለቤትነት ድርሻ ከአንዱ ወደ ሌላው ሲዞር በ15 ቀን ውስጥ አላሳወቃችሁም፣
2. ህትመቱ ሲወጣ ለቤተ-መዛግብት ሁለት ሁለት ኮፒ በነፃ አልሰጣችሁም እና
3. የገንዘብ ምንጫችሁ አይታወቅም የሚሉ ናቸው፡፡
በቃ፡፡ ህዝብን መናቅ ሙያ ብሎ የያዘው ገዥው ፓርቲ መፅሄታችንን ለመዝጋት የሰጠው ምክንያት እነዚህ ናቸው፡፡ አስገራሚው ጉዳይ የባለቤትነት ድርሻ ሲዞር በጊዜው ማስታወቃችን፣ ለቤተ-መዛግብትም ህትመታችን ሲወጣ ሁለት ሁለት ሳይሆን አምስት አምስት ኮፒ በነፃ የሰጠንበትን ማስረጃ ማቅረባችን እና ምንጩ አይታወቅም ለሚለው ደግሞ የመፅሄቱ ኮፒ 35 ሺህ በመሆኑ ምንጩ ህዝባችን (አንባቢያን) መሆናቸውን ብሮድ ካስት አብጠርጥሮ ማወቁ ነው፡፡
ይሁንና እነዚህ የተጠቀሱት ምክንያቶችስ ተፈፅመው ቢሆን እንኳ አዋጁ የሚለው አስራ አምስት ሺህ ብር ያስቀጣል ነው፡፡ ታዲያ መዝጋትን ከየት ያመጡት ህግ ነው? ማንአለብኝነት እና ጉልበተኝነት ካልሆነ በቀር፡፡
በነገራችን ላይ ‹‹ብሮድ ካስት›› በሚል ስያሜ የተመሰረተ ተቋም ከቴሌቪዥንና ራዲዮን ውጭ ያልተፈቀደለትን የ‹‹ህትመት ሚዲያ››ንም ጨምሮ መቆጣጠሩ ከበረከት ስምዖን ውጪ ለማንም ግልፅ አይደለም፡፡ ለቤተ-መፅሀፍት መፅሄት ማስገባትን እና አለማስገባትንም እንዲሁ ከሙያ ብቃት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በረከት ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡
… አሁን የመለስ ራዕይ ግልፅ ነው፤ አፈናውን አጠናክሮ ማስቀጠል፡፡
መቼም ሃያ አንድ ዓመት ሙሉ በስልጣን ላይ ተቀምጦ ምንም ያልፈየደን መሪ፣ ልክ ስልጣን በያዘ ማግስት ህይወቱ እንዳለፈ ሰው ሁሉ ‹‹ራዕይ ነበረው፣ እናስቀጥለዋለን…›› ጂኒ ቁልቋል ማለቱ በህዝብ ላይ ማላገጥ ነው፡፡ ለሀገር የሚጠቅም ራዕይ ቢኖረው ኖሮ፣ በስልጣን ላይ ያሳለፋቸው ሃያ አንድ ዓመታት ከበቂ በላይ ነበሩና፡፡
ጥያቄው ግን ‹‹ይህ የቀልድ ዘመን ዕድሜው ስንት ነው?›› የሚል ነው፡፡ ስድስት ወር፣ አንድ ዓመት ወይስ ሁለት ዓመት? ….በጣም… በጣም በቅርቡ የምናየው ይሆናል፡፡ (በዓለም አቀፍ መድረክ የተሸነፈበትንም ታላቅ ዜና ጊዜው ሲደርስ እንሰማለን፡፡)
የመለስ ራዕይ በ‹‹አዲስ ታይምስ›› መፅሄት ተተገበረ!!!

ye gudayu adiss neger adelem woyana yalemkenyat yemimera chifen ,Abagenenawi serat yemimera new ere tekdeno yebsele tbloenji ......
ReplyDelete