ኢትዮጵያ በ2012 ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛላ ች !
ከነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በራሱና በጽሑፍ አቅራቢዎች አምስት ጊዜያት ታትመው በወጡ መጣጥፎች ምክንያት ክስ ተመሥርቶበት፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ዋስትና በመከልከሉ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ መደረጉ ይታወሳል፡፡
ዓቃቤ ሕግ ላለፉት ሦስት ወራት አቋርጦት በድጋሚ በተንቀሳቀሰው ክስ ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገን በተለያዩ ጊዜያት ዕትሞች ‹‹ሞት የማይፈሩ ወጣቶች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እስከ መጨፈር፣ የሁለተኛ ዜግነት ሕይወት እስከመቼና ሲኖዶስና መጅሊስ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ›› የሚሉ መጣጥፎች ማወጣቱ ተገልጿል
<<<<ፍርድ ቤቱ በሁለተኛነት ክስ የተመሠረተበትና የፍትሕ አሳታሚ የሆነው ማስተዋል የሕትመትና የማስታወቂያ ድርጅትም እንዲቀርብ አዞ፣ ክሱ መቀጠል አለመቀጠሉን በሚመለከት ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ፍትሕ ጋዜጣ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ለሕትመት ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የገባ ቢሆንም፣ ‹‹ፍትሕ ሚኒስቴር እንዳታትም ብሎኛል›› በሚል ምክንያት ማተሚያ ቤቱ አላትምም ማለቱ ይታወሳል::
ጋዜጣው በወቅቱ ለምን እንዳልታተመ እስካሁን በግልጽ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፣ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት መለስ ዜናዊ ሕመምና በአጠቃላይ በወቅቱ ስለነበሩበት ሁኔታዎች የሚያትት መጣጥፍ ይዞ ስለነበር፣ ጋዜጣው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም፣ ጋዜጠኛ ተመስገን በማኔጂንግ ኤዲተርነት ‹‹አዲስ ታይምስ›› በሚባል መጽሔት ላይ እየሠራ ይገኛል
GENA TGLACHIN YKETILALL WEYANEA TEBABREN KALATEFAN GENA KEZI YEBASE CHIGR EDEMIGETMEN MEZENGAT YELEBINIM
ReplyDelete