Friday, February 19, 2016

አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !





ኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆናለች። እነ ጀነራል ሶሞራ በጭካኔና በግፍ ሕዝቡን በጥይት እያረገፊት ነው"" ባለፉት 3፣ 4 ቀናት ብቻ ቢያንስ ወደ መቶ የሚጠጉ ወገኖቻችን ተገድለዋል። "ቢያንስ" የሚለው ላይ አስመርበታለሁ። ለምን እጅግ በጣም ብዙ የቆሰሉ አሉ። የቆሰለ ሁሉም ይደናል ማለት አይደለም። ሃኩም ሄዶ መሞትም አለ።፡

በጣም ያሳዝናል.....በጣም ልብን ያደማል። አለም በሰለጠነችበት በዚህ 21ኛው አለም፣ እንደ ረሃብ፣ ድርቅ፣ ድህነት የመሳሰሉ የሁላችንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ችግሮች እያሉን፣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፣ በአጋዚዎች እጆች ላለፉት 25 አመታት እንደነበረው አሁን ዜጎች እየተገደሉ መሆናቸው በጣም ይሳዝናል።

በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚያሳየው ተቃዉሞው በጣም ተባብሷል። ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምቴ ፣ ከነቀምቴ ወደ ጂማ፣ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ ....የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል። በብዙ ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ ከፌዴራሎች ጋርም ግብግብ የፈጠሩበት ሁኔታ ነው ያለው። ሰላማዊ የሆነው እንቅስቃሴ፣ ወያኔዎች የኃይል እርምጃ በወሰዱ ቁጥር ወደ አመጽ መሸጋገሩ አይቀርም። እየተሸጋገረም ነው።


አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !

‎OromoProtest‬

Saturday, December 19, 2015

የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል

"ጥቂቶች በብርሀን ፍጥነት ተዝቆ ወደማያልቅ ሀብት የተመነጠቁበት መንኮራኩር፣ መሬት "

ከ5 ዓመታት በፊት እኚህ ክቡር ሰው ሲናገሩ መስሚያ ጆሮ ቢኖራችሁ ዛሬ መያዣ መጨበጫ ባልጠፋችሁ። በነገራችን ላይ ይህ የአቶ በቀለ ገርባ ንግግር እና የአቶ አንዷለም አራጌ ንግግር ምንጊዜም ልቤን የሚያነሳሳኝ፣ በሀገሬ ተስፋ ከሚሰጡኝ መሳጭ ንግግሮች ዋነኞቹ ናቸው

ሀገር መምራት ቀላል እንዳልሆነ እናውቃለን ነገር ግን ከዓመት ዓመት የሕዝቡን ብሶት እያዳመጠ እየተሻለው፣ ልምድ እየቀሰመ ሀገሪቱን ሕዝቡን ወደፊት ማራመድ ሲገባው ከዕለት ወደ ዕለት ወደኋላ እየተመለሰ፣ የኋሊት እየሄደ ሀገሪቱን መምራት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል::

የኤፌድሪ ሕግ መንግስት እንደሚናገረው ፣ የገዢው ሥርዓት የፖሊሲ ሰነድ እንደሚገልጸው መሬት የመንግስት እና የሕዝብ ነው ይላል:: ነገርግን መሬት የሕዝብ ነው፣ የመንግስት ነው፣ የሁለቱም ነው? መሬት የማንም አይደለም:: መሬት የገዢ ባለስልጣኖች የግል ንብረት ነው::

እንደፈለገ የሚሸጡት፣ የሚለውጡት፣ ጓደኛ የሚያፈሩበት፣ በዘመድ አዝማድ የሚያከፋፍሉት፣ ለወገን እያሉ ለነሱ ፓርቲ አባላት መመልመያ የሚጠቀሙበት ማማለያ ነው መሬት::

*መሬት የተማረውን ሳይቀር፡ ምሁሩን ሳይቀር ማሳወርያ ሆኗል። ዛሬ ምሁሩን አንዳንድ ቦታ በአበዛኛው በምንመለከትበት ጊዜ ስለፍትሕ፣ ስለመብት፣ ስለ እኩልነት የማያወራበት ጊዜ ደርሷል።ምክንያቱ ይኼ ማሳወርያ ነው ዛሬ በየከተማው እና በአዲስ አበባ ዙርያና ሌሎች ከተሞች አካባቢ በብዛት መሬት እየተሰጣችው አፋቸው ተሸብቧል።ስለዚህ መሬት አፍ መሸበቢያ ነው።

* መሬት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ መሳቢያ ማግኔት ሆኗል። ዳያስፖራ እየተባለ በአንድ ወቅት ግር... ብለው መጥተው፣ እዚህ ወገኖቻችን ሜዳ ላይ ወድቀው አንዲት ስንዝር መሬት የሌላቸው ወገኖች እያሉ በውጭ ቢያንስ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መጥተው መሬት ተቀራምተው ሽጠውት ሄደዋል። ስለዚህ ማግኔት ነው የምንለው ለዚህ ነው።
*መሬት ዛሬ ጥቂቶች በብርሀን ፍጥነት ተዝቆ ወደማያልቅ ሀብት የተመነጠቁበት መንኮራኩር ነው።
ብንመለከት፣ እነድውም አንዳንዶቹን ሀብታሞች ብንጠይቃቸው... በሕዝቡ ዘንድ "ታሪኬ በአጭሩ" እየተባሉ የሚጠሩ አሉ። "እንዴት ነው፣ ይህ ሀብት ከየት መጣ እንዴት አገኛችሁ?" ተብለው ቢጠየቁ "እንደዚህ አድርጌ፣ እንደዚህ ለፍቼ አመጣሁ..." ማለት እንኳ የማይችሉ፣ገንዘቡን እንዴት እንዳፈሩት የማያውቁ...ስለዚህ ዛሬ መሬት እንደዚህ ነው:: መሬት የምንም አይደለም
መሬት ወሳኝ ሀብት መሆኑን እናውቃለን::
እኛ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ሀብት ጋራ ባለን ግንኙነት ምክንያት የዜገነት ደረጃችን በ4 ቦታ የተከፈለ ይመስለኛል:-->

1.መሬቱን የሚሸጡ አሉ አንደኛ ደረጃ ዜጎች
2.መሬቱን ከነሱ የሚቀበሉ አሉ፣ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች

3.እነሱ ሲቀባበሉ ቁጭ ብሎ ትዕይንቱን የሚመለከተ ዜጋ ደግሞ አለ ፤ ሦስተኛ ደረጃ- የበይ ተመልካች
4.መሬቱን ተነጥቆ፣ እትብቱ ከተቀበረበት፣ ተወልዶ ካደገበት መሬቱ ሥፍራ እየተባረረ መሬቱ ለሌላ የሚሰጥ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆነ አርሶ አደር ደግሞ አለ::

እኛ ምንታገለው ለዚህ ነው!!!

*****ደግማችሁ ደጋግማችሁ አድምጡት፣ የተቃውሞው መሠረታዊ ጥያቄዎች ያልገባችሁ ፍንትው ይልላችኋል። ይህ የጭቁን ኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው!
የመንግሥት ኃይሎች ኦሮሚያ ውስጥ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ “እጅግ አስከፊ” ወይም በእንግሊዝኛው ቀጥተኛ አባባል “ብሩታል” ናቸው ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል

Sunday, October 18, 2015

BREAKING NEWS

BREAKING NEWS

**********************

The public meeting convened by Oromo Federalist Congress (OFC) in Finfinne Sunday, October 18, to discuss the so-called Addis Ababa and Oromia Special Zone Integrated Development Master Plan has ended adopting a 9-point resolution expected to be announced by OFC in an official press release. Sources say the meeting concluded that the Master Plan is a land grab policy disguised as a development plan and called on Ethiopian authorities to halt it, and on the public to continue rejecting it.

Saturday, October 17, 2015

365 DAYS IN PRISON

ፍትሕና ልዕልና ጋዜጦች፣ እንዲሁም የፋክትና የአዲስ ታይምስ መፅሔቶች ባለቤትና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ከታሠረ ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም አንድ ዓመቱን ደፍኗል፡፡ የተመስገን ጤና አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቡቹ ገልጸዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ግን ተመስገን ሕክምና እያገኘ መሆኑን ጤናማም እንደሆነ ይናገራል፡፡

የተመስገን ደሣለኝ ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሣለኝ ተመስገንን ረቡዕ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ዝዋይ ሄዶ መጎብኘቱንና፣ ወንድሙ የግራ ጆሮው ሙሉ በሙሉ እንደማይሰማ፣ ጀርባው ላይ ያለው እብጠት እየባሰበት መሆኑን በጀርባው መተኛትም እንደማይችል አስረድቷል፡፡
ተመስገን ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ሕክምና እንደማያገኝና ቤተሰቡም ለማሳከም ቢጠይቅም ፍቃድ መነፈጉን፣ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ይዘው ሄደው “በማረሚያ ቤቱ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም” የሚል መልስ ማግኘታቸውን ታሪኩ ለቪኦኤ ገልጿል፡፡
ተመስገን ያዘጋጃቸው ከነበሩት መፅሔቶች በአንዱ ላይ አምደኛ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምም ከጥቂት ወራት በፊት ከፕሮፌሰር መስፍንና ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው እዚያው ዝዋይ ድረስ ሄደው እንዳዩትና በወቅቱ የግራ ጆሮው ይደማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
የተመስገን ደሣለኝ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንንም የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ ዝዋይ ሄደው ያዩት መሆናቸውንና በቦታው ርቀት ምክንያት ከዚያ በኋላ በአካል እንዳላገኙት ገልፀው ከቤተሰቦቹ ግን አሁን ያለበትን ሁኔታ እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት፣ መንግሥቱ ባወጣቸው ደንቦችና በዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችም መሠረት ማንም እሥረኛ ጤንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መያዝ እንደሚገባው፤ አስፈላጊ በሆነ ጊዜም ሕክምና የማግኘት መብት እንዳለው፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርም ሆነ የወህኒ ቤቱ ሃኪም ታራሚው ሕክምና ማግኘቱን የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የማረሚያ ቤቱ የፅሕፈት ቤት ኃላፊ ተመስገን አዲስ አበባ ድረስ ተወስዶ ሕክምና ማግኘቱን፤ በማረሚያ ቤቱ ውስጥም እየታከመ መሆኑን፣ ጤናማና እየተንቀሣቀሰ ያለ መሆኑን ገልፀው ጤንነቱ ታውኳል፤ ሕክምና ማግኘት አልቻለም የተባለው ሃሰት መሆኑን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡
ጠበቃው አቶ አምሃ ግን አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ አለመታከሙን፣ ሄዶ ቢሆን ኖሮ እርሣቸው ያውቁ እንደነበር ተናግረዋ የማረሚያ ቤቱን የሥራ ኃላፊ መግለጫ አስተባብለዋል፡፡
 

Friday, September 11, 2015

በ2008 ወንድሞቻችን፣እህቶቻችንና ኢትዮጵያ ነፃ የሚወጡበት አመት !!!

በ2008 ወንድሞቻችን፣እህቶቻችንና ኢትዮጵያ
ነፃ የሚወጡበት :የኢትዮጵያ ህዝብየ24ዓመቱን የህወሀት አገዛዝ በቃህ የሚልበት:አመት
 

Sunday, September 6, 2015

የህወሀት እስርና እንግልት ያልበገረው ፍቅር





የህወሀት እስርና እንግልት ያልበገረው ፍቅር

ቂሊንጦ የተካሄደው የቀለበት ስነስርዓት





ብዙ ጊዜ ስለተቃራኒ ፆታ ፍቅር መጻፍ ብዙመ አልወድም ወይም አይመቸኝም ይህ ተከታዩን በቂሊንጦ እስር ቤት ከሰሞኑ የተፈፀመው የቀለበት ስነስርዓት ስሠማ ግን የሆነ የተለየ ነገር ሆኖ ስላገኘሁት ትንሽ ፈለግኩኝ፡፡

ጉዳዩ እንዲህ ነው በተደጋጋሚ ከዚህ ቀደም እዚህ ፌስቡክ ላይ እንደገለፅኩት በአንድ ወቅት የአሁኑ የኢትዮጵያ አየር ሐይል አባል የነበረው ወጣት ሻለቃ አክሊሉ መዘነ የገዢውን ፓርቲ ዘረኝነት እና ጭቆና መቋቋም አቃተኝ በማለት የኢትዮጵያ አየር ሀይልን ከድቶ ኤርትራ በመግባት የትጥቅ ትግል እያካሄደ የሚገኘውን አርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሐይልን ይቀላቀላል ወጣቱ የአየር ሐይል አባል ወደአርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀሉን የሠሙት የገዢው ፓርቲ ደህንነቶች በቂም በቀል ተነሳስተው የሻለቃ መዘነ ታናሽ ወንድምን ሠይፈ መዘነን ከሚኖርበት ኮተቤ አካባቢ በመያዝ ወደማዕከላዊ በመውሰድ ከፍተኛ ድብደባ የፈፀሙበት ሲሆን በወቅቱም ይህንን ጉዳይ መረጃ አሰባስቤ ይፋ ማውጣቴ ይታወሳል፡፡ እናም ታናሽ ወንድምዬወን ሠይፈ መዘነን ማዕከላዊ ወስደው ከደበደቡት በኋላ ፍርድ ቤት እንኳን ሳይወስዱ በአሁኑ ሠዓት ቂሊንጦ ወስደው አስረውት ይገኛል አስገራሚው ነገር ሠይፈ መዘነ ከጉዳዩ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለውና ምንም አይነት ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያልነበረውና ስለጉዳዩ ምንም ሳያውቅ በግል ስራ ይተዳደር የነበረ ወጣት ነው፡፡

የሠይፈ መዘነን ወደቂሊንጦ እስር ቤት መዛወር የሠማችው ፍቅረኛው ሚዛን ፎቶው ላይ የምንመለከታት እንስት ጓደኞቿን ሰብስባ ቂሊንጦ እስር ቤት ድረስ በመሄድ ለፍቅረኛዋ ለሠይፈ መዘነ የቃልኪዳን ቀለበት አድርጋለታለች፡፡ በዙሪያዋ የሚገኙ ወጣቶች ሰይፈ በቃ ሻለቃው ወንድሙ አክሊሉ ከድቶ ኤርትራ በመግባቱ የህወሀት ሠዎች ለቂም በቀል ሠይፈን ምን አልባት ለበርካታ አመታት ሊያስሩት ይችላሉ የሚል ማስፈራሪያ ቢሠጧትም አሉባልታውንና ማስፈራሪያውን ችላ ብላ ከሠሞኑ ለሠይፈ መዘነ ቀለበት አድርጋለት እንዲህ ብላው ከቂሊንጦ እስር ቤት ለቃ ሄዳለች ""እውነት ማሸነፏ አትቀርም ያኔ አንተ ነፃ ትወጣና የቃልኪዳን ቀለበታችንወደትዳር ቀለበትነት ትለወጣለች እስከዛው ግን እጠብቅሀለው እወድሀለው""

ምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው በአሁኑ ሠዓት ቂሊንጦ በእስር ላይ የሚገኘውን ሠይፈ መዘነን እና ፍቅረኛውን ሚዛንን ነው

Ermias Tokuma Alemayehu 

Thursday, September 3, 2015

የአቶ ሃብታሙ የአቶ አብርሃም ሰሎሞን መለቀቅ ታገደ!!!

የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌውና ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች  ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲፈቱ የሰጠውን ትዕዛዝ የበታች ፍርድ ቤቱ አግዷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ውሣኔውን የሰጠው የአቃቤ ሕግን አቤቱታ ተቀብሎ ነው፡፡
ጉዳዩ ያስቀርብ ወይም አያስቀርብ እንደሆነ ለማየትም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል፡