Wednesday, July 24, 2013

ወያኔ በኦነግ አባልነት የሀሰት ክስ አቀናጅቶ በግፍ ባሰረቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ አስተላልፏል።

ወያኔ በኦነግ አባልነት የሀሰት ክስ አቀናጅቶ በግፍ ባሰረቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላይ በሚቆጣጠራቸው ዳኞችና አቃቢህጎች አማካኝነት ሽብርተኛ ናቸው በማለት የጥፋተኛነት ፍርድ አስተላልፏል።

በሽብርተኛነት ተፈርጀው ጥፋተኛ ከተባሉት ውስጥ አያሌ የአዳማ፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ እና የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።

*“በኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀ የሰብአዊ መብት ረገጣ መኖሩ ይታወቃል ይሁንና ለጋሽ ሀገሮች ይህንን ጉዳይ ከግምት ያስገቡ አይመስልም።” አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች!

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዝና የለጋሽ አገሮችና ሚና

በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ትኩረት ሳያደርጉ ዘለቄታ ያለው ልማት ማምጣት የማይቻል መሆኑን በያዝነው ወር ይፋ የሆኑ ሁለት የጥናት ዘገባዎች አመለከቱ። ለጋሽ አገሮች የሚሰጡት ገንዘብ የመብት ጥሰትን ለማባባስ ያለመዋሉን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሪፖርቱ ይጠይቃል!!

ጃዋር መሀመድ ኢሳት ከ አድማጭ ለተነሱ ጥያቄዎች ሲመልስ!

   ጃዋር መሀመድ  ኢሳት ከ አድማጭ ለተነሱ ጥያቄዎች ሲመልስ!                             


             

Friday, July 19, 2013

ቂሊንጦ የሚገኙ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል የሆኑ እሥረኞች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡



በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች ውስጥ በአብዛኛው ታስረው የሚገኙት የኦሮሞ ልጆች ናቸው

በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች ውስጥ በአብዛኛው ታስረው የሚገኙት የኦሮሞ ልጆች ናቸው” ያሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋ በቅርብ ቀን ደግሞ ከቃሊቲ እሥር ቤት ወደ አንድ መቶ የሚሆኑ እሥረኞች ቂሊንጦ ወደሚባል አቃቂ አካባቢ የሚገኝ እሥር ቤት መወሰዳቸውን አመልክተዋል፡፡

እነዚህ እሥረኞች ከሁለት ዓመታት በላይ ያለፍርድ ታስረው እየተንገላቱና ፍትሕ አጥተው እንደሚገኙ፣ ቤተሰቦቻቸው ለችግር መጋለጣቸውንና መበተናቸውን፣ እነርሱም በእሥር ቤቶቹ ውስጥ ተደጋጋሚ ድብደባ እንደሚፈፀምባቸው አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

አቶ በቀለ አክለውም ሰሞኑኑ እሥረኞቹን ለመጎብኘት ወደዚያው ተጉዘው የነበሩት የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ ልዑካን ቡድን አባላት የመንግሥት ፍቃድና ትዕዛዝ ቢይዙም በእሥር ቤቱ ኃላፊዎች እምቢተኝነት ምክንያት ሳያይዋቸው ለመመለስ መገደዳቸውን አመልክተዋል፡፡

እሥረኞቹ እየደረሰብን ነው የሚሉትን እንግልትና ያሉበትን ከባድ ሕይወት እንዲሁም ፍትሕ የዘገየባቸው መሆኑን የሚገልፅ አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለፍትሕ ሚኒስትሩ፣ ለፓርላማ፣ ለሰብዓዋ መብቶች ኮሚሽን፣ ለእምባ ጠባቂ ኮሚሽን እና ለመሣሰሉት ከፍተኛ የመንግሥት አካላት ማስገባታቸውን አቶ በቀለ ጠቁመዋል፡፡

እየደረሱ ናቸው የሚሏቸው በደሎች ከቁጥጥር ዋጭ የሆኑ እንደሚመስላቸው የተናገሩት አቶ በቀለ ነጋ እሥረኞቹ አሁን የሚገኙት በረሃብ አድማ ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡

Tuesday, July 16, 2013

በቂልንጦ እስርቤት የእሰረኞች ደም በድብደባ እንደጎርፍ መፍሰሱን የአይን እማኞች ተናገሩ

በቂልንጦ እስርቤት የእሰረኞች ደም በድብደባ እንደጎርፍ መፍሰሱን የአይን እማኞች ተናገሩ





አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል። እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ ብይን በሚሰጥበት ወቅት ለ4 ወራት ተራዝሟል መባሉ ተገቢ አይደለም” በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የሚላክ ፊርማ ማሰባሰብ ሲጀምሩ ማረሚያ ቤቱ መረጃው ይደርሰውና 69ኙ እሰረኞች በ20 ተከፋፍለው ወደ ተለያዩ የማረሚያ ክፍሎች ወይም ዞኖች እንዲበተኑ ይደረጋል።
አርብ ጧት ሌሎች እስረኞች ወደ ውጭ እንዳይወጡ ከተደረገ በሁዋላ ፣ ሻእቢያ በሚባለው የእስር ቤቱ ሀላፊና ከውጭ በመጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲደበደቡ ይደረጋል። አስተባባሪ ናቸው የተባሉትን 18 እስረኞችን እንደገና በማውጣት በሰደፍና እና በዱላ ከቀጠቀጡዋቸው በሁዋላ 8ቱ ራሳቸውን ሲስቱ ወደ እስር ቤቱ የህክምና ክፍል ይወሰዳሉ። ችግሩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን የእስር ቤቱ የህክም ክፍል በመግለጹ፣ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጹት እስረኞቹ የተደበደቡበት ቦታ በደም በመጨቅየቱ አርብ እለት በውሀ ሲታጠብ አርፍዷል።
ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በላይ ኮርሜ ፣ ተፈሪ ቀብኔሳ እና መንግስቱ ግርማ የሚባሉ ይገኙበታል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአህኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና እሰረኞቹ መደብደባቸውንና የተወሰኑት ሆስፒታል መግባታቸውን መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸዋል።
ዶ/ር መረራ “ድርጊቱን በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተን መልስ በማጣታችን መንግስት ሆን ብሎ በፖሊሲ ደረጃ ይዞ የሚያካሄድ ይመስላል” ሲል አክለዋል።
የእስር ቤቱን ሀላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

ኢሳት ዜና

Monday, July 15, 2013

ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ታገቱ

ሰበር ዜና

በጎንደርና በደሴ በደረሰበት ፖለቲካዊ ኪሳራ የተበሳጨው ኢህአዴግ ዛሬ ከ28 በላይ የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላትን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች አግቷል፡፡ የታጋቾቹን ስም ዝርዝርና የታሰሩባቸውን አከባቢዎች ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ እናደርጋለን፡፡

Sunday, July 14, 2013

የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነቶ ተነስታል ብረት ሊያስቆመው የማይችለው ትግል ተቀጣጥላል!!!


የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነቶ ተነስታል ብረት ሊያስቆመው የማይችለው ትግል ተቀጣጥላል!!!

                              1 . ፍርሃት የወለደው ታጋሽነት .....ለብዙ ሕግወጥ ድርጊት ዳርጎናል !!!
                                        
2. የታሰሩት የህሊናና የፓለቲካ እሰረኞች ባሰቸኳይ ይፈቱ !!

3 . ውሽት ሰልችቶናል ይቁም !!

4 . በፈጠራ ክስ በዜጎች ላይ የሚፈፀመው ግፍ ባሰቸኳይ ይቁም !

                                                 
አንድነት ፓርቲ በጎንደርና በደሴ የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ 






የኢትዮጵያ ህዝብ ለነፃነቶ ተነስታል ብረት ሊያስቆመው የማይችለው ትግል ተቀጣጥላል!!!