Saturday, March 30, 2013
Friday, March 15, 2013
ፊን ፊሸር ሰላዩ ቫይረስ!!!
ፊን ፊሸር የተባለ የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም በዓለም 25 ሀገሮች ዉስጥ መሠራጨቱንና መንግስታቱም የገዛ ዜጎቻቸዉን ለመሠለል እንደሚጠቀሙበት አንድ ጥናት አመለከተ። ኢትዮጵያ ዉስጥም በሠፊዉ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን ጥናቱ ይፋ አድርጓል።
http://www.dw.de/%E1%8D%8A%E1%8A%95-%E1%8D%8A%E1%88%B8%E1%88%AD-%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%8B%A9-%E1%89%AB%E1%8B%AD%E1%88%A8%E1%88%B5/a-16678127
ሙሉ ዘገባውን==>

Tuesday, March 12, 2013
Wabeshebelle Hotel: 'You can't eat the dinner you payed for!'
Guests of Semayawi Party- Ethiopia were denied entry to eat dinner with Prof. Mesfin Woldemariam and others last Friday, March 8, 2013, at Wabeshebelle Hotel in Addis Ababa. The dinner was already payed for. The management told the invited guests that' they had 'technical' issue.
Sunday, March 10, 2013
ETHIOPIA: ACADEMIC INSTITUTIONS ARE MEANT TO TEACH; NOT TO SERVE AS POLITICAL TOOLS

HRLHA Appeal and Urgent Action
March 4, 2013 (HRLHA) — The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA) strongly condemns the academic dismissals and suspensions of ten students of Addis Ababa University from their studies on February 21, 2013 upon their return to the University to resume their studies after a two-week break following the end of the first term exam. According to information obtained through HRLHA informants, this purely racial and politically motivated decision handed down by what is known as the discipline committee of the University was connected with the incident that took place in January 2013 between the Tigre and Oromo students. Various sources, including the HRLHA, have reported that the clash between the two groups of students was triggered when some students of Tigre nationals posted posters containing derogatory messages that aimed at the Oromo people. In connection with this incident, HRLHA had then reported, under an urgent action entitled, “Beatings, Arrests and Detentions at Addis Ababa University”, that more than 100 Addis Ababa University students, the majority of whom were Oromos, were arrested and detained.
All the ten dismissed and/or suspended students, one of whom was a female, spent about a month in detention before they were released on bail and returned to the University. The ten students who were given academic dismissal and suspension were:
March 4, 2013 (HRLHA) — The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA) strongly condemns the academic dismissals and suspensions of ten students of Addis Ababa University from their studies on February 21, 2013 upon their return to the University to resume their studies after a two-week break following the end of the first term exam. According to information obtained through HRLHA informants, this purely racial and politically motivated decision handed down by what is known as the discipline committee of the University was connected with the incident that took place in January 2013 between the Tigre and Oromo students. Various sources, including the HRLHA, have reported that the clash between the two groups of students was triggered when some students of Tigre nationals posted posters containing derogatory messages that aimed at the Oromo people. In connection with this incident, HRLHA had then reported, under an urgent action entitled, “Beatings, Arrests and Detentions at Addis Ababa University”, that more than 100 Addis Ababa University students, the majority of whom were Oromos, were arrested and detained.| No | Name | Sex | Department & Year | Birth Place |
| 1 | Tadele Tarkegn | M | Earth Science – 3rdyear | Nekemt/Wolega, Oromia |
| 2 | Abebe Tuji Chala | M | Biology 3rd year | South Showa, Oromia |
| 3 | Gemechu Deleto Dafo | M | Science 4th | |
| 4 | Melkamu Mulugeta Kefyalew | M | Physics 4th | Liben, Oromia |
| 5 | Fikadu Meserra | M | Chemistry 3rd | Chalia, Gedo, Oromia |
| 6 | Addis Gatera Yadessa | F | Mathematics 4th | |
| 7 | Bekalu Siyum Teshale | M | Mathematics 4th | Ajje, Oromia |
| 8 | Kajela Adimasu Deressa | M | Biology 3rd | Aira, Wolegga, Oromia |
| 9 | Isayas Itana | M | Geology 2nd | Mendi, Wollega, Oromia |
| 10 | Ararsa Waktola Oljirra | M | Earth Science 4th | Limu, Wollega, Oromia |
Saturday, March 9, 2013
Journalism under Ethiopia's anti-terrorism law

==>silence dissident journalists
Our feature takes us to Ethiopia where the US 'war on terror' has provided cover for laws that are being used to silence dissident journalists. Reeyot Alemu is one of those journalists - she has been sentenced to five years in jail. Foreign reporters have also been charged under anti-terrorism laws for daring to communicate with opposition groups. The Listening Post's Nic Muirhead takes a closer look.
===============>>>> ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ
Thursday, February 28, 2013
Oromo Students expelled not one Tigray
Oromo studenst have been suspended and expelled from Addiss Abab University but not one Tigray or Amhara that were involved.
They were expelled and suspended for a riot that took place based on a deragotry insult written on a wall against Oromos. The writers of dergatory are Tigrays. The riot included Tigrays, Amahras and Oromos. But Oromos were singled out and expelled and and suspended. Not one Tigray was reprimanded or expelled.

Friday, February 22, 2013
መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል
መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል?
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ-ማርያም
የካቲት 2005
በአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤ የአንድ አገር ዜጎች የተለያየ ዘር፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም፣ የተለያየ ቁመትና ውፍረት፣ የተለያየ ጾታና ዕድሜ፣ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ሃይማኖት፣ የተለያየ የፖሊቲካ አመለካከት፣ የተለያየ ትምህርት፣ የተለያየ ሙያና የተለያየ ገቢ ሊኖራቸው ይችላል፤ የጋራ ማንነታቸው ዜግነት ነው፤ እኩልነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ አንድነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያረጋግጥላቸውና ሚዛኑን የሚጠብቅላቸው ከበላይ ሆኖ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ነው፡በቡድን ወይም በጅምላ የሚያስቡ ሰዎች የሕግን ባሕርይ አያውቁትም፤ ‹‹ክርስቲያኖች እስላሞችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ ወይም እስላሞች ክርስቲያኖችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ በሚል አሉባልታ ላይ ክስ ተመሥርቶ ሕጋዊ ፍርድ መጠበቅ አይቻልም፤ በየትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ጽንፈኛ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ሕልማቸውንም ሆነ ቅዠታቸውን በስውርም ሆነ በአደባባይ ይገልጻሉ፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ጥቁሮችንና ይሁዲዎችን ከአገሩ ጠራርገን እናወጣና ንጹሕ የነጮች አገር እንፈጥራለን የሚሉ ግለሰቦች አሉ፤ ይህ እምነት ለአሜሪካ ማኅበረሰብ መርዝ ነው፤ አሜሪካ የነጻነት አገር ነው፤ የነጭ ዘረኞቹ መርዛቸውን ለመንዛት መብት አላቸው፤ የዘረኞቹን መብት ለማፈን የሚወሰድ የጡንቻ እርምጃ ሁሉ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ይሽራል፤ ከዚያም በላይ የአሜሪካ መንግሥት በሚከተለው ዘዴ ከነጭ ዘረኞቹ የተሻለ አይሆንም ነበር፤ ስለዚህም ነጭ ዘረኞችን ለመቋቋም የሚወሰደው አርምጃ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ሳይሽርና ነጭ ዘረኞቹም እምነታቸውን የመግለጽ መብታቸው ሳይደፈጠጥ መሆን አለበት፤ የነጻነት ትርጉሙ ይህ ብቻ ነው፡፡
በሥልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጡ ብቻ አንድ ዓይነት የፖሊቲካ እምነት ብቻ ይዞ ሌላውን መደፍጠጥ፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የኦርቶዶከስ ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን፣ መንግሥት የባረከውን አንድ ዓይነት የእስልምና ሃይማኖት ብቻ ማደርጀትና ሌላውን ማፈን ልማድና የአሠራር ባህል እየሆነ ሲሄድ ሁሉንም ነገር አንድ ዓይነት ብቻ ለማድረግ የሚታየው ጥረት የኢትዮጵያን ጉራማይሌ ባሕርይ የሚቃረን በመሆኑ ስር አይኖረውም፤ ይህ ሁሉም ሰው ሊያስብበት የሚገባው አንዱ ነገር ነው፤ ሁለተኛው አንድ ወይም ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ቢሉ አገር የሚሸበርበት ምንም ምክንያት የለም፤ ኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አገር ለማድረግ የሚመኙም አሉ፤ ኢትዮጵያን ሃይማኖት-አልባ የጉግማንጉግ አገር ለማድረግ የሚፈልጉ አሉ፤ ኢትዮጵያ በአንድ አጋጣሚ ወንበሩ ላይ የወጣ ጉልበተኛ የሚያትምባትን እምነትም ሆነ ሃይማኖት የማትቀበል አገር መሆንዋ ተደጋግሞ የታየ ነው፤ ኢትዮጵያን የይሁዲ አገር ለማድረግ ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የክርስቲያን አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ኢትዮጵያን የእስላም አገር ለማድረግም ተሞክሮአል፤ ሁሉም አልሆነም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ሆና ዘልቃለች፤ ይህንን በማክሸፍ ለማንም ምንም ጥቅም አይገኝም፤ በአንጻሩ ደግሞ የሥልጣን ወንበሩ ላይ የወጡ ጉልበተኞች ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጉጉት የሚጠብቀውን የነጻነት ጮራ እያዳፈኑ የነጻነትን፣ የእኩልነትንና የሕግ የበላይነትን ዓላማ ለማክሸፍ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፡፡
የነጻነትና የሕጋዊነት መክሸፍ የሰላም ጠንቅ ነው፤ የሰላም መክሸፍ የልማት ጠንቅ ነው፤ የልማት መክሸፍ ደሀነት ነው፤ ደሀነት የሞት አፋፍ ነው፤ ይህንን ለመገንዘብ የሚያዳግተው ሃያ አንድ ዓመት የሞላው ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለመምራት የሚደናበሩት ሰዎች ሁሉ ሃያ አንድ ዓመት አልፎአቸዋል፤ ነገር ግን ከላይ የተገለጸው የመክሸፍ ጉዞ ጭራሽ አይታያቸውም፤የሚታየውም ሲነግራቸው የተበለጡ ስለሚመስላቸው አይሰሙትም፤ ስለዚህም የሚታየውን ሳያዩ፣ የሚሰማውን ሳይሰሙ ጊዜ የሚበላውን ጉልበታቸውን ብቻ ተማምነው በጭፍን እንምራችሁ የሚሉትን ተከትለን ለእኛ በሚታየንና ለእነሱ በተሰወረባቸው ገደል ውስጥ ለምን አብረን እንግባ? አብረን ገደል በመግባት አንድነታችንን የምንጠብቅ የሚመስላቸው ሰዎች በሁለት በኩል ይሳሳታሉ፤ አንደኛ ከአገዛዙ መሪዎች ዘንድ የሎሌ ተከታይነትን እንጂ የአኩልነት አንድነትን አያገኙም፤ እኩልነት በሌለበት አንድነት አይፈጠርም፤ ሁለተኛ ወደገደል የሚጨምር አንድነትን መምረጥ ሕይወትን ትቶ ሞትን መምረጥ ነው፡፡
በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ መክተፍ-መከታተፍ ሙያ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችና ድርጅቶች ሠለጠኑበት፤ መክተፍ-መከታተፍ አብሮ የመኖር ጸር ነው፤ አብሮ የመኖር ጸር የሚሆነው በፍቅር ፋንታ ጥላቻን፣ በሰላም ፋንታ ጠብን፣ በመረዳዳት ፋንታ መጋጨትን፣ በልማት ፋንታ ጦርነትን በመንዛት ነው፤ አንዳንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በግልጽም ሆነ በስውር እንደጠላት መቁጠርና በእነሱ ላይ ቂምን እንዲቋጥሩ ማድረጉ የማንንም የፖሊቲካ ቡድን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ይጎዳል እንጂ አይረዳም፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ በኩል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ በየገዳማቱና ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በሊቀ ጳጳሳት ምርጫው ላይ አገዛዙ እያሳየ ያለው ጣልቃ-ገብነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን እያስቀየመና እያስኮረፈ ነው፤ በሌላ በኩል በእስልምና ሃይማኖት ላይም የሚታየውን ጣልቃ-ገብነት ተከታዮቹ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በርትተው በመቋቋማቸው እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ለጆሮ እየቀፈፈና በጣም አሳፋሪ እየሆነ ነው፡፡
ይህ በሃይማኖቶች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ውጤት ይኖረዋል፤ ውጤቱ በአገዛዙ የውስጥም ሆነ የውጭ አመራሩ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖረዋል፤ የሃይማኖቶቹ ጉዳይ እንደጎሣዎች መከታተፍ በኑሮ ላይ ብቻ ጫናውን የሚያሳርፍና በምድር የሚንከላወስ አይደለም፤ ወደሰማይ ያርጋል፤ የሰማይ ሠራዊትን ይጠራል፤ ያንን ኃይል እንኳን የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአሜሪካውም አይችለውም፤ ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ ልብ ያለው ያስተውላል፤ ዶላር ነፍስን አይገዛም፤ ክብርን አይገዛም፤ ወዳጅንም አይገዛም፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)