Monday, December 31, 2012
Sunday, December 30, 2012
ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው
ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን አጀንዳ በቀጣይ ስብሰባ ለመመልከት ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ለጉባዔው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ቀደም ብለው በማወቅ በጉዳዩ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች ካሉ ደግሞ ሰነዶቹ ከውይይቱ ሦስት ቀናት በፊት እንዲደርሳቸው የምክር ቤቱ የአሠራር ደንብ ቢደነግግም፣ የሕግ ከለላን ስለማንሳት ቀርቦ ስለነበረው አጀንዳ የቀረበላቸው ምንም ዓይነት ሰነድ እንደሌለ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የሕግ ከለላው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት የምክር ቤት አባል ማንነት በይፋ ባይገለጽም፣ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ መሆኑን እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጁነዲን ሳዶ በአሁኑ ወቅት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ ጋር በተያያዘ፣ በድርጅታቸው ኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግመው ከፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ወደ ተራ አባልነት ዝቅ መደረጋቸው ይታወሳል አቶ ጁነዲን ሳዶ በአሁኑ ወቅት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸውን ተዘግቧል፡
Sunday, December 23, 2012
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና እነ አንዱዓለም አራጌ የይግባኝ ክርክራቸውን አጠናቀቁ!!!
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና እነ አንዱዓለም አራጌ የይግባኝ ክርክራቸውን አጠናቀቁ!!!
--------ኢሳትም የመገናኛ ብዙኃን እንጂ የአሸባሪ ድርጅት ሚዲያ አለመሆኑን ማረጋገጣቸውን < አቶ ደርበው ገልጸዋል፡፡
--------ለአንድ ዓመት ከሦስት ወር መሬት ላይ እንዲተኛ መደረጉን
---------ትንሽ ብርሃን ባለበት በጨለማ ክፍል ውስጥ ከስድስት ሰዎች ጋር መታሰሩን
-------- የመተንፈስ ችግር እንዳለበት
---------ከተወሰኑ ቤተሰቦቹ በስተቀር ሌላ ሰው እንዳይጠይቀው መከልከሉን አስረድቷል
አንዱዓለም አራጌ
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በ18፣ በ25 ዓመታትና በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጥተው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) እና አንዱዓለም አራጌ ቅጣታቸውን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ላይ ከዓቃቤ ሕግ ጋር ታህሳስ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ክርክር አድርገው አጠናቀቁ፡፡ አንዱዓለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንንና ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) ክርክራቸውን ያደረጉት በጠበቃ ተወክለው ሲሆን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ግን ክርክሩን ያደረገው ያለጠበቃ በራሱ ነው፡፡
ጋዜጠኛ እስክንድር ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ወይም ባደረገው ክርክር ላይ በዋናነት ያነሳው ነጥብ፣ የግንቦት 7 ድርጅት አባል ስለመሆኑ የተገኘበት መረጃም ይሁን የሰው ምስክር በዓቃቤ ሕግ እንዳልቀረበበትና “አባል ነው” መባሉም ፍፁም ሐሰት መሆኑን ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤትም በዋናነት ሲከራከርበት የነበረበትንና “የግንቦት 7 ዓባል ስለመሆኔ ዓቃቤ ሕግ ምንም ዓይነት ማስረጃ ባላቀረበብኝና ባልተመሰከረብኝ ሁኔታ እንዴት ልቀጣ እችላለሁ?” የሚለውን ሐሳብ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው የክርክር ሐሳብም በዋናነት ተናግሯል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በሥር ፍርድ ቤት ላቀረበበት ክስ በዋና ማስረጃነት ያቀረበው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተናገራቸውንና የጻፋቸውን የተለያዩ መጣጥፎች፣ እሱን ጨምሮ ሰባት ሆነው ሊመሠርቱት ስለነበረ የሲቪክ ማኅበር መመሥረቻ ጽሑፍ እንጂ የሰው፣ የሰነድም ሆነ የኢ-ሜይል ማስረጃዎች እንዳልቀረቡበትና በፍፁም የግንቦት 7 ድርጅት አባል አለመሆኑን አስረድቷል፡፡
ዓቃቤ ሕግ እንደ ዋና ማስረጃ ያቀረበበት በመስከረም ወር 2004 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት የመኢዴፓ ዋና ጸሐፊ ከአቶ ዘመኑ ሞላ ጋር ያደረገውን ንግግር መሆኑን ጋዜጠኛ እስክንድር አስረድቷል፡፡ አቶ ዘመኑ ወደሱ መጥቶ ሰለ ሰላማዊ ሠልፉ ምክር ሲጠይቀው፣ ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ወቅቱ እንዳልሆነ፣ ሠልፍ የሚያደርጉም ከሆነ በማንኛውም መንገድ የውጭ ኃይሎች እጅ ሊኖርበት እንደማይገባኧ የገንዘብ እጥረት ቢኖርባቸው እንኳን እሱም ቢሆን በገንዘብ ሊረዳቸው እንደሚችል ከመመካከር ውጭ፣ አንዲትም ቃል ስለአመፅና ረብሻ ተነጋግረው እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ አቶ ዘመኑም በሥር ፍርድ ቤት ለዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው በቀረቡበት ወቅት ያረጋገጡት ይህንኑ መሆኑንና ፍርድ ቤቱ የሥር ፍርድ ቤት መዝገብን ሊመለከተው እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በሰሜን አፍሪካና በዓረብ አገሮች የተቀሰቀሰውን አመፅ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ነበር በማለት ስላቀረበበት ክስ ጋዜጠኛ እክስንድር ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፣ “ዓቃቤ ሕግ ይህንን ሐሳብ ወይም ክስ ያቀረበው እኔ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ያቀረብኳቸውን መጣጥፎች በግንቦት 7 ልሳን ላይ ስላገኛቸው እንጂ፣ ምንም ዓይነት እውነተኛ ማስረጃ አግኝቶ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ እንኳን ለተቃውሞ የቆመ ድርጅትን ቀርቶ ማንም ከተለያዩ ድረ ገጽ ላይ ወስዶ ራሱ በፈለገው ቅርፅና አመለካከት ቀይሮ ሊያቀርበው ይችላል፡፡ የእኔን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም መጣጥፍ እንደፈለጋቸው የሚያደርጉ ናቸው፤” ብሏል፡፡
የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ በተሳሳተ ሁኔታ እየተተረጐመ መሆኑን የጠቆመው ጋዜጠኛ እስክንድር፣ ሌላው የተከሰሰበት ወንጀል የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን አንቀጽ 23 ተላልፏል በሚል መሆኑን ተናግሯል፡፡ ዓላማውም እንደ ዓረብ አገሮች የመንግሥትን ሥልጣን በኃይል ለመያዝ መሆኑን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ማስረዳቱን የገለጸው ጋዜጠኛው፣ በዓረብ አገሮች ማለትም በግብፅ፣ በቱኒዝያ፣ በሊቢያ፣ በየመንና በሶሪያ የተደረገው አመፅ ዓቃቤ ሕግ ከሚለው በእጅጉ የተለየ መሆኑን አስረድቷል፡፡ “የሥር ፍርድ ቤት በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የዓረብ አገሮች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ዓላማ መከተልህ ትክክል አይደለም” በማለት ፈርዶብኛል፡፡ እኔ በፖለቲካ ድርጅት ተመርቼ ያደረግኩት እንቅስቃሴ የለም፡፡ ለአገሬ ይጠቅማል ብዬ ስላመንኩና አሁንም ስለማምን፣ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ ዓላማ ነው ያለኝ፡፡ በዓረብ አገሮች የተደረጉ አመፆች በፖለቲካ ድርጅት የታገዙ አይደሉም፡፡ የታገሉት ወይም እየታገሉት ያለው ለነፃነትና ለፍትሕ ነው፡፡ ይህንንም ድርጊታቸውን የአፍሪካ ኅብረት ሙሉ ዕውቅና ሰጥቶታል፡፡ ይህ ድርጊታቸው እንደ ምሳሌ እንጂ እንደ ተቃውሞ ሊወሰድ አይገባም፡፡ አድርገሃል ስለተባልኩት ነገር ሁሉ አንድ ማስረጃ ከተገኘ ጥያቄዬን አነሳለሁ፤” ብሏል፡፡ በግልጽ ያደረጋቸው ቃለ ምልልሶች፣ በአንድነት ፓርቲ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ተጋብዞ ያደረጋቸው ንግግሮችና በተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ላይ በግልጽ የጻፋቸውን መጣጥፎች፣ ዓቃቤ ሕግ በማስረጃነት ከማቅረቡ ውጭ ምንም ዓይነት የተደበቀና ሚስጥር ነው የተባለ ማስረጃ እንዳላቀረበበት ጋዜጠኛ እስክንድር አስረድቷል፡፡
Thursday, December 20, 2012
አራት ኢትዮጵያዊን ጋዜጠኞች የሄልማን/ሃሜት ተሸላሚ ሆኑ
![]() |
አራት ኢትዮጵያዊን ጋዜጠኞች የሄልማን/ሃሜት ተሸላሚ ሆኑ
መስፍን ነጋሽ ,ውብሸት ታየ ,እስክንድር ነጋ ,ርዕዮት ዓለሙ
አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የሚዲያ ሥራ በዓለም እጅግ አዳጋች በሆነበት ሀገራቸው ሃሣብን በነፃ የመግለፅ መብቶች እንዲከበሩ ላደረጓቸው ጥረቶች (እአአ) የ2012ን ስመ-ጥሩን የሄልማን/ሃሜትን ዓለምአቀፍ ሽልማት አግኝተዋል
በሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ድርጅት በሂዩማን ራይትስ ዋች አስተዳደር ጥላ ሥር የሚገኘው ሄልማን/ሃሜት በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የፖለቲካና ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዒላማ ለሆኑ ደራሲዎችና ጋዜጠኞች ሽልማቱን የሚሰጠው በያመቱ ነው።
ስመ ጥሩ ሽልማት መጠሪያውን ያገኘው እአአ በ1950ዎቹ ፀረ-ኮሚኒስት ምርመራዎች ወቅት ወከባ ከደረሰባቸው ሁለት ጋዜጠኞች ከሊልያን ሄልማን እና ዳሸል ሃሜት ነው።
እስክንድር ነጋ ፈንታ፥ ነፃ ጋዜጠኛና ብሎገር ወይም የኢንተርኔት አምደኛ፥
ርዕዮት ዓለሙ ጌቤቦ፥ በታገደው ሣምንታዊ “ፍትሕ” ጋዜጣ አምደኛ፥
ውብሸት ታየ አበበ፥ የተከለከለው ሣምንታዊ “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፥
የ “አዲስ ነገር Online” አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ፥ የዘንድሮውን ሽልማት ካገኙ ከ 19 ሀገሮች የተውጣጡ 41 ጋዜጠኞችና ፀሀፊዎች መካከል ናቸው።
እስክንድር፥ ርዕዮትና ውብሸት ባሁኑ ወቅ ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ የአዲስ ነገሩ መስፍን ነጋሽ ግን፥ እአአ በ2009 ዓ.ም ሀገሩን ጥሎ ወጥቶ በስደት ላይ ይገኛል።
ባጠቃላይ አራቱም ግን በሀገሪቱ በፀረ ሽብር ሕግ መሠረት በዚህ ዓመት ጥፋተኞች ተብለው ተፈርዶባቸዋል።
ርዕዮት ዓለሙ ጌቤቦ፥ በታገደው ሣምንታዊ “ፍትሕ” ጋዜጣ አምደኛ፥
ውብሸት ታየ
ውብሸት ታየ አበበ፥ የተከለከለው ሣምንታዊ “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፥
መስፍን ነጋሽ
የ “አዲስ ነገር Online” አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ፥ የዘንድሮውን ሽልማት ካገኙ ከ 19 ሀገሮች የተውጣጡ 41 ጋዜጠኞችና ፀሀፊዎች መካከል ናቸው።
እስክንድር፥ ርዕዮትና ውብሸት ባሁኑ ወቅ ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ የአዲስ ነገሩ መስፍን ነጋሽ ግን፥ እአአ በ2009 ዓ.ም ሀገሩን ጥሎ ወጥቶ በስደት ላይ ይገኛል።
ባጠቃላይ አራቱም ግን በሀገሪቱ በፀረ ሽብር ሕግ መሠረት በዚህ ዓመት ጥፋተኞች ተብለው ተፈርዶባቸዋል።
Tuesday, December 18, 2012
እስክንድር ነጋ እንዲፈታ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ጠየቁ
እስክንድር ነጋ እንዲፈታ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ጠየቁ
የአውሮፓ ፓርላማ 16 አባላት በጋዜጠኛና የኢንተርኔት አምደኛው እስክንድር ነጋ የተራዘመ እሥር የተሰማቸውን ብርቱ ሥጋት በመግለፅ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ደብዳቤ ፅፈዋል፡
የደብዳቤውን ይዘት እና የተፃፈበትን ምክንያት አስመልክቶ የቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት ኃላፊ ፒተር ሃይንላይን “ፍሪደም ናው” የሚባለውን ተቀማጭነቱ ዋሽንግተን ዲሲ የሆነ በነፃነትና በፖለቲካ እሥረኞች ጉዳዮች ላይ የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የፕሮግራም ጠበቃ ፓትሪክ ግሪፊትዝን አነጋግሯል፡፡
“የአቶ እስክንድር መታሠር በዓለምአቀፍ ደረጃ ጥበቃ የሚደረግለትን ሃሣቡን በነፃነት የመግለፅ መብቱን የተጋፋ ነው፡፡ ደብዳቤውን የፃፉት የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን የጠየቁት እስክንድር ነጋ ሳይዘገይ እና ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ሥልጣናቸው የሚፈቅድላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው፡፡“ ብለዋል ፓትሪክ ግሪፊትዝ፡፡
“ግልፅነት ይጎድለዋል” እየተባለ በሚተቸው ፀረ-ሽብር ሕግ የተከሰሰው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ18 ዓመት እሥራት ተፈርዶበት ወህኒ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ከዓመት በፊት ታስሮ ለሁለት ወራት ያህል ከጠበቆች ጋር እንዳይገናኝ ተደርጎ መቆየቱን የሚያስታውሰው ዛሬ የወጣው የ“ፍሪደም ናው” መግለጫ እስክንድር የታሠረውና ተከስሦም የተፈረደበት የዐረቡን ዓለም አብዮት ዓይነት ንቅናቄ ኢትዮጵያ ውስጥም ሊከሰት እንደሚችል የሚናገር ፅሁፍ በኢንተርኔት በማውጣቱና በግልፅም በመናገሩ እንደነበረ ጠቁሟል፡፡
ደብዳቤው የኢትዮጵያ መንግሥት ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የማክበር ግዴታ እንዳለበት ያስታውስና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን በሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ወደፊት እንዲመሩና ከመንግሥታት ማኅበረሰብ ቤተሰብነት ያቀላቅሏት ዘንድ የተለየ ዕድልና አጋጣሚ ያላቸው መሆኑን ያሣስባል፡፡
እስክንድር ነጋ

Voa Amharic
Monday, December 17, 2012
ETHIOPIAN MUSLIM ACTIVISTS DENY TERROR CHARGES
ETHIOPIAN MUSLIM ACTIVISTS DENY TERROR CHARGES
BY KIRUBEL TADESSE
Ap
BY KIRUBEL TADESSE
Ap
ADDIS ABABA, Ethiopia (AP) -- A group of more than two dozen Ethiopian Muslims pleaded not guilty on Monday to charges of terrorism.
Federal prosecutors are accusing the group, which includes prominent clerics and journalists, with terrorism and attempts to create an Islamic state that would undermine the country's secular constitution. Among the 28 pleading not guilty was the wife of a former senior Cabinet minister who was fired last month after publicly defending her. One defendant did not plead and instead said he was mentally unfit to stand trial.
"I have not committed any crimes but a crime has been committed against me," one defendant told the court.
The charges come amid running confrontations between authorities and Muslim protesters who accuse the government of unconstitutionally encouraging a moderate teaching of Islam called Al-Ahbash. Some of protests turned violent and eight people were killed in two spate incidents in regional towns.
The group of 29, through their 11 lawyers, had challenged the charges as unconstitutional. A three-judge panel at the country's federal court disagreed in a ruling read out Monday.
For over a year protesters at a mosque in the capital, Addis Ababa, have demanded that the government stop meddling in their religious affairs.
Right groups blame the government for the latest tension with the Muslim community. Amnesty International says the protests were first triggered when the state started "unconstitutionally meddling" in religious affairs and squashed peaceful protests with "excessive force." The United States Commission on International Religious Freedom has said the charges are part of an attempt to "crush" members of the opposition.
The Ethiopian government blames "extremists" for the ongoing protests.
"Despite the allegation of the USCIRF, it has consistently been the position of the government, both in theory and in practice, that religion is constitutionally excluded from the dominion of the state," the country's Ministry of Foreign Affairs said in a statement.
The judges said the case would reconvene Jan. 22 to hear from the witnesses of the prosecution
Thursday, December 13, 2012
አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች ከሦስት ዓመታት እስከ 13 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትናንትና ተወሰነባቸው
<<በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋ መምህርና የመድረክ ፓርቲ አመራር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች ከሦስት ዓመታት እስከ 13 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትናንትና ተወሰነባቸው
አንደኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባን በስምንት ዓመታት፣ የኦህኮ ፓርቲ አመራር የነበሩትን አቶ ኦልባና ሌሊሳን በ13 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
ሌሎቹ ተከሳሾች ማለትም ወልቤካ ለሜ፣ መሐመድ ቡሳ፣ ሐዋ ዋቆ፣ ደረጀ ከተማ፣ አዲሱ ሙከሪና ገልገሎ ቱፋ ከሦስት እስከ 12 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳና አቶ ገልገሎ ቱፋ ለአራት ዓመታት ከማንኛውም ማኅበራዊ መብቶቻቸው ታግደዋል፡፡ ሌሎቹም ለሁለት ዓመታት ታግደዋል፡፡
ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ አቶ በቀለ ጥፋተኛ አለመሆናቸውንና አድርገዋል በተባሉት ጉዳይ ላይ ምንም ነገር እንዳልፈጸሙ፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት ሲታገሉ ሕዝቡን በድለው ከሆነ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ከመጠየቅና ባለቤታቸው በእሳቸው ምክንያት ከሥራ በመባረራቸው ልጆቻቸው ያለ ገቢ ከመኖራቸው በስተቀር፣ ምንም ያጠፉት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አቶ ኦልባናም ለምን እንደታሰሩ አለማወቃቸውን ከመግለጽ በስተቀር ምንም ባለማለታቸው በሁለቱም ላይ ቅጣቱ ከብዶ ተወስኗል፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)