Sunday, December 30, 2012

ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው


ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች  እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን አጀንዳ በቀጣይ ስብሰባ ለመመልከት ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ለጉባዔው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ቀደም ብለው በማወቅ በጉዳዩ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች ካሉ ደግሞ ሰነዶቹ ከውይይቱ ሦስት ቀናት በፊት እንዲደርሳቸው የምክር ቤቱ የአሠራር ደንብ ቢደነግግም፣ የሕግ ከለላን ስለማንሳት ቀርቦ ስለነበረው አጀንዳ የቀረበላቸው ምንም ዓይነት ሰነድ እንደሌለ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ 
የሕግ ከለላው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት የምክር ቤት አባል ማንነት በይፋ ባይገለጽም፣ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ መሆኑን እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጁነዲን ሳዶ በአሁኑ ወቅት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ ጋር በተያያዘ፣ በድርጅታቸው ኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግመው ከፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ወደ ተራ አባልነት ዝቅ መደረጋቸው ይታወሳል  አቶ ጁነዲን ሳዶ በአሁኑ ወቅት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው  ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸውን ተዘግቧል፡

1 comment: